1.መግቢያ

እንደሚታወቀው የአንድ ሀገር ትልቅ ሀብት የሰው ሃይል ነው፡፡ በአገር ዉስጥ ሁለንተናዊ እድገትና ለዉጥ ለማምጣት በዕውቀትና በክህሎት የበለጸገ፤አቅሙ በሳይንስና ቴክኖሎጅ የተገነባ፤መረጃዎችን ማግኘትና በአግባቡ መጠቀም የሚችል፤ የመግባባት አቅም ያለዉ፣ መወያየትና  ለችግሮች መፍትሄ  ማፍለቅ  የሚችልና  ምክንያታዊ የሆነ በራሱ የሚተማመን የሰው ኃይል  ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አኳያ ከፍተኛ ትምህርት የማስፈጸም አቅምን በማመንጨትና በመገንባት  የሰለጠነ  የሰው ኃይል ለማፍራት ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡ 

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ኮሌጅ ብቃት ያለው የተማረ የሰው ሀይል በማፍራት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ ምርምሮች በማድረግና የእድገትና ልማት አቅም የሚሆኑ ማህበረሰባዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአፍሪካ ቀዳሚ የምርምር ተቋም ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ ለማሳካት ኮሌጁ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ 

ከ2013 እስከ 2017 በተዘጋጀው የዩኒቨርሲቲው የአምስት ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ላይ የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ቅበላ የማስፋትና የድህረ ምረቃ ት/ቤትን አደረጃትና አሰራር ማሻሻል የመማር ማስተማር ዘርፍ ከያዛቸው ሁለቱ ዋና ዋና ስልታዊ ዓላማዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ ከ2013 እስከ 2017 በተዘጋጀው የዩኒቨርሲቲው የአምስት ዓመት ስልታዊ ዕቅድ መሰረት አካዳሚክ ዘርፉ ትኩረት የሚያደርግባቸው ስልታዊ ጉዳዮችም፤

1.የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ቅበላ የማስፋት፣

2.የድህረ ምረቃ ት/ቤትን አደረጃትና አሰራር ማሻሻል፣

3.የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን አግባብነትና ጥራት መጠበቅ፣

4.የተሻሻለ የትምህርት አሰጣጥና የተማሪዎች ምዘና መተግበር፣

5.በመማር ማስተማር ውስጥ የአገር በቀል ዕውቀቶችን አሰናስሎ መጠቀም (Integrate indigenous knowledge use)

6.የበየነ መረብ ትምህርት አሰጣጥና የተማሪዎች ምዘና መተግበር (Strengthen online learning)፣

7.የመምህራን ልማት ማሳደግ ናቸው፡፡

በዚህ መሰረት በመማር ማስተማር ዘርፍ የተከናወኑ አበይት ተግባራትና መሰረታዊ መረጃዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡

2. መሠረታዊ መረጃዎች

2.1. የተማሪዎች መረጃ

በሳይንስ ኮሌጅ በአሁኑ ጊዜ በ7 የመደበኛ የቅድመ ምረቃ መርሐ ግብሮች ወንድ=446፤ ሴት=105፣ በድምሩ=551 በድህረ ምረቃ (ማስተርስ)፣ ወንድ=39፤ ሴት=11 በድምሩ=50 በድህረ ምረቃ (ፒ.ኤች.ዲ ዲግሪ) ወንድ= 81፣ ሴት=16 በድምሩ=97 በጠቅላላው 698 ተማሪዎች አሉ፡፡ 

ከጠቅላላ የመደበኛ ተማሪዎች ውስጥ የድህረ ምረቃ (ማስተርስና ፒ.ኤች.ዲ ዲግሪ) ተማሪዎች ድርሻ 21.06 በመቶ ሲሆን በሌላ በኩል ከጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ የሴት ተማሪዎች ድርሻ 18.91 በመቶ ነዉ፡፡ በቅድመ ምረቃ፣ ድህረ ምረቃ (ማስተርስ) እና ድህረ ምረቃ (ፒ.ኤች.ዲ) መርሐ ግብሮች 19.05፣ 22 እና 16.49 በመቶ እንደ ቅደም ተከተላቸው መሆኑ የሴት ተማሪዎች ቁጥር በሁሉም የትምህርት ደረጃ አናሳ መሆኑን ያሳያል፡፡

