የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀድሞ ምሩቃኑ ወርሃዊ የምክክር መድረክ ላይ ተገኘ
Poly Campus
08 Jan, 2025
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀድሞ ምሩቃኑ ወርሃዊ የምክክር መድረክ ላይ ተገኘ
[ታህሳስ 01 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ኢስኮ/ባቴኢ]
============================
በፖሊ ቴክኒክ ምሩቃን ተጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊ ካፌ ሲካሄድ የቆየው ወርሃዊ የመሰባሰቢያ መርሃግብር በዛሬው እለትም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት በዓል አከባበር የፖሊ ፔዳ ምሩቃን ተሳትፎ ኮሚቴ አማካኝነት በብሄራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተካሂዷል::
መርሃ ግብሩ በያዝነው ዓመት እየተከበረ በሚገኘው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት በዓል አከባበር የቀድሞ ምሩቃንን ሚና መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን በሰብሳቢው ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው አማካኝነት ተመርቷል::
በመርሃ ግብሩ በተለይም በኮሚቴው አማካኝነት በአዲስ አበባ እና በባሕር ዳር ከተሞች በታህሳስ እና ጥር ወራት ሊካሄዱ በታሰቡት ጉባኤዎች ዝግጅት ዙርያ የተከናወኑ ተግባራት በስራ አስፈፃሚዎች በኩል ቀርበው ጥልቅ ግምገማና ምክክር ተካሂዶባቸዋል::
በመርሃ ግብሩ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተለያየ ደረጃ አመራሮችና የበዓል አከባበር ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚዎች የተገኙ ሲሆን የቀድሞ ምሩቃኑ ለዩኒቨርሲቲው እያደረጉ ላሉት ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸውና ምስጋናቸውን አቅርበው ጥረታቸው ከዚህም በላይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋርም ተናብቦ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል:: የብሔራዊ አልኮል ፋብሪካ እያደረገ ላለው ድጋፍም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/bitpoly
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et