የቢዝነስ ፈጠራ ኃሳብ ውድድር ተካሄደ

አለም አቀፍ የኢንትረፕርነርሽፕ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ የተሻለ የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን ተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ የፈጠራ ኃሳብ ውድድር ተካሄደ፡፡
በወጣው ማስታዎቂያ መሰረት 48 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች በተማሪዎች ለማዕከሉ የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የተሻሉ የተባሉ 11 ፕሮጀክቶች ለውድድር ቀርበው ሕዳር 6/2010 ዓ.ም በዘርፉ ባለሙያ በሆኑ ዳኞች ከተገመገሙ በኋላ ሶስቱ ለድጋፍ ተመርጠዋል፡፡የተመረጡትም፡-
1. Smart Assistant Stick for visually impaired persons by; Yinebe Tamiru
2. Production of Building and Construction Materials from Waste Plastics by; Ayalew Emiru
3. Fixed Water Sprinkler irrigation System by; Ayalachew Dessie,Baye Mekonnen and Bereket Assefa

እየታጠበ በተደጋጋሚ መጠቀም የሚቻልበት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ(Reusable sanitary Pads) አዘገጃጀት ላይ ስልጠና ተሰጠ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከዩኒሴፍ አማራ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ባሉ 4 ወረዳዎች ባለፈው ዓመት 80 ለሚሆኑ ሰዎች ታጥቦ በድጋሚ መጠቀም የሚቻልበት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ(ሞዴስ) አዘገጃጀትና አጠቃቀም ላይ ስልጠና የሰጠ መሆኑ ይታወሳል፡፡
አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ከጥቅምት 22-25/2010 ዓ.ም ከአራቱ ወረዳዎች አንዱ በሆነው በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማ ለ20 ሰልጣኞች ስለ ፓዱ ሙያዊ አዘገጃጀት በጨርቃጨርቅ ባለሙያ፤ጤና ላይ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ በጤና ባለሙያና ፓዱን አምርተው እንዴት ትርፋማና ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ በቢዝነስ ባለሙያዎች በዩነቨርሲቲው የኢንትረፕርነርሽፕ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል አስተባባሪነት ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡

የስራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል በ2010 ዓ.ም ለሚመረቁ ተማሪዎች የኢንትረፕርነርሽፕ ስልጠና ተሰጠ

የስራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል(Entrepreneurship Development and incubation Center, EDIC) በ2010 ዓ.ም ለሚመረቁ ተማሪዎች የኢንትረፕርነርሽፕ ስልጠና ከኢዲሲ ኢትዮጵያ(EDC,Ethiopia) ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ፡፡

ማዕከሉ በሶስት የስልጠና አዳራሾች ማለትም በዋናው ግቢ፤በባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንቲቱትና በሰላም ካምፓስ ለ1094(ለአንድ ሺህ ዘጠና አራት) ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 3 እና 4/2010 ዓ.ም የሁለት ቀን ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፡ አንድ ተማሪ ተመርቆ ስራ ከመፈለግ ይልቅ በራሱ ስራ መፍጠር እንዲችል የሚያነቃቃ ነበር፡፡

Subscribe to Entrepreneurship Development and Incubation Center RSS