የስራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል በ2010 ዓ.ም ለሚመረቁ ተማሪዎች የኢንትረፕርነርሽፕ ስልጠና ተሰጠ

የስራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል(Entrepreneurship Development and incubation Center, EDIC) በ2010 ዓ.ም ለሚመረቁ ተማሪዎች የኢንትረፕርነርሽፕ ስልጠና ከኢዲሲ ኢትዮጵያ(EDC,Ethiopia) ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ፡፡

ማዕከሉ በሶስት የስልጠና አዳራሾች ማለትም በዋናው ግቢ፤በባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንቲቱትና በሰላም ካምፓስ ለ1094(ለአንድ ሺህ ዘጠና አራት) ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 3 እና 4/2010 ዓ.ም የሁለት ቀን ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፡ አንድ ተማሪ ተመርቆ ስራ ከመፈለግ ይልቅ በራሱ ስራ መፍጠር እንዲችል የሚያነቃቃ ነበር፡፡

ማስታወቂያ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንተርኘርነርሽኘ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል በተመረጡ የአይሲቲ (ICT) ዘርፎች የቢዝነስ ኃሳብ እና ፍላጎት ያላቸውን 10 አመልካቾች ሙሉ ግብዓት ባሟላ ቤተ ሙከራ (Incubation Center) ለ1 ዓመት ኃሳባቸውን በማበልፀግ ወደ ንግድ ድርጅት ለማሸጋገር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፍላጐት ያላችሁ እና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ እንድታመለክቱና የእድሉ ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡

ሀ. የመመዝገቢያመስፈርት

1. በቴክኒክና ሙያ ቢያንስ በደረጃ 3 በICT ዘርፍ የተመረቀ/ቀች እና ከዚያ በላይ

2 አመልካቹ በዘርፉ ሊሠራ ያሠበውን/ችውን የቢዝነስ እቅድ ማጠቃለያ /business plan executive summary/ማቅረብ የሚችል/ምትችል

News on Incubation

The center has performed different activities associated with incubation. Two main activities have been on the way as part of this endeavor.

Subscribe to Entrepreneurship Development and Incubation Center RSS