ነሐሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባህር ዳርዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ምየትምህርት ዘመንበሁለተኛ ዲግሪእና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ እና በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀንጀምሮ እስከመስከረም 14 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ለአዲስ አመልካቾች በተዘጋጀው ድረ ገጽ https://studentportal.bdu.edu.et በ”Online” ማመልከት የሚችሉ መሆኑንእየገለጽን
- ለምዝገባ መሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤
- የማመልከቻ ፎረም፤
- በመንግስት ስፖንሰር ለሚማሩየስፖንሰር ሽፕፎርም አና
- ለማመልከቻ (application fee) የሚከፈልባቸውን የዩኒቨርሲቲው የባንክ ቁጥሮች
ከዩኒቨርሲቲውሬጅስትራር ድረ-ገጽhttps://bdu.edu.et/registrar/ ማግኘት ይችላሉ::
ማሳሰቢያ፤
1ኛ. አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2ኛ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ከምዝገባ በፊት ማስላክ ይኖርባቸዋል፡፡
3ኛ ዩኒቨርሲቲው የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ወስደው ማለፍ ይኖርባቸዋል፡፡ ፈተና የሚሰጥበት ቀንበውስጥ ማስታወቂያ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ እና የፌስቡክ ገጽ ወደ ፊት ይገለፃል፡፡
3ኛ ከዚህ በፊት ለመማር ተመዝግበው ባቋረጡበት የትምህርት መስክ በተመሳሳይ የቅበላ ዓይነት መመዝገብ አይቻልም፡፡
4ኛ በቂ የተማሪ ቁጥር የማያመለክትባቸው የትምህርት መስኮች አይከፈቱም፡፡
Bahir dar University CBE Bank Account Number | 1000013099522 |
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት