ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል የማህበረሰቡን ችግር ሊፈታ የሚያስችል የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን ተማሪዎች ለማበረታታትና ኃሳባቸው ወደ ተግባር እንዲለወጥ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
ስለሆነም የፈጠራ ኃሳብ ያላቸሁ ተማሪወች በግል ወይም በጋራ በመሆን ፕሮፖዛል አዘጋጅታችሁ የጥበብ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 407 ማምጣት ወይም ኢሜይል በማድረግ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ፕሮፖዛል ለማዘጋጀት የምትጠቀሙበትን ፎርማት በየግቢያችሁ ባሉ የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ወይም በማዕከሉ ዌብ ሳይት http://www.bdu.edu.et/edic/ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል