በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2014 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገመገመ
Poly Campus
11 Oct, 2024
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2014 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገመገመ፡፡
========================
[ነሐሴ 05/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ]
በግምገማ መድረኩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮችና የማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል። ግምገማው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ መሪነት የተከፈተ ሲሆን፣ የ2014 አፈፃፀም በጥንቃቄ መገምገም እንዳለበት ገልፀው፣ 2015 ዓ.ም 60ኛ የምስረታ በዓልን የምናከብርበት ልዩ ዓመት ስለሆነ ዓመታዊ እቅዱ በትኩረት ልንሄድበት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በመቀጠልም የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት የ2014 ዓ.ም ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር ፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም በአፈጻጸሙ የታዩ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል። በዓመቱ ታቅደው ሳይተገበሩ የቀሩ እንዲሁም ለአተገባበሩ እንቅፋት የነበሩ ተግባራት ላይ ትኩረት በመስጠት በ2015 ዓ.ም ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የ2015 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ በሳይንቲፊክ ዳይሬክተሩ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን በትኩረት መሠራት ያለባቸዉና ማብራርያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በሚመለከታቸዉ የሥራ ኃላፊዎች አማካኝነት ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻም በ2014 በእቅድ አፈፃፀም የተሰሩ ሥራዎች የሚያበረታታ ስኬት መመዝገቡም ተወስቶ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና እንደ ክፍተት የታዩትን ደግሞ ለማካካስ እንዲቻል ክፍተት ያለባቸው ክንውኖች በ2015ዓም የተሻለ አፈፃፀም እና ውጤት ሊያሳዩ እንደሚገባ አስተያየት ተስጥቶባቸውመድረኩ ተጠናቋል።
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/bitpoly
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et