2.2 የመምህራን መረጃ

2.2.1 በስራ ላይ ያሉ መምህራን በትምህርት ደረጃ

aa

2.2.2. በስራ ላይ  ያሉ  መምህራን በማዕረግ

f

2.2.3 በትምህርት ላይ ያሉ መምህራን ብዛት

e

2.3. የቴክኒክ ረዳቶች መረጃ 

2.3.1 በስራ ላይ ያሉ የቴክኒካል ረዳቶች በትምህርት ደረጃ

t

 2.3.2. በስራ ላይ ያሉ የቴክኒክ ረዳቶች በማዕረግ

2.3.2

 2.3.3. በትምህርት ላይ ያሉ የቴክኒካል ረዳቶች በትምህርት ደረጃ

2.3.3

 2.4.የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ብዛት

2.4

 3. በ2016 የትምህርት ዘመን የአራተኛዉ ሩብ ዓመት ዋና ዋና ክንውኖች

 3.1. የደረጃ ዕድገት ያገኙ መምህራን

3.1

 3.2. አዲስ የተቀጠሩ መምህራን በትምህርት ደረጃ

3.2

 3.3. አዲስ የተቀጠሩ መምህራን በማዕረግ

3.3

 3.4. አዲስ የተቀጠሩ ቴክኒካል ረዳቶች በትምህርት ደረጃ

3.4

 3.5. የመምህራን የአጭር ጊዜ ስልጠና እቅድ ክንዉን በሥልጠና ዓይነት

3.5

 3.6. የተግባር ትም/ት አተገባበር እቅድ አፈጻጸም

3.6

 3.7. መማሪያ ክፍሎችን በግብዓት የማደራጀት እቅድ ክንዉን

3.7

 3.8. በበጀት ዓመት ቤተሙከራዎችን በግብዓት (በኬሚካል፤ በቁሳቁስ እና በመሣሪያዎች) የማሟላት ዕቅድ ክንዉን

3.8

 3.9. በ2016 የትምህርት ዘመን የአራተኛዉ ሩብ አመት የሚሰጡ ኮርሶች የተከታታይ ምዘና እና ግብረ መልስ እቅድ ክንዉን (ቅድመ ምረቃ)

3.9

 3.10.በ2016 የትምህርት ዘመን የአራተኛዉ ሩብ አመት የሚሰጡ ኮርሶች የተከታታይ ምዘና እና ግብረ መልስ እቅድ ክንዉን (ድህረ ምረቃ)

3.10

 3.11. በአዲስ የተቀረጹ ሥርዓተ ትምህርቶች

3.11

3.12. ክለሳ የተደረገላቸዉ ሥርዓተ ትምህርቶች

3.12

 3.13. የድህረ ምረቃ (ማስተርስ) ተማሪዎች የምርምር ተሳትፎ

3.13

3.14. የድህረ ምረቃ (ፒ.ኤች.ዲ) ተማሪዎች የምርምር ተሳትፎ

3.14

 4. በ2016 በጀት ታቅደው/ሳይታቀዱ የተከወኑ አበይት ተግባራት በአጭሩ መማር ማስተማርን በተመለከተ

~ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተዉ ክፍል ተልኳል፡፡

~ በ2016 የመውጫ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች እና ለሚያስተባብሩ መምህራን የLMS ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተገኙ ሞዴል ፈተናዎችን በቴሌግራም በመጫን ተማሪዎች እንዲለማመዱ ተደርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከሚያዚያ 21-24፣ 2016 ዓ.ም. እንዲሁም ግንቦት 26-27፣ 2016 ዓ.ም. ለሁለት ጊዜ ሞዴል ፈተና በኮሌጅ ደረጃ ተማሪዎች እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም ተማሪዎቻችን ከሰኔ 14-19፣ 2016 ዓ.ም. የተሰጠዉን የመዉጫ ፈተና በተሳከ ሁኔታ ተፈትነዋል፡፡

~ ኮርስ የጨረሱ የክረምት Premaster ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፋቸዉን ለማስቀረብና እንዲጨርሱ በተደረገዉ ሙከራ 19 ተማሪዎች የምርምር ስራቸዉነ አቅርበዉ ለምረቃ ዝግጁ ሆነዋለ፡፡

~ በጀማሪ መርሐ-ግብር ፕሮግራም የሚሰጠውን  Mathematics for Natural Sciences እና General Physics ኮርሶች በጥሩ ሁኔታ ተሰጥተዋል፡፡ 

~ የስታቲስቲክስ የማማከር አገልግሎት ለመክፈት በኮሌጅ ደረጃ ቀርቦ ግባቶች ተሰብስበዉና የተሰጡ ግባቶች በማካተት የማማከር አገልግሎት በኮሌጅ ደረጃ ለማስጀመር  የማጸደቅ ስራዉ ብቻ የቀረና በቅርቡም አገልግሎቱን ለማስጀመር በሒደት ላይ ነን፡፡

~ የኢትዮጲያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጆርናል  መመሪያ ክለሳ ተደርጉዋል

~ የኢትዮጲያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጆርናል 16(3) ታትሞ ወጥቷል፡፡የ12ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ ልዩ ዕትም በሂደት ላይ ነዉ፡፡

~ በዌብ ኦፍ ሳይንስ/ስኮፐስ እዉቅና ለማሰጠት ጥያቁዉ ለድርጅቱ ቀርቧል፡፡ መልስ በመጠባበቅ ላይ ነን

~ የት/ሚኒስቴር እዉቅናን ለማደስ ጥያቄዉ በወቅቱ ለሚመለከተዉ ቀርቧል፡፡

~ በመደበኛዉ መርሀ-ግብር ለቅድመ-ምረቃ  የ1ኛው ወሰነ-ትምህርት በጥሩ ሁኔታ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ተመራቂ የመጀመሪያ ድግሪ የባዮሎጂ ተማሪዎች በተለያዩ በተመረጡ ቦታወች ለሁለት ሳምንት የተግባር ልምምድ (internship) አድርገዋል፡፡

~ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ አካሂደዉ 1ኛ አመት ተማሪዎች ትምህርት የጀመሩ ሲሆን 2ኛ አመት ተማሪወች ፕሮፖዛል በማቅረብ የምርምር ስራ ላይ ናቸዉ 2ኛ አመት እና ከዚያ በላይ ያሉ የ3ኛ ድግሪ ተማሪወች ሪሰርች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁ መደበኛ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ድግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን እንዲየጠናቅቁ ተደረጓል፡፡

~ ለአጭር ጊዜ ስልጠና ዉጭ ሃገር ለሚሄዱ ሰልጣኞች ክትትል እና ድጋፍ ተደርጓል፡፡

~ አኒማል ሀዉስ እና ግሪን ሀዉስ አዲስ በተመረጠዉ ቦታ የመስረት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ 

~ በስታቲስቲክስ ትም/ት ክፍል መምህራን በዩኒቨርቲው በተለያዩ ግቢዎች የሚገኙ ተመራማሪወችና ለድህረ ምረቃ ተማሪወች (ለሳይንስ፤ ለስነ-ባህሪናለስነ-ትምህርት) ከ50 በላይ ለሚሆኑ በሁለት ዙር የሶፍትዌር ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ 

~ በስታቲስቲክስ ትም/ት ክፍል በኩል ለዩኒቨርሰተው ኮምፒውተር ላብራቶሪ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ 

~ በስታቲስቲክስ ትም/ት ክፍል የሦስተኛ ድግሪ ስርዓተ-ትምህርት ለመከለስ ኮሚቴወችን ተዋቅሮ እየተሰራ ይገኛል፡፡

~ በ2016 ዓ.ም. አንደኛ ወሰነ ትምህርት የመምህራን ከጫና በላይ ለሰሩ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በመሰራት ላይ ላይ ይገኛል፡፡

~ የኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ ቤተ-ሙከራ በከፊል ማደራጀት ተችሏል። ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ሁለተኛ ዙር በወጣ ጨረታ  የሸናፊ ልየታ ተደርጓዋል።

~ የቅድመ ምረቃ ቤተሙከራዎችን በአዲስ መልኩ ለማደራጀት ከየቤተሙከራዎች መረጃ የመሰብሰብ ስራ በፊዚክስ ትም/ት ክፍል ተሰርቷል፡፡ 

~ የፕሮግራም  ስርዓተ ትምህርት ክለሳ ለመስራት ታቅዶ የ3 ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት ክለሳ በፊዚክስ ትም/ት ክፍል ተሰርቷል፡፡

~ የመጀመሪያ ድግሪ (BSc) ፕሮግራሞችን አለም አቀፍ እዉቅና ለማሰጠት ይረዳ ዘንድ ከት/ት ክፍል የተዉጣጡ መምህራን በፕሮግራም አክሪዲቴሽን ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ አምስት ፕሮግራሞች (ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሒሳብ እና ስታቲስቲክስ) አለም አቀፍ እዉቅና / Program Accreditation/ እንዲያገኙ ለማድረግ በኮሌጅ ደረጃ ኮሚቴ በማቋቋም የተለያዩ ስራዎችን ኮሚቴዉ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

~ በ2015 ዓ.ም ክረምት ኮሌጁ በተቀናጀ መልኩ አገር አቀፍ የመዉጫ ፈተና LMS በመጠቀም በተሳካ ሁኔታ በ10 ፕሮግራሞች (6 BSc እና 4 BEd) 172 ተማሪዎችን ማስፈተን ችሏል:: በፈተናዉም 94.2% ተማሪዎችን ማሳለፍ ተችሏል፡፡

~ በአገር አቀፍ Remedial ፈተና ኮሌጁ በአራት ፐሮግራሞች ካስተማራቸዉ ተማሪዎች 93.76% ማሳለፍ ችሏል፡፡

~ በመደበኛዉ መርሀ-ግብር የ2015 ዓ.ም. የቅድመ ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ የሁለተኛ ሴሚሰተር ትምህርት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በዚህም 162 ተማሪዎችን በ Bsc እና በ BEd ፣  52 ተማሪዎችን በ MSc አንዲሁም 5 ተማሪዎችን በ PhD በድምሩ 219 ተማሪዎችን በ 2016 የመጀመሪያዉ ሩብ አመት ማስመረቅ ተችሏል፡፡

~ የኮሌጁ ካውንስል መማር ማስተማር ባልነበረበትና አስቸጋሪ በሆኑ ጊዚያቶች ሁሉ በመሰብሰብ በርካታ አካደሚክ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ዉሳኔዎችን አሳልፏል፡፡የመፍትሔ አቅጣጫዎችንም ሰጥቷል፡፡

~ የኮሌጁ አባላት የ Remedial course በማስተማር፣ የመዉጫ ፈተና ከዝግጅት እስከ ፈተና ድረስ በመሳተፍ እንዲሁም የ 2015 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርትፍኬት ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

~ ኮሌጁ ለረጅም ጊዜ መምህራን ሲጠይቁ የነበረዉን የላፕ-ቶፕ ጥያቄ ለመመለስ 60 ላፕ-ቶፖችን በመግዛት ለመምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ተሰጥቷል፡፡

