ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Submitted by TANA on

 መጋቢት 02 ቀን 2018 ዓ.ም

ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ 

1ኛ በመደበኛው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤

2ኛ በማታው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤

ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከመጋቢት 02-11 2018 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች የሚያመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር እና የመግቢያ መስፈርቶችን ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የመመዝገቢያ ጊዜ ከመጋቢት 14-18 2018  ዓ/ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ መጋቢት 21 20118  ዓ/ም ነው፡፡ ጥራት ያለዉ ትምህርት ለመስጠትና የምርምር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ደረጃዉን የጠበቀ የምርምር ቤተሙከራ (laboratory) እና ትልቅ አቅም ባላችው ኮምፒውተሮቸ የተደራጀ ኮምፒዩቴሽናል ቤተሙከራ (high-tech capacity digital computer lab.) ዩኒቨርስቲዉ አለዉ፡፡ በተጨማሪ ለተማሪዎች የማንበቢያና መመራመሪያ ቢሮ እና  የዶርም አገልግሎት ዩኒቨርስቲዉ የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Remarks: We will admit 20 students to the MEd in Educational Sciences—Teaching of Mathematics and the MED in Educational Sciences—Teaching of Science Subjects, both supported by the BDU-NORHED scholarship program.

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች

  • የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤ 
  • ኦፊሻል ትራንስክሪፕት
  • በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚያመለክቱ አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የ National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያለው/ያላት፣
  • ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application fee 300 ብር)፣

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የትምህርት ክፍሎች

1000224663378

ለግብርናና አካባቢ ሳይንስ፤ ለሂውማኒቲስ፤ ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ለሳይንስ፤ ለአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስት ጥናት፤ ለስነ-ምድር፤ ለሶሻል ሳይንስ፤ ለእንስሣት ህክምና፤ ለባዮቴክኖሎጂ፤ ለትምህርት፤ለመሬት አስተዳደር፤ ለስፖርት እና ለህግ የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ፤

1000013094563

ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (BiT) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ

1000096185007

ለኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ (EiTEX) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ

1000257812956

ለህክምናና ጤና ሳይንስ የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ

የማመልከቻ ቦታ: -

  • ምዝገባ የሚካሄደው በ”Online” በረ ገጽ http://studentportal.bdu.edu.et/ በመጠቀም ወይንም በሚመለከታቸው የአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • በማታው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ በ Master of Business Administration,Master of Arts in Curriculum and Instruction and Master of Arts in Political Science አዲስ አበባ ማዕከል መማር የምትፈልጉ በዩኒቨርሲቲው የርቀት ማስተባብሪያ ቢሮ አራት ኪሎ ሚኒሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማመርከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት