የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በመረጃ አያያዝና አደረጃጀት ዙሪያ ለሚለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

Campus Name

23 Jul, 2025

በመረጃ አያያዝና አደረጃጀት ዙሪያ ለሚለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በዩኤንዲፒ ( UNDP ) በጀት ድጋፍ የተፈናቃዮችን የመረጃ አያያዝና አደረጃጀትን አስመልክቶ በተዘጋጀ ሶፍትዌር ዙሪያ ከሚመለከታቸው የክልል እና የዞን ባለሙያዎች ጋር ወርክሾ እያካሄደ ነው፡፡የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሰርካዲስ አታሌ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለጹት በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም እና በቂ የሆነ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ከአሁን በፊት የተሟላ የመረጃ አያያዝ ባለመኖሩ ለስራ እንቅፋት መፍጠሩን አመላክተዋል፡፡በመሆኑም ይህንን ችግር ሊፈታ የሚችል እና ለውሳኔ ሰጪ አካላት ግልጽ የሆነ የተፈናቃይ መረጃን አደራጅቶ ለመያዝ ከባህር ዳር እና ደብረብርሀን ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር ኮሚሽናችን መረጃዎች ተሟልተው ወደ አንድ ቋት ለማምጣት የሚያስችል ሶፍቴዌርን በማበልፀግ ስራዎች ከሚተገብሩ አካላት ጋር ወደተግባር ለማስገባት በቅድመ ትግበራ የተዘጋጀ ወርክሾኘ ነው ብለዋል፡፡ ምክትል ኮሚሽነሯ አክለው እንደገለጹት በዚህ ወርክ ሾኘ ላይ የተገኛችሁ ባለሙያዎች የተሟላ የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን ለማዳበር የእናንተ ተሳትፎ ወሳኝ እና ሥራውንም የምታከናውኑት እናንተው ስለሆናችሁ ይህንን ወርክ ሾፕ በንቃት በመሳተፍና ወደተግባር ስራው መግባት ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡ ስልጠናውን የሚሰጡት ሶፍትወሩን ያበለጸጉት የባህር ዳር ዩኒቪርስቲ ባልደረባ አቶ ሃይለእየሱስ አባቴነህ ሲሆኑ ለመግቢያነት የሚሆን መነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ የወርክሾፑ ተሳታፊዎች አስተያዬታቸውን ሲሰጡ እንደተናገሩት ይህ ሶፍትወር መዘጋጀቱ የነበረውን ችግር የሚፈታ፣ ድግግሞሽን የሚያስቀርና ወጥ የሆነ መረጃ በክልልና በዞን ደረጃ እንዲኖር የሚያግዝ ስለሆነ በአሁኑ ስዓት ስልጠናው መሰጠቱ ለምንሠራው ሥራ በቂ ግብዓት የምናገኝበት ነው በማለት አስተያየተቸውን ሠጥተዋል፡፡

abkm1abkm2