news

የመመረቂያ ፕሮጀክቶችን የተመለከተ ትምህርታዊ ጉባኤ ተካሄደ

Campus Name

27 Apr, 2024

በኮምፒውቲንግ ፋኩልቲ አሰናጅነት ለፋኩልቲው ተመራቂ ተማሪዎች የተዘጋጀው የመመረቂያ ፕሮጀክትን በተመለከተ ገለፃና የልምድ ልውውጥ የተደረገበት ትምህርታዊ ጉባኤ ተካሂዷል። ጉባኤው ተመራቂ ተማሪዎች የመጨረሻ ዓመት ፕሮጀክታቸውን ሲሰሩ አዲስ ሃሳብ እንዲያፈልቁ ለማስቻል መሆኑን የፋኩልቲው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች መኮንን አቶ ተስፋሁነኝ ምንውየለት ለኢስኮ ገልፀዋል፡፡ ስለሆነም በጉባኤው የፋኩልቲው መመህራን በሆኑት አቶ ሙሉጌታ ሙጬ፣ አቶ ቃለዳዊት እስመለዓለምና አቶ ማርዬ መንግስቱ አማካኝነት ስለ ፕሮጀክት ሃሳብ ማመንጨት ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ልምዳቸውንም ለተመራቂ ተማሪዎች አካፍለዋል፡፡ ገለፃው የተደረገው በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ከእነዚህም ጉዳዮች መካከል “አንድሮይድ”፣“ኦግመንትድ ሪያሊቲ”፣ “ሃርድዌር” እና የ“ኢንተርኔት” ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡ በጉባኤው ከመቀሌ ቴክኖሎጂ ኢስቲትዩት (MiT) በምደባ የመጡ ተማሪዎችን ጨምሮ የሶፍትዌር ምህንድስና፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ጨምሮ የሰባት ት/ክፍል ተማሪዎች እንደተሳተፉበት አቶ ተስፋሁነኝ ለኢስኮ አሳወቀዋል፡፡