Summary Report

Bahir Dar University, Research & Community Service V/President Office, Community Service Directorate 2007 E.C Activities

Introduction

This report is organized into four parts.

Part 1: contains community service activity reports of academic units,

part 2: BDU project cites,

part 3: research centers and

part 4: different partnership projects of the University in and out of Bahir Dar City.

In part 1, seven academic units such as College of Agriculture and Environmental Sciences (CoAESc), College of Business and Economics (CoBE), College of Medicine and Health Sciences (CoMHSc), College of Science, Faculty of Social Sciences, Faculty of Education and Behavioral Sciences and Faculty of Humanities have carried out various community service activities in the fiscal year. Through academic units, a total of 39 community service activities have been performed in the year 2007. Among these, 7 were performed by College of Agriculture and Environmental Sciences, 3 by College of Business and Economics (CoBE), 5 by College of Medicine and Health Sciences (CoMHSc), 5 by College of Science, 8 by Faculty of Social Sciences, 7 by Faculty of Education and Behavioral Sciences and 4 by Faculty of Humanities.

In part 2, Bahir Dar University has two rural and one urban project cities namely Birr-Adama Integrated Watershed Development Project, Kolela Solar Village and Integrated Development Project and Bahir Dar City Project. In the year 2007, these project cities performed a total of 14 community service activities. Among these, 5 were performed under Birr-Adama Integrated Watershed Development Project, 6 under Kolela Solar Village and Integrated Development and 3 by Bahir Dar City Project.

In part 3, Although BDU has more than 9 research centers, all research centers were not engaged in community service activities in the year 2007. Among the research centers, Biotechnology Research Center, Blue Nile Water Institute (BNWI), Geospatial Data Technology Center (GDTC) and Institute of Pedagogical and Educational Research (IPER) were engaged in various community service activities. Biotechnology performed 7 community service activities, IPER 3, Blue Nile 2 and 1 by GDTC.

In part 4, BDU is also working in collaboration with many organizations working in Bahir Dar City and out of Bahir Dar City. These partnership projects include Green Environment for All Development Association, SOS, Retired Civil Servants Association and Biodiversity. Activity reports from these partnership projects are described in the last part of this report document.

Detail of the report is attached at the bottom of this page

መግቢያ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ከሚገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት/ዩኒቭርሲቲዎች ዉስጥ አንዱና አንጋፋው መሆኑ ይታዎቃል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ- ዕውቀትን መጠበቅና ማስተላለፍ (መማር ማስተማር)፣ ዕውቀት በማዳበር (ምርምር) ብሎም በማህብርስብ አገልግሎት ግንባር ቀደም በመሆንና ለአገሪቱ እድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ ታላቅ እንቅስቃሴ እያደረገ ይግኛል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ ማህብርስብ አገልግሎት ዋና ዐላማ፡ - በምርምርና እዉቀት እንዲሁም በማህበረሰቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ፤ ጉደለት የሚታይባቸውን መርጦና ቅደም ተከተል አውጥቶ፣የትኩረት አቅጣጫ በመለየት ባልተበታተና ዘላቂነት ባለዉ ሁኔታ የስልጠና፣ የማማከርና ድጋፍ አገልግሎት መስጠት እና ማኅበረሰቡ ቴክኖሎጂዎችን ከተገቢው ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ጋር እንዲጨብጥ በማድረግ ተፈጥሮን በመጠበቅ ምረታማነትን በማሳደግ በዘለቄታነት ህይወቱን እንዲቀይር ማብቃት ሲሆን፡-

በአጠቀለይ ማህበረሰቡን

ስለ ተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና አያያዝ፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ወዘተ ግንዛቤ አንዲጨበጥ ማድረግ
እነዚህን ስራዎች በተቀነጀ መልኩ ሰርቶና ተለማምዶ በዘለቄታ እራሱ ተረክቦ የሚያሰኬድበትን ሁኔታ መፈጠር
ተስማሚ ቴክኖሎጅዎችን አንዲያገኝ በማድረግ፣ ሰልጥኖ ኑሮዉ አንዲሻሻል ማገዝ
በተለይ ህጻናት፣ ሴቶች ወጣቶች እና የተቁአማትን አቅም በማሳደግ አራሳቸዉን ችለዉ ለአካባቢያቸዉም እድገት አስተወጽኦ አንዲኖራቸዉ ማስቻል ነዉ
የ 2007 የማህበረሰብ አገልግሎት እንቅስቃሴ በዋናነት ዩኒቨርሲቲው ከ2003 እስከ 2007 እነዲፈጸም ባዘጋጀዉ ሰትራቴጂካዊ እቅድ ላይ ባሰፈረዉ ተልዕኮ፣ግብ እና አላማ አንጻር የተቃኘ ሲሆን በየአካዳሚክ ዩኒቶችና ምርምር ማአከላት ባሏቸው የማህበረሰብ አገልግሎት የትኩረት አቅጣጫዎች፤ በ2006 የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አሰጣጥ የግምገማ ጥናት ሪፖርት እና ጳጉሜ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው ማህበረሰብ አገልግሎት ቀን የዩኒቨርሰቲዉ ማህበረሰብ ከአጋር አካለት ጋር በነበረዉ ምክክር የተሰጡ ሀሳቦችን እነደግብአት በመጠቀም የተጠናቀረ ሪፖርት ነዉ፡፡ ሁሉም ስራዎች በየአካዳሚክ ዩኒቶችና ምርምር ማአከላት ባሏቸው የማህበረሰብ አገልግሎት የትኩረት አቅጣጫዎች የተነደፉ ናቸው፡፡

ስለሆነም የ2007 የማህበረሰብ አገልግሎት በሚከተሉት አግባብ ቀርቧል

የዩኒቨርስቲዉ የማህበረሰብ አገልግሎት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ከመሆኑ አንጻር ስርአት ተዘርግቶ እየተሰራ ስለመሆኑ
በዩኒቨርስቲዉ የማህበረሰብ አገልግሎት የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየደረገ ስለመሆኑ
የምርምር ዉጤቶች እነዲሰርጹና የአካባቢዉ ህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ እነዲሻሻል የተከናወኑ ስራዎች
ለአካባቢዉ ህብረተሰብ የማማከር አገልግሎት እነዲሰጥ የተደረገ ጥረት
በየንቨርሰቲዉ አካባቢ ለሚገኙ ት/ቤቶች በልዩ ልዩ አግባብ የተደረጉ ጥረቶችና የተገኙ ዉጤቶች
1ኛ) የዩኒቨርስቲዉ የማህበረሰብ አገልግሎት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ከመሆኑ አንጻር ስርአት ተዘርግቶ እየተሰራ ስለመሆኑ

ከ2003 እስከ 2007 ድረስ ዩኒቨርሲቲው ፡-

3 የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን በከተማ እና በገጠር በመመስረት አገልግሎቱን መስጠት ከሚለዉ ግብ
በባህር ዳር ከተማ፣
ሜጫ ቆለላ ሞዴል የገጠር መንደርና
ብር አዳማ ተፋሰስ ልማት የተሰኙትን አቋቁሟል
በክልል ደረጃ አገልግሎት ማስፋት ከሚለዉ ግብ
ከላይ የተገለጹትን 2 የገጠር አገልግሎት መስጫዎችን (ቆለላ እና ብር አዳማ፡ ም/ጎጃም) ጨምሮ፣ ከአጋሮቻችን፡ -ም/ጎጃም/ት/ጽ/ቤት እና አዊ ት/ጽ/ቤት ፣ ም/ጎጃም/ህ/ስ/ማ/፣ደ/ጎንደር ፣ ዋግ ህምራ፣ ደ/ወሎና አርጎባ ብሄረሰብ ፣ የተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ፣ ከ1 ሚሊዮን በላይ አባላት ካሉት ከአማራ ክልል ሴቶች ፌድሬሽን ፣ የተለያዩ የሙያና በጎ ፈቃድ ማህበራት፣ ወዘተ ጋር በመሆን የማህበረሰቡን ፍላጎት ባካተተ መልኩ የስልጠና፣ የማማከርና ድጋፍ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዉ በባህር ዳር ከተማ፣ 2ቱ የገጠር አካባቢዎች (ሜጫ ቆለላ ሞዴል የገጠር መንደርና ብር አዳማ ተፋሰስ ልማት) ፣ በክልል ደረጃ ብሎ በመለየት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ መሆኑንና ስርአት ዘርግቶ እየሰራ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነዉ፡፡

በዩኒቨርስቲዉ የማህበረሰብ አገልግሎት የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየደረገ ስለመሆኑ
ከዚህ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም በተለያዩ አካዳሚክ ክፍሎች የሚቀረጹ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን ተገቢነት ለማየት የሚያግዙ የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት የትኩረት መስኮች በየአካዳሚክ ዩኒቶችና ምርምርተቋማት የተዘጋጁ ሲሆን በማእከል የሚገመገምበት ስርአት (Review system) አለ፡፡ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠዉን የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን በጋራ ገምግሞ ማጽደቁና አነዚህ አጋር አካላት ቅድሚያ ለሰጧቸዉ/አንገበጋቢ ለሚሏቸዉ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀሱ፣አገልግሎቱን ተቀባይነት እነዲኖረዉና ለዉጥ ማምጣት እነደሚቻል አመላካች ነዉ፡፡ ለዚህ አንዱ ማስረጃ በዚህ አመት የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ከ10 በላይ ከሚሆኑ አጋር አካላት ጋር በትብብር/መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም የተፈጸሙ ተግባራት ናቸዉ (ሰንጠረዥ )፡፡ የሚሰጡት የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ምን መልክ መያዝ እንዳለባቸው፣ ከምክትል ፕሬዚዳንት ጀምሮ እስከተለያዩ ኮሌጆች፣ ፋኩልቲዎች ወዘተ ያሉትን የመዋቅር ጉዳዮችን ጨምሮ ስራዎች እንዴት መመራት እንዳለባቸው፣ አገልግሎቶችን የሚሰጡት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች ስራቸውን ከሌሎች የምርምርና ማስተማር ጫናዎች ጋር በምን መንገድ ማስኬድ እንዳለባቸውና በማህበረሰብ አገልግሎትስ ሲሳተፉ ምን ወጪዎች በምን ሁኔታ ሊሸፈንላቸው እንደሚገባ የሚያሳይ አንድ ወጥ የሆነ የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ፖሊሲ (guidelines) ተጠናቆ ቀርቧል፡፡ መመሪያዉ በተለያዩ ግለሰቦች፣ በቡድንና ጽ/ቤቱ በመረጣቸዉ ገምጋሚ ኮሚቴ ሃሳብ የተሰጠበትና የዳበረ ነዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በየአመቱ የማህበረሰብ አገልግሎት ለሰጡ ግለሰቦች የማበረታቻ ትምህርታዊ ጉዞና የምስክር ወረቀት በመስጠት እዉቅና መሰጠቱ እነዲሁም መረጃ ለመያዝ የሚያስችል መመዘኛና ልዩ ልዩ ቅጾች ተዘጋጅተዉ ስራ ላይ መዋላቸዉ የአገልግሎቱን አፈጻጸም የተቀላጠፈ አድርጎታል፡፡ በአጠቀላይ የአስራር ስርዓት ለመዘርጋት መመሪያዎችና አሰራሮች ዝግጅት ላይ

የማህበረሰብ አገልግሎት መመሪያ በተለያዩ ግለሰቦችና በቡድን ሃሳብ ተሰጥቶበት በአሁኑ ሰአት ለመጽደቅ በዝግጂት ላይ ይገኛል፡፡
በ2005 (ሰሜን ተራራ) እና 2006 (የሰሜን የሀገራችን ክፍልና 5 ዩነቨርስቲወችን) የማህበረሰብ አገልግሎት ለሰጡ የዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ አባላት የማበረታቻ ትምህርታዊ ጉዞ የተዘጋጀ ሲሆን የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል
መመሪያዉ እስከሚጸድቅ ለነጻ አገልጋዮች እውቅና ወይም ማበረታቻ የሚያሰጥ እንዲሁም መረጃ ለመያዝ የሚያስችል መመዘኛና ልዩ ልዩ ቅጾች ተዘጋጅተዋል/ስራ ላይ ዉለዋል፡፡ በዚህ መሰረት ወጥ የሆን የ2006 ሪፖርት ቀርቧል/ታትሟል/ዶክመንታሪም ተዘጋጅተዋል፣ ፡፡ የ2007 ደግሞ በተሻለ መልኩ ለማቅረብ ዝግጅቱ አልቋል፡፡
የተለያዩ ሙያ ያላቸውን ሰዎች በቡድን በማደራጀት ከአጋር አካላት ጋር በማጣመር ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲሰማሩ ተደርጓል፡፡
ከአጋር አካላት ጋር የውል ስምምነት በመፈጸም እያንዳንዱ ወገን የድርሻውን እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ይህን ብዛት ያለውን የመምህራንና የተማሪዎች ሃይል (አቅም) ከመጠቀም አኳያና አገልግሎቱ በነፃ ከመሆኑ አንፃር በተለያዩ ምክንያቶች ያለአግባብ ክፍያን የመጠበቅ ሁኔታን ከማስቀርት አንጻር የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል፤
በኮሌጆች/ ፋካልቲዎች/ ት/ቤቶች ካሉት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪዎች በተጨማሪ መልካም ፍላጎትና ቀና አመለካከት ያለቸዉን ሰዎች በየፋካሊቲው እነዲተባበሩ በማድረግ ያለምንም ክፍያ (በአስተባባሪ በመመደብ)፣ በአጠቃላይ ስራን ለሰሪዉና ለተባባሪዉ በማከፋፈል ለመስራት ጥረት ተደርጓል፡፡ ለወደፊቱ ግን በመዋቅር የሚፈታዉን በማህበረሰብ አገልግሎት መመሪያ ላይ እነዲካተት ሁኗል
የምርምር ዉጤቶች እነዲሰርጹና የአካባቢዉ ህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ እነዲሻሻል የተከናወኑ ስራዎች
በአለፈዉ አመት 2 ብቻ (በባዮ ቴክኖሎጂ) የመርምር ስርጸት የነበረዉ በ2007 17 ታቅደዉ እስካሁን በለን ሪፖርት 12 መፈጸማቸዉ የሚየበረታታ ነዉ፡፡ ዩኒቨርስቲዉ ካለዉ ራእይና በየአመቱ ከሚታተሙት ብዛት ካላቸዉ ወረቀቶች አንጻር በዚህ ዙሪያ ብዙ አገልግሎቶቻች የምጠበቁ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን የዩኒቨርሰቱዉ ማህበረሰብ አገልግሎት ከምርምር ከተገኙት በተጨማሪ በእዉቀት ላይ ተመስርቶ አገልግሎቶችን/የግብ ተግባራትን በገጠር፣ በከተማ፣ በክልልና ምርምር ዉጤቶች ማስረጽና ግንዛቤ ማስጨበጥ ብሎ በመለየት ከላይ እነደተገለጸዉ በትምህርት፤ ጤና፤ በባህልና ቱሪዝም፤ በህጻናት፣ ወጣቶችና ሴቶች አገልግሎቶች፤ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፤ በኑሮ ማሻሻያ፤ በማህበረሰብ ማነቃቃት፤ መልካም አሰተዳደር/ደንበኛ አገልግሎት እና በመሰል ስራዎች በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፡ (ሰንጠረዥ )

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ የሆነ የዕውቀት፣ የአመለካከትና የክህሎት ማሳደግ ስራ በመስራት (ሰንጠረዥ 1 ግንዛቤ ፈጠራ)
የምርምር ውጤቶችን በማስፋፋትና በማስተዋወቅ የማላመድ ስራ ለመስራት (ሰንጠረዥ በማህበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊዎች የተዘጋጁ ማንዋሎችና ብሮሸሮች)
የህብረተሰቡ ኑሮ የሚሻሻልበትን ሁኔታ በመፍጠር አስተዋጽኦ ከማድረግ አኳያ
የመማር ማስተማሩን ስራ ከአዉነተኛዉ አለም ጋር እነዲገናኝ ምሁራን ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ የመስራት ባህልን በማዳበር የዩኒቨርስቲውን ራዕይ ለማሳካት ጥረት አድርጓል
ለምሳሌ በኑሮ ማሻሻያ - ባለፈዉ አመት ተሰርተዉ እነዲቀጥሉ በተመረጡ ዘርፎች በተለይ በወተት ምርት ማሻሻል (አስከ ግማሽ ሊትር መርታማነት መጨመር) ፣ በማር ምርት ስራ (በአማካኝ ከ10 ኪ.ግ በላይ ከባህላዊዉ መጨመር) ፣ ዶሮ ርባታ የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም ከመገንባት አንጻር የተሰራዉ፤ የአካባቢዉ ህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ እነዲሻሻል የማህበረሰብ አገልግሎት ከሰራዉ የሚጠቀሱ ናቸዉ

ለአካባቢዉ ህብረተሰብ የማማከር አገልግሎት እነዲሰጥ የተደረገ ጥረት
በአመቱ በርካታ የግንዛቤ መስጨበጫ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን (ሰንጠረዥ ) ከበርካታ አጋር ድርጅቶች ጋር (ሰንጠረዥ ) የትብብር ስምምነት በማድረግ ዘርፈ ብዙ እነቅስቃሴ ለማድረግ ተችሏል፡፡ከብዙ በጥቂቱ

