አንድ እርምጃ›› የመድረክ ቴአትር

‹‹አንድ እርምጃ›› የመድረክ ቴአትር ለእይታ ቀረበ

*************************************************

(ጥር 20/2015 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ‹‹ሰላም ለሁሉም  ሁሉም ለሰላም›› የሚል መሪ ሀሳብ ያነገበው አንድ እርምጃ ቴአትር ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ተዘጋጅቶ የቀረበ የመድረክ ቴአትር ሲሆን በፔዳ ግቢ አዳራሽ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለእይታ ቀርቧል።

የአንድ እርምጃ ቴአትር ደራሲና አዘጋጅ ቢንያም ወርቁ ሲሆን በቴአትሩ ‹‹ሰላም ለሁሉም  ሁሉም ለሰላም›› ያለውን አስፈላጊነት በተለይም አገራችን ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያጋጠማት ያለው የዘረኝነትና ጎጠኝነት ችግር ዜጎቿን ለሞትና መፈናቀል እየዳረጋቸው በመሆኑ ይህ አላስፈላጊ ድርጊት መቆም እንዳለበት ግንዛቤ የሚፈጥር ቴአትር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቴአትሩን ለመመልከት ከዩኒቨርሲቲው ሁሉም ግቢዎች የመጡ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

 በቴአትሩ ይገረም ደጀኔ፤ ፍቃዱ ከበደ፤ ሸዊት ከበደ፤ ትዕግስት ግርማ፤ያሬድ ኢጉ፤ሰለሞን ሀጎስ፤ ማህሌት ሰለሞን፤ ሄኖክ በሪሁን እና ሌሎችም ታዋቂና ወጣት አርቲስቶች ተሳትፈዋል፡፡

ከከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

Tik Tok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY