የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመረቀ
Poly Campus
08 Jan, 2025
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመረቀ
[August 3, 2024 Bahir Dar, ISC/BiT]
**********
(ሀምሌ 27/ 2016 ዓ.ም ISC/BiT) ባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመደበኛው መርሃ-ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ስድት መቶ አስራ ሶስት (613) ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 442 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ሲሆኑ፤ 169 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ እና 02 ተማሪዎች በሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛው ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ፣የዕለቱ የክብር እንግዳ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል ወ/ሮ አስቴር ዘዉዴ፣ መምህራን፣ ተመራቂ ተማሪዎች እና የተመራቂ ወላጆች ተገኝተዋል፡፡
ዶ/ር መንገሻ አየነ ባደረጉት ንግግር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 60 አመታት ለሀገር ብሎም ለዓለም የተማሩ ዜጎችን ያበረከተ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል። በመቀጠልም ዩኒቨርሲቲው በምርምር፣ በፈጠራ እና በማህበረሰብ አገልግሎት ትኩረት አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን አዉስተው አሁን ላይ ምርጥ የምርምርና ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፋዊነቱን እያጎላ እንደሚገኝ የገለፁት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ፤ ከአፍሪካ ምርጥ 100 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል። ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በአራት ፕሮግራሞች አለም አቀፍ ዕውቅናን ከABET (Accreditation Board for Engineering and Technology) ማግኝቱን ገልፅዋል፡፡ ይህም ተመራቂ ተማሪዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋቸዉ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት በቀጣይ ጉዞአችው መሪ፣ ተመራማሪ እና ችግር ፈቺ በመሆን ቤተሰባቸዉንና ሀገራቸዉን እዲያገለግሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በምረቃ መርሐ-ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ አባል ወ/ሮ አስቴር ዘዉዴ ባስተላለፉት ንግግራቸው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሚያደርገዉ የምርምርና የተማሩ ዜጎችን በማፍራት የሃገር ኩራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም ከአባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ በሚለዉ መርሁ ከሚታወቀው አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት እንድሰራ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች በቆይታቸው ያገኙትን ዕዉቀትና ክህሎት በቅንነት በተግባር ለሀገራቸው እንዲያዉሉት አሳስበዋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከየፋኩልቲያቸው የላቀ ውጤት ያመጡ ተመራቂ ተማሪዎች የሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆኑ ከአጠቃላይ የኢንስቲትዩቱ ተመራቂ ተማሪወች መካከል የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪግ ተማሪ የሆነው ዳንኤል ሹመት 3.98 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።
Information and Strategic Communication Directorate
Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly
Telegram፡- https://t.me/bitpoly
Website፡- https://bit.bdu.edu.et
Twitter: - https://twitter.com/BiT_BDU
LinkedIn: - https://www.linkedin.com/company/bitpoly/
Facebook (https://www.facebook.com/bitpoly)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.