አለማቀፋዊ ተሳትፎ እድሎችና ፈተናዎችን የተመለከተ ሕዝበ ገለፃ ተካሄደ

የዩኒቨርሲቲዎች አለማቀፋዊ ተሳትፎ እድሎችና ፈተናዎችን የተመለከተ ሕዝበ ገለፃ ተካሄደ

(ታህሳስ 06/2015 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) በኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ የአለማቀፍ ልማት ቢሮ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ተሾመ ይዘንጋዉ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ አዳራሽ በመገኘት የዩኒቨርሲቲዎች አለማቀፋዊ ተሳትፎ እድሎችና ፈተናዎች (University Global Engagement Opportunities and Challenges) በሚል ርእሰ ጉዳይ በገፅ ለገፅና በይነ መረብ ህዝበ ገለፃ (Public Lecture) አቀረቡ፡፡

ለህዝበ ገለፃዉ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመገኘታቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉን በመግለፅ ሃሳባቸዉን ያቀረቡት ዶ/ር ተሾመ ኢትዮጵያውያን በብዙ ቦታዎች እንደሚታየዉ ሃሳባችንን የመግለፅ ችግር አለብን፤ ስንቀመጥ እንኳን ጥግ ይዘን ነዉ፤ ይህም ደግሞ አለማቀፋዊ ግንኙነታችንን ዝቅ አድርጎታል ብለዋል፡፡ ለዚህም ዋናዉ ምክንያት መንግስታዊ የአስተዳደር ስርዓታችን፤ የትምህርት ስርዓታችን እና ባህሎቻችን ጉልህ አስተዋፆ አላቸው ብለዋል፡፡

ለአለማቀፋዊ ተሳትፎ ፈተናዎች በርካታ መሆናቸዉን ያወሱት ዶ/ር ተሾመ ግልፅ የሆነ ስልት አለመኖር፣ የአለማቀፋዊ ትስስር መላላት፣ የሀብት ዉስንነት፣ የአመራር ድክመትና የትብብር ባህል አናሳ መሆን ጥቂቶቹ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

በሕዝባዊ ገለፃዉ ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬዉ ተገኘ እንደገለጹት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአለማቀፍ ተሳትፎና ግነኙነት ያለዉን ጠቀሜታ ቀድሞ በመረዳቱ በምክትል ፕሬዚዳንት ደረጃ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤትን በማቋቋም እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፍሬው አክለዉም ዩኒቨርሲቲው ከበርካታ አለማቀፍ ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማት ጋር በከፍተኛ ትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

`ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ``

``Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY