በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሐገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ ዓለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስናን መታገል በተግባር!” በሚል መሪ ቃል በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተከበረ
poly
08 Jan, 2025
[ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ኢስኮ/ባቴኢ]
*************************************
በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሐገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ ዓለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስናን መታገል በተግባር!” በሚል መሪ ቃል በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተከበረ።
መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት እንደተናገሩት፣ ሙስና የሀገር እድገትን በማደናቀፍ እና ህዝባዊ ስብዕና መላሸቅ በማስከተል የሥራን ሞራል በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ስልሆነ በጋራ ልንታገለው ይገባል። በንግግራቸው አክለውም የሙስና መገለጫዎች ዘርፈ ብዙህ በመሆናቸው ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት፣ ባጋራ መስራት፣ መተባበርና በአንድነት በመቆም ሙስናን በእጅጉ መቀነስ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በመቀጠልም አቶ አታሌ አያሌው፣ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል፣ የሙስና ስጋት ተጋላጭነት ጥናት ባለሙያ፣ የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ በባሕር ዳር ዪኒቨርሲቲ የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል። በገለፃቸውም የሙስና ፅንሰ ሀሳብ፣ በኢትዮጵያ የፀረ ሙስና ትግል፣ አስቻይ ሁኔታና ተግዳሮቶች፣ የፀረ ሙስና ትግል ቀጣይ አቅጣጫዎችና የባለድርሻ አካላት ሚና በሚሉት ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል።
በመጨረሻም በዶ/ር ሚንችል ግተው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ እንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር መሪነት በቀረበው ሰነድ ላይና ከተሳታፊዎች በተነሱት ሓሳቦች ዙርያ ውይይት ተደርጎ መርሃግብሩ ተጠናቋል::
Information and Strategic Communication Directorate
Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly
Telegram፡- https://t.me/bitpoly
Website፡- https://bit.bdu.edu.et
Twitter: - https://twitter.com/BiT_BDU
LinkedIn: - https://www.linkedin.com/company/bitpoly/