ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲበ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ
1ኛ በመደበኛው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛዲግሪ ፕሮግራም፤
2ኛ በማታው መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ እና የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም፤
3ኛ በርቀት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ እና PGDT ፕሮግራም አመልካቾችን፤
ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህ ማስታወቂያከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 09 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ለርቀት ፕሮግራም አመልካቾች በርቀት ማዕከላት፤ ለመደበኛና የማታ ፕሮግራም አመልካቾች ደግሞ ትምህርቱ በሚሰጥበት የአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይንም በ”Online” https://studentportal.bdu.edu.et ማመልከትየሚችሉ መሆኑን እየገለጽን
- ትምህርቱ የሚሰጥባቸውን የሙያ መስኮች ዝርዝር እና
- ለምዝገባመሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤
ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ማግኘት ይችላሉ::
ማሳሰቢያ፤
- ለ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test /NGAT/) ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ፤
- ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት በትምህርት ሚኒስቴር የወጣውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስፈርት ወይም መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
- ለPGDT አመልካቾች በመምህርነት ሙያ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፤
- ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ማስላክ የሚችሉ (ለሚመለከታቸው ብቻ)፡፡
- የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝር የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ/ም የሚገለጽ ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 24 እስከ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት