bit

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የእቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫወች ላይ ግምገማ አካሄደ

Poly Campus

08 Jan, 2025

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የእቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫወች ላይ ግምገማ አካሄደ

[December 5, 2024 Bahir Dar, ISC/BiT]

***************************************

(ታህሳስ 26/ 2017 ዓ.ም ISC/BiT) የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ኢንስቲትዩቱ እንደሃገር በቀዳሚነት የሚታወቅ በመሆኑ የሚያቅደውን ዕቅድና አፈፃፀም ለተቋሙ ማህበረሰብ ማሳወቅ እንዳለበት ገልፀዋል። በመቀጠልም በየአመቱ የሚታቀደው ዕቅድ ተቋምን ማስተዋወቂያና ሃሳብን መሸጫ መሳሪያ በመሆኑ ትኩረት ተሰጦበት ሊሰራ እንደሚገባ አስገዝበዋል። በመጨረሻም ተቋሙ ተጨማሪ ፀጋዎችን ማግኘት የሚያስችለው በትክክለኛው መንገድ ዕቅዱን ለሌሎች አካላት መሸጥ ሲችል መሆኑን ገልጸዋል።

የበጀት አመቱን የእቅድ አፈፃፀም ዋና ዋና ተግባራት በዝርዝር ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ተወካይ ሳይንትፊክ ዳሬክተር የሆኑት ዶ/ር ምትኩ ዳምጤ ሲሆኑ ኢንስቲትዩቱ የ5 አመት ስትራቴጂካዊ መመሪያ ዕቅድ ያለው መሆኑን ገልፀዋል። በመቀጠልም የአመቱ የዕቅድ አፈፃፀምም ተፈላጊ የሆኑ የት/ት ፕሮግራሞችን መክፈት እንደተቻለ፣ በመውጫ ፈተና በ11 ፕሮግራሞች 100% ተማሪ ማሳለፍ መቻሉን፣ ተቋሙን በ4 የኢንጂነሪንግ ፕሮግራሞች ከABET ዕውቅና ማግኘት መቻሉን፣ ሁለት ትላልቅ አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በስኬት የተካሄዱ መሆኑንና በአዲሱ መዋቅር መሰረት የአካዳሚክ ቦታዎች ላይ ምደባ መደረጉን ገልፀዋል። በመጨረሻም የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ትኩረቱን የትምህርት ጥራትን ማስበቅ፣ ምርምርና የተለያዩ ፕሮግራሞችን አለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ ሰፊ ትኩረት ተሰጦ እንደሚሰራ አብራርተዋል።

በሪፖርቱ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችም የተለዩ ሲሆን ጎልተው የወጡት የበጀት ችግር፣ የዋጋ ንረት እና የትምህርት ካላንደር መጨናነቅ መሆናቸው ተገልፆ በቀረበው የአፈፃፀምና የትኩረት አቅጣጫ ሪፖርት ላይ ተሳታፊዎች አስተያየት እንዲሰጡ ተደርጎ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

Information and Strategic Communication Directorate

Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly

Telegram፡- https://t.me/bitpoly

Website፡- https://bit.bdu.edu.et

Twitter: - https://twitter.com/BiT_BDU

LinkedIn: -https://www.linkedin.com/company/bitpoly