በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(INSA) ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
Poly Campus
10 Oct, 2024
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(INSA) ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
[ነሐሴ 04/2014፣ አዲስ አበባ- ኢስኮ/ባቴኢ]
***************************************
በአዲስ አበባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መስሪያ ቤት ላይ በተካሄደው የፊርማ ስነስርዓት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በመወከል የተገኙት የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት ከፊርማ ስነ-ስርዓቱ በሗላ ባደረጉት ንግግር INSA ተነሳሽነቱን ወስዶ መድረኩን ስላዘጋጀ ምስጋናቸውን አቅርበው ዩኒቨርሲቲወች ካላቸው ተልዕኮዎች አንጻር በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በቴክኖሎጅ ሽግግር መስክ ተስማርቶ ለሃገር ደህንነት በተለይም በሳይበር ሴኩሪቲ ዘርፍ መስራቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ከINSA ጋር በመተባበር ሲሆን ደግሞ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ጠቁመዋል:: አክለውም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ፋይዳ የሚኖረው ወደ ተግባር ሲቀየር መሆኑን አውስተው ለዚህም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያለውን ቁርጠኝነት በመግለጽ በኢመደአ በኩልም ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንደሚጠብቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል::
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰሎሞን ሶካ በበኩላቸው
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር እንዴት በጋራ በመስራት የሃገራችንን የሳይበር ጥቃት የመከላከል አቅም እንገነባለን? የዲጅታል ሉአላዊነታችንስ እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? በሚሉና መሰል ጉዳዮች ዙርያ ምክክር መካሄዱን ያነሱ ሲሆን ይህ የፊርማ ፕሮግራምም ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ መስራት ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት በዘርፉ እምቅ አቅም ካላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም አብሮ መስራት እንዲቻል ታልሞ የተዘጋጀ መርሃግብር እንደሆነ አመላክተዋል:: የትብብር ሰነዱም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የሰው ሃይል ግንባታን ማሳደግ፣ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ ምርምሮችና ፕሮጀክቶች በሃገር ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ማስቻል እና የታለንት ማዕከላት ልማትን ተጋግዞ ለመስራት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ያካተተ እንደሆነ አስገንዝበው ተግባራዊ ለማድረግም ኢመድአ አበክሮ እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል::
የመግባቢያ ሰነድ መፈራረምን ተከትሎ ተቋማቱ በቀጣይነት ስለሚሰሯቸው የጋራ ተግባራት የባለሙያዎች የምክክር መድረክም በነገው እለት እንደሚካሄድ ይጠበቃል::
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/bitpoly
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et