ለመደበኛ መርሃ ግብር ድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ እና መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ለአዲስ አመልካቾች ከተዘጋጀው ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/graduatapp/ የማመልከቻ ቅጹን በማውረድ (Download) በማድረግና በመሙላት ከላይ በተገለፀው ድረ ገጽ online ወይም በአካል ትምህርቱ ወደሚሰጥበት የአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር በመገኘት ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