~ የ2015 ዓ.ም 2ኛ ወሰነ ትምህርት የመምህራን እና የ 6 ወር  የአስተዳደር ሰራተኞች ግምገማ ውጤት ተሰርቷል፡፡

~ የዋሸራ ምርምር ማእከል ለሚያሰራው የላብራቶሪ ክፍል አሰተዳደራዊ እገዛ ተደርጓል፡፡

~ የመምህራን ቢሮ ማደራጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

~ ቤተ ሙከራዎችን ለማጠናከር  አስፈላጊ መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ ተሰርቷል፡፡

~ የመምህራን ልማትን በተመለከተ በኮሌጁ 4 መ/ራን ለ PhD ፕሮግራም ሄደዋል፡፡ አራት (4) መምህራን ለድህረ-ዶክትሬት ልከናል፡፡ አራት (4)  መ/ራን ከ ሌክቸረር ወደ ረዳት ፕሮፌሰር ፣አንድ መ/ርት ከ ረዳት ፕሮፌሰር ወደ ተባባሪ ፕሮፌሰር እንዲሁም አራት መምህራን ከተባባሪ ፕሮፌሰር ወደ ሙሉ ፕሮፌሰር  እንዲያድጉ ተደርጓል፡፡

~ የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ስርዓተ ትምህርት የመከለስ ስራ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

~ ለ2016 ዓ.ም የሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት የኮርስ ምደባ ተሰርቷል፡፡

~ ለኮሌጁ  መምህራን ከአሜሪካ በመጡ  ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

~ በኮሌጁ የመምህራን እጥረት በሚታይባቸዉ ትም/ት ክፍሎች መምህራንን በዝዉዉር የማምጣት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ፡- በስታቲስቲክስ ት/ት ክፍል አንድ (1) መምህርት በዝውውር የመጣች ሲሆን  ሁለት (2) የሦስተኛ ድግሪ እንዲሁም አንድ (1) የዳታ ሳይንስ መምህራንን በዝውውር ለማመጣት በሂደት ላይ ነን፡፡

~ በኮሌጁ በተለያዩ ዘርፎች የማማከር አገልግሎት ለመክፈት እንዲሁም የሳመር ስኩል ለመክፈት በእንቅስቃሴ  ላይ እንገኛለን፡፡ ለምስሌ፡- በስታስቲክስ ትም/ት ክፍል የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች አሉ፡፡

ድህረ-ምረቃ፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በተመለከተ

ሀ)ምርምር

  1. 1. 14 ነባር ሜጋ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ እገዛ አግኝተዉ ወደስራ ገብተዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ ስድስቱ የደረሱበትን ደረጃ የሚያሳይ ዲፌንስ ለኮሌጁ ማህበረሰብ አቅርበዋል፡፡ ማራዘሚያም ሂደቱን ጠብቀዉ ጠይቀዋል፡፡ በምርምር እና ማህበረሰብ አግልግሎት ቢሮ ማራዘመያዉ ፀድቋል፡፡
  2. 2. 6 የሜጋ ፕሮጀክቶች ግምገማ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
  3. 3. 4 ነባር የሜጋ ፕሮጅክቶች የስራቸዉን ሂደት የሚያሳይ ፖስተር ለ12ኛዉ ዓመታዊ የሳይንስ ኮንፍረንስ አዘጋጅተዋል፡፡
  4. 4. በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በግራንት ዙሪያ ልምድ ልዉዉጥ ተካሂድዋል በዚህም መሰረት አንድ senior project በፊዚክስ፤ በኬሚስትሪ እና በባሎጂ ት/ክፍሎች በጋራ የሚሰራ አስጀምረናል፡፡ BSF ፕሮጀክት ለሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ጥሪ አድርገናል፡፡
  5. 5. በኮሌጅ ደረጃ የተዋቀሩ መምህራን የግራንት ራይቲንግ ስልጠና ታህሳስ 12 እና 13፣ 2016 ዓ.ም. ለ2 ቀን ወስደዋል፡፡
  6. 6. ነባር የድህረ-ምረቃ የMsc ሁለተኛ ዐመት ተማሪዎች  እና የ PhD ተማሪዎች  የምርምር ስራቸዉን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
  7. 7. በመምህራንና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምርምር ስራዎች ታትመዋል፡፡

)ማህበረስብ አገልግሎት

  1. 1. ለ11ኛዉ Math Camp ፕሮግራም ከ 24/10/2016 -30/10/2016 ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቶች በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡
  2. 2. አዲስ ስምንት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በኮሌጁ አካዳሚክ ካዉንስል ፀድቀዉ ወደ ማእከል ተልከዋል፡ ለ2017 በጀት ወደፊት የሚገለፅ ይሆናል
  3. 3. 6 የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በፖስተር ሰኔ 21/2016 ዓ.ም. በማዕከል ደረጃ ኮሌጃችን ወክለዉ ቀርበዋል፡፡
  4. 4. ለ2016 ዓ.ም የቀረቡ ሰባት የማህበረሰብ አገልግልት ፕሮጀክቶች በኮሌጁ አካዳሚክ ካዉንስል ፀድቀዉ ወደ ማዕከል ተልከዉ የነበረ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ በባህር ዳር እና ዙሪያዋ ሊሰሩ የሚችሉ አራቱ በጀት ተለቆላቸዉ ስራቸዉን በማገባደድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሐ)ድህረ-ምረቃ ትምህርትን በተመለከተ

  • 1. የመማር ማስተማሩ ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ከት/ክፍሎች እና ከተማሪ ተወካዮች ካገኘነዉ መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
  • 2. የ97 የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ስታተስ እና የ53 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ስታተስ ተጠናቅሮ ለሚመለከተዉ ክፍል ተልኳል፡፡
  • 3. የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በ Validity period and Extension ዙሪያ በሴኔት ፀድቆ የመጣዉን ህግ ለማስረዳት የግማሽ ቀን ዉይይት አድርገናል፡፡

) የኮሌጁ ዓመታዊ ኮንፍረንስ

  • .12ኛዉ ዓመታዊ የኮሌጁ የሳይንስ ኮንፍረንስ በሚያዚያ 04-05/2016 ዓ.ም. (April 12-13, 2024) በጥሩ ሁኔታ ተካሂዳል፡፡

) ጆርናል

  1. 1. የኢትዮጲያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጆርናል 17(1) ታትሞ ወጥቷል፡፡
  2. 2. በዌብ ኦፍ ሳይንስ/ስኮፐስ እዉቅና ለማሰጠት ጥያቁዉ ለድርጅቱ ቀርቧል፡፡ መልስ በመጠባበቅ ላይ ነን

የቤተ ሙከራ ማኔጀር የ2016 በጀት አመት በ4ኛዉ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት

1. የ 2017 ዓ.ም የላቦራቶሪ መሳሪያዎች እና ኬሚካሎች የግዥ እቅድ ታቅዷል፡፡

2. በኮሌጃችን ለሚገኘዉ የ ICP-OES ላቦራቶሪ መሳሪያ ለረጅም ጊዜ ስራ አቁሞ የቆየ ቢሆንም በኬኒያ ሃገር ከሚገኘዉ International    livestock research institute (ILRI) 7500 ዶላር የሚያዎጡ የመለዋወጫ እቃቆችን በስጦታ በማግኘት ስራ እንዲጀምር ተደርጓል፡፡

3. የተመረጡ ቤተ-ሙከራዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ እዉቅና ለማሰጠት የሰነድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ከተመረጡት 5 ላቦራቶሪዎች አንደኛዉ በሃገርም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ እዉቅና ያገኘ ተቋም ማኘት ባለመቻሉ እና በእዉቅና ሰጪ ተቋሙ (EAS) ሰራተኞች ጋር ዉይይት በማድረግ ከሂደቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ 

4. ሌሎች 4ቱ ላቦራቶሪዎች የድርጊት መርሃግብር በማዘጋጀት ለአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት በኮሌጃችን ላቦራቶሪ ማናጀር በኩል በኢሜል እንዲላክ ተደርጓል፡፡

5. 4ቱን ላቦራቶሪዎች እዉቅና ለማሰጠት እየተደረገ ያለዉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የኮሌጁ ማኔጅመንት በየሳምንቱ ይገመገማል፡፡

6. የተመረጡ ቤተ-ሙከራዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ እዉቅና ለማሰጠት የሰነድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከታህሳስ 8/2016 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 12/2016 ዓ/ም ድረስ ለ5 ቀን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በተዘጋጀዉ የላቦራቶሪ እዉቅና አሰጣጥ ስልጠና 14 የኮሌጃችን  አባላት በተሳካ ሁኔታ ስልጠናዉን አጠናቀዋል፡፡  

7.የ2015 ዓ.ም የቤተ-ሙከራ መሳሪያዎች እና ኬሚካሎች  ቆጠራ  በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

8.የኮሌጁ ቤተ-ሙከራ አጠቃቀም መመሪያ ክለሳ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የጥራት አስተባባሪ የ2016 በጀት አመት በ4ኛዉ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት፣
4

ሳይታቀዱ የተከወኑ

1.ለመምህራን አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መውሰድ (Master Class Training  )

2.በስራ ገባታቸዉ ያልተገኙ እና ለትምህር ሄደዉ ያልተመለሱ መምህራንና እና  የቤተ ሙከራ ቴክኒሻኖች  ከስራ መሰናበት

3.የኮሌጁ ላቦራቶሪ ቴክኒሻን (Website Manager)   ወደ  ኢንዱስትሪያል ትም/ት  ክፍል መዛወር 

4.በተለምዶ ጦጣዉ ካፌ በአዲሱ አጠራሩ ሳይንስ አምባ ካፌ ተብሎ የሚጠራዉን የመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች መዝናኛ ክበብ በኮሌጁ ተነሳሽነት የማደስና እንደ አዲስ የማደራጀት ስራ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

5.የድህረ ምረቃ ኮምፒዩቴሽናል ላቦራቶሪ ለማቋቋም አስፈላጊ ግብዓቶች ከተሟላ ስፔስፊኬሽን ጋር ተለይተው ወደ ግዥ ሲስተም እንዲገቡ በፊዚክስ ትም/ት ክፍል ተደርጓል በግዥ ሂደት ላይ ነዉ ፡፡

6.አዲስ ወደ ተቋቋመዉ የትምህርት ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም. ሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት 9 የኮሌጃችን መምህራን ተዛውረዋል፡፡

ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራት

1.የድህረ ምረቃ (ፒአችዲ)  ካሪኩለም ቀረጻ እና የ ማስተርስ ካሪኩለም ክለሳ አለማድረግ

2.በወቅታዊ ችግር ምክንያት የትምህርት ካሌንደሩ መገፋቱ፡፡ 

3.በወቅታዊ ችግር ምክንያት እና ከGAT ፈተና ጋር በተያያዘ በቂ ቁጥር ያለዉ የመጀመሪያ አመት የ2ኛ እና የ3ኛ ድግሪ ተማሪ አለማግኘት፡፡

4.ሀይቴክ ፕሮሰሲንግ ኮምፒዉተር መግዛት(ለመምህራን፤ለድህረ-ምረቃና ለዳታ ሳይንስ የመጀመሪያ ተማሪዎች) አለመቻል

5.አዲስ የክረምት ትምህርት ተማሪዎችን ተቀብለን ማስተማር አለመቻላችን፡፡

 5. ያጋጠሙ ችግሮች

~ በኮሌጃችን በኩል ለጨረታ ከወጡት 26 የላቦራቶሪ መሳሪያዎች መካከል 6ቱ በቴክኒክ ኮሚቴ በኩል ያለፋ ቢሆንም ከገበያ ጥናት ጋር በተያያዘ ዉድቅ ተደርገዋል፡፡

