ከትግራይ ክልል ወደ ባህርዳር ዩኒቨረሲቲ በጊዜያዊነት ተመድባችሁ ኮርሶችን ለጨረሳችሁ ተማሪዎች በሙሉ
እንደሚታወቀው በትምህርት ሚኒስትር በተወሰነው መሰረት የቀሩዋችሁን ኮርሶች በዩኒቨርሲቲያችን አጠናቃችሁ ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃችሁን ለመውሰድ እየተጠባበቃችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡በመሆኑም ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃችሁ የደረሰ ስለሆነ ከ02/03/2015 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