image

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን

Campus Name

16 Mar, 2026

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንበዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ “Give to Gain” በሚል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ “50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ "ጥበብ" የመሰብሰቢያ አዳራሽ በልዩ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከአብክመ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ነቢያ መሀመድ እና የሴቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዘዳንት ጦይባ ሀሰንን እንዲሁም የባህር ዳር ከተማ ም/ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪና ምሁራን፣ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም የሴቶችን የታሪክ ተጋድሎና ጥንካሬ አውስተዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም

በዓሉ የሴቶችን ተጋድሎ የምናስታውስበት ብቻ ሳይሆን፣ ላለፉት 50 ዓመታት የሴቶች ድምፅ ለሀገራዊ ለውጥና ለታሪክ መታደስ ያበረከተውን አስተዋጽኦ የምናከብርበት ነው ብለዋል።

በተለይም በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሠለጠኑትና የተመረቁት 27 ሴት መርከበኞች የሴቶችን ብቃትና አቅም በተግባር ያሳዩ የዘመኑ የጥንካሬ ተምሳሌቶች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ "ሴት ስትሠራ ሀገር ትሠራለች፤ የሴቶች ውጤታማነት የሀገር ውጤታማነት ነው" ሲሉ የሴቶችን ሚና አጉልተዋል።

imageimageimage