የእርስዎን ልዩነት ፈጣሪ ይምረጡ፣ያሸልሙ!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከምስረታው ጀምሮ በየዘርፉ ለዕድገቱ ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ላደረጉ እና በማድረግ ላይ ለሚገኙ አካላት ዕውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምስረታ በአሉን በተለያዩ ዝግጅቶች በ2015 ዓ/ም እያከበረ ይገኛል፡፡ ለዚህም እንዲረዳው በየዘርፉ ስራውን የሚያስኬዱ ኮሚቴዎች አቋቁሞ ሥራውን እያሳለጠ ነው፡፡ ከእነዚህ ኮሚቴዎች አንዱ የእውቅናና ሽልማት ኮሚቴ ነው፡፡  የኮሚቴው ተግባር ለዩኒቨርስቲው ከምስረታው (ከፔዳጎጂ አካዳሚ እና የፖሊ ቴክኒክ ኢኒስቲትዩት) ጀምሮ በየዘርፉ ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ያደረጉትን አካላት ለይቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ነው፡፡ ይህን አላማ ከግብ ለማድረስ እንዲረዳው መረጃ ይኖራቸዋል ተብለው ከሚገመቱ የዩኒቨርስቲው የቀድሞና የአሁን ሰራተኞች፣ምሩቃን (አሉሚናይ) ተቋማት እና አጋር ድርጅቶች መረጃ መሰብሰብ ነው፡፡ ይህን ማሳካት እንዲቻል የሚከተለው የመጠይቅ ቅጽ ተዘጋጅቷል፡፡

 

ስለዚህ እርስዎ በየዘመኑ በዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ እና በአስተደደር ዘርፍ መሰረት የጣሉ እና ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ልዩና ላቅ ያለ አስተዋጽዎ ያደረጉ በዩኒቨርሲቲው በስራ ላይ ያሉ፣ከዩኒቨርሲቲው ውጪ የሚኖሩ፣በህይወት ያሉም ሆነ የሌሉ፣ በሰለጠኑበት መስክ ለዩኒቨርስቲው ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ የሆነ አበርክቶ ያላቸውና በአስተዋጽኦቸው የዩኒቨርስቲውን ስም ያስጠሩ የዩኒቨርስቲው ምሩቃን/ አልሙናይ/፣ ለዩኒቨርስቲው እድገት ልዩ እና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የሥራ አጋሮች/ፓርትነርስ/፣በሥነጥበብና በስፖርት ልዩ አበርክቶ ያላቸው ግለሰቦችም ሆነ ተቋማትን አወዳድሮ በየደረጃው እውቅና መስጠት እንዲቻል ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሟላ መረጃ በታማኝነት በመስጠት እንዲተባበሩ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ለትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡ መጠይቁን ይህንን ሊንክ በመንካት ማግኘት ይችላሉ (https://docs.google.com/forms/d/1GPfvhnYFlXJ0ZG0ZvvKloPOshAm0E5ZOfIfAgYB...)፡፡

ማሳሰቢያ፡ ይህንን መጠይቅ በጥራት እና በተሻለ ሁኔታ ለመሙላት ጉግል ክሮም (Google Chrome) እንዲጠቀሙ እንጠይቃለን፡፡

Tuesday, April 18, 2023 - 01