ያለፈዉን አመት ስራ የገመገመ፣ የ2007 አቀድን ያየበትና ለንቁ ተሳታፊዎች እዉቅና የተሰጠበት መድረክ ተዘጋጅቶአል
ለ2007 ማህበረሰብ አገልግሎት በቀረቡ ምክረሃሳብ ላይ ዉይይት ተካሂዷል
በተሰጡ አገልግሎቶች የኣጋር ኣካላት ደንበኞች እርካታ በዚህ መድረክ ከመገለጹ በተጨማሪ፣ ከአ/ብ/ክ/መ/ ባህል ቱሪዝም እና ፓርኮች ልማት ቢሮ፣ ከ SOS CHILDREN VILLAGES ETHIOPIA, BAHIR DAR BRANCH፣ ከአ/ብ/ክ/መ/ የህ/ስ/ማ/ኤ/ም/ጎ/ዞ/ጽ/ቤት፣ ባህር ዳር የመንግስት ጡረተኞች ማህበር ወዘተ በደብዳቤ ተገልጾአል
የ waste management day የተለዩ ጽሁፎች ቀርበዉ ተከበሯል፡፡ በዚሁ መድረክ በጣና ሀይቅና አካባቢዉ በተከሰተዉ የእነቦጭ አረም የማጥፋትና መከላከል ዘመቻ ጽኁፍ ቀረቦ የግነዛቤ ማሰጨበጥ ስራ ከመካሄዱ በተጨማሪ፣ በዚሁ አረም ዙሪያ በተዘጋጀዉ አገራዊ አዉደ ጥናት ተሳትፎ ከማደረጉም በተጨማሪ ለዚሁ ስራ መስፈጸሚያ 4 ሚሊዮን ብር ከማህበረሰብ አገልግሎት በጀት አስተዎጽኦ አድርጓል
ከፍተኛ አዉቅና ባገኘዉ የደንገል ፕሮጄክት አማከኝነት አድማሱን በማስፋት፣ የእነቦጭ አረምን ለመከላከልና ከደለል ለመከላከል በጣና ሀይቅ ዙሪያ፣ በቆሻሻ መፋሰሻ ቦዮች፣ በከተማዉ ዋና ዋና ቦተወች (በተለይ በላይ ዘለቀ ክ/ከተማ) ደንገልን በማስፋፋት በመከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ስራዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የቆጋ ግድብን ከደለል ለመከላከል እንዲሁ ደንገል ለመትከል ከሚመለከታቸዉ ወገኖችና ከማህበረሰቡ ጋር ተመካክረን ስራዉ በጥሩ ሁኔታ ከሜዱ በተጨማ በአቅዳችን መሰረት በተፈላጊ ቦተዎች የአመቱ የተከላ ስራ ተጠናቋል፡፡
ዩኒቨርሲተዉ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በም/ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ደብረታቦር (አገልግሎት የሚሰጥበት መስክ በዪኒቨርስቲዉ የትምህርት ክፍል ባለመኖሩ ምሳሌ ፔዳጎጂ፣ አማርኛ) እና በሌሎች ወረዳወች፤ በመደበኛ ትምህርት፣ በጎልማሶች፣ በመጤ አረም፣ በትምህርትና በመሳሰሉት አገልግሎት እየተሰጠ ነዉ
በጤና ዙሪያም ከንጹህ ዉሃ አቅርቦት ጀምሮ እስከ አካባቢ ጽዳት ትኩረት ተሰጥቶና ለጤና ባለመያዎች ስልጠና በመስጠት፤ በኅይል አቅርቦት (የደን ጭፍጨፋ ለመቀነስ ሀይል ቆጣቢ ምድጃዎና ሶላር አገልግሎት በመስጠት)፤በግብርናና ኑሮ ማሻሻያ ረገድም ቢሆን በርካታ ስራዎች በከተማም በገጠርም ተሰርተዋል፡፡
በአማራ ክልል ደረጃ ከተመረጡ ሴክተሮች ጋር በመሆን አገልግሎትን ማስፋፋት (ሰፖርተ ኮሚሽን፣ በሴቶች ፌድሬሽን፣ ወዘተ)ና አብሮ የመስራት ስራ ተሰርቶአል (ሰንጠረዥ )
አንድ ክልል አቀፍ የሆነ የምከክር መድረክ (Establishing a Model Ecotourism & Biodiversity Conservation Center in Amhara Region) ከ Society for Ecotourism & Biodiversity Conservation ከሚባል ማሀበር ጋር አዘጋጂተናል
በ3 አካባዎች በባህር ዳር (ድባንቄ)፣ ቆለላ እና ብር አዳማ የአገር በቀል ዘፎችና የመድሃኒት አጽዋቶች ችግኝ ጠቢያ ተቋቁመዉ ከተለያዩ ቦተዎች የተሰበሰቡት እጽዋቶች አየተተከሉ ነዉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በSTEM center ዘመናዊ የከተማ የጓሮ አትክልት አያያዝና የጠብታ መስኖ አጠቃቀም ስረቶ ማሳያ በተማሪዎች በራሳቸዉ መንገድ በባለሙያ እየተመሩ ያዘገጁት ስራም ለብዙዎች በትምህርት ሰጭነቱ ምስጋና የተቸረዉ ነዉ
በቁጥር 16 የሚሆኑ ማኑዋሎች እና የ2006 ሪፖረት ለተጠቃሚዉ እንዲደርሱ ተዘጋጅተዋል
በ ISSD (ምርጥ ዘር ብዜት) ና CASCAPE (ምርጥ የግብርና ተሞክሮወች ለአርሶ አደሩ ማለማመድ) ስራ በገበሬዎች ቀን የተሳተፍን ሲሆን፣ ከተወካዮች ም/ቤት ለመጡ ልኡካን የቆለላን ሶላር መንደርና የ ISSD የስራ እንቅስቃሴ አስጎብኝተናል
ከ5 የኒቨርሰቲዎች ጋር የልምድ ልዉዉጥ አድርገን የማህበረሰብ አገልግሎት መመሪያ የተዘጋጀ ሲሆን የተገነኘዉን ልምድ ለዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ በማካፈል ለአሰራራችን ግባት ይሆን ዘንድ ሐሳብ አቅርበናል
በየንቨርሰቲዉ አካባቢ ለሚገኙ ት/ቤቶች (በተለይ ለ2ኛ ደ/ት/ቤቶች) በልዩ ልዩ አግባብ የተደረጉ ጥረቶችና የተገኙ ዉጤቶች
በተለይ በትምህርት ዙሪያ ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም መሰናዶ ት/ቤቶች የቤተ-ሙከራዎች፣ ሂሳብ፣ ሳይንስ፣ እንግሊዝኛ ቋንቋ ልዩ ፍላጎት ላላቸዉ ተማሪዎችን ለሚየሰተምሩ መምህራን ጭምር ስልጠናዎች ተለይተው የተሰጡ ሲሆን ከከተማው ና ገጠር ትምህርት ጽ/ቤቶች ጋር በመቀናጀትበርካታ ስራ ተሰርቷል።

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ፣ ኤስኦኤስ የህጻናት መንደር ባህር-ዳርፕሮግራም እና ባህር ዳር ከተማአስተዳደር፣ ህዳር11 ክፍለ ከተማ የማህበረሰብ ድጋፍ እናእንክብካቤጥምረት 1000 ለሚሆኑ የወላጆቻቸውን ድጋፍ ያጡና ለማጣት በቋፍ ላይ የሚገኙ ህጻናትና በቁጥር 844 ለሆኑ ወላጆቻቸዉ/አሳዳጊዎቻቸዉ ዘላቂ የሆነ ማህበረሰብ ተኮር ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ የማህበረሰቡን አቅም ማጎልበት እናየወላጆቻቸውን አቅም ለማጠናከር የባ/ዳር ዩንቨርሲቲ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ የሚሰረዉ ስራ
በባኅር ዳር ከተማ ለሚገኙ 33 የመንግስት ት/ቤቶች የ1ኛ ክፍል መምህራንን ተማሪዎች በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ ማንበብ፣ መጻፍና ማስላት እነዲቸሉ/እንዲያበቁ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ በመሰጠቱ የባህር ዳር ከተማ ት/ቤቶች ጽ/ቤት እንዳረጋገጠዉ በሁሉም ት/ቤቶች ከገጠር ቀበሌ ካሉት ወጭ በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ ማንበብ፣ መጻፍና ማስላት መቻላቸዉን መስክሯል (100% of grade one students in Bahir Dar city (excluding those in rural kebeles) were able to read, write and calculate within the time frame i.e. before Tahsas 30, 2007 E.C.) ከዚህ በተጨማሪ ፋካልቲዉ ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶቹ ጋር ያለዉን ግነኙነት ያጠናከረበትና ከመሰረቱ የትምህርት ጥራትን ለመጠበቅ ዩኒቨርሲቲዉ የሚኖረዉን ድረሻ/ሃላፊነት ለመወጣት መሰረት የጣለበትም ጭምር ነዉ፡፡
የኬሚሰትሪ ትምህርት በአካባቢ ቁሳቁስ የተግባር ትምህርት እንዴት እንደሚሰጥና በመርጃ መጻህፍት (7 – 8) ላይ ስላሉ ደካማና ጠንካራ ጎኖች ለወላጆች፣ ለ5 ት/ቤቶች መምህራንና ለትምህርት ባለሙያዎች በየኒቨርሲቲዉ መምህራን በቀረበ ዝግጂት በተለይ ከትም/ጽ/ቤት የተወከሉት በሌሎች ትምህርቶችም ጭምር ተጠናክሮ እነዲቀጥል ሃሳብ ተሰጥቶ ለሚቀጥለዉ አመት ለማስፋት ስምምነት ላይ ተደርሧል፡፡
በአዊ መስተዳድር ዞን (በህዳሴ 2ኛ ደ/ት/ቤትና አገዉ ምድር የመሰናዶና 2ኛ ደ/ት/ቤት) በም/ጎጃም መ/ዞን (መራዊ 2ኛ ደ/ት/ቤት) to improve the knowledge, attitude and skill of conducting problem solving, collaborative and participatory action research of secondary school teachers and principals በሚል ግብ ለ415 መምህራንና ሃላፊዎች የተሰጠዉ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በስልጠናዉ መርካታቸዉን በሰጡት ግብረመልስና የምስጋና ስረቲፊኬት ለማወቅ ተችሏል፡፡
የ2ኛ ደ/ት/በቶች ሴት ተማሪዎች ጤናማ የትምህርት አካባቢ መፍጠር (ስለ አላስፈላጊ እርግዝና እና ዉረጃ ወዘተ)