~ ሞዴል Exit Exam ለመፈተን የ Server እና መብራት መቆራረጥ

~ የምርምር (የሜጋ ፕሮጀክት) ግዥ ለመፈፀም በተለያዩ ምክንያቶች አለመቻል፡፡

~ የምርምር በጀት በወቅቱ አለመለቀቅ

~ በወቅታዊ እና አካባቢያዊ ችግሮች ተመራማሪዎች ተንቀሳቅሰዉ መረጃ ለመሰብሰብ መቸገራቸዉ፡፡

~ የቴክኒካል አሲስታንቶች የክሬዲት ሃወር እና የክፍያ ተመንን በተመለከተ ከዚህ በፊት የነበረዉ በከፍተኛ ትምህር ተቋማት በመንግስት በጀት ለሚሸፈኑ ወጪዎች የክፍያ ተመን መመሪያ እንዲሁም በቅርብ ጊዜ የመጣዉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካዳሚክ ቴክኒክ ረዳት ባለሙያዎች የአስተዳደር መመሪያ አተረጓጎም ልዩነት በመፈጠሩ ለአፈጻጸም መቸገር፡፡

~ በወቅታዊ ችግር  ምክንያት   የቅድመ- ምረቃ ፕሮግራም መማር -ማስተማር  በታቀደው ልክ አለመሄድ እንዲሁም በድህረ ምረቃ ፕሮግራም የአዲስ ገቢ ተማሪወ ቁጥር በጣም መቀነስ፡፡

~ የት/ት ካሌንደር መጣበብ፤ ኮርሶችና አስተምሮ ለመጨረስ የሚሰጠው ጊዜ አጭር መሆን በተለይ የጀማሪ መርሀ-ግብር ፕሮግራም፡፡

~ በኮሌጁ ላሉት ትም/ት ክፍሎች አስፈላጊዉን ግባቶችን ለማሟላት የግዥ ሥርዓት ችግር

~ የመምህራን ቢሮ እጥረት እና በአንድ ስፋራ አለመሆን ችግር፡፡

~ በመምህራን ቢሮ እንዲሁም Smart Classroom አከባቢ መብራት በተደጋጋሚ መጥፍት፣ መማር-ማሰተማር መቋረጥ እና ስራ ላይ ጫና መፍጠር

~ በወቅታዊዉ የጸጥታ ችግር እንዲሁም  መብራት በተደጋጋሚ መጥፍት ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎት በተደጋጋሚ መቋረጥ እና አንዳንድ ቢሮዎች ለረጅም ጊዜ የኢንተርኔት አገልግሎት አለማግኘት፡፡

~ በትምህርት ሚኒስቴር ዉሳኔ የክረምት መርሀ-ግብር በታቀደዉ ወቅት አለመሰጠቱ፡፡

 6. የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች

~ የተጀመሩ (Program Accriditation, Grant Writing, Laboratory Accridititation) አጠናክሮ መቀጠል፡፡

~ የተጀመሩ የግንባታ ስራዎችን (ቤተ-ሙከራ ማደራጀት, Green house and Animal house) አጠናክሮ መቀጠል፡፡

~ የመማር ማስተማር ስራን አጠናክሮ መቀጠል፡፡

~ የመዉጫ ፈተናን/Exit Exam/ በተመለከተ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራት::

~ ዩኒቨርሲቲው ብሎም ት/ት ሚኒሰቴር በሚያወጣው አካዳሚክ ካሌንደር መሰረት መማር ማሰተማሩን አንዲቀጥል ማደረግ፡፡

~ ኮርስ ቸሮችና ሜንተሮች ከዚህ በፊት ከነበርው አሰራር በተሻለ መልኩ ሰራውን በባለቤተነት እንዲሰሩ ማደረግ፡፡ 

~ የ EJST Article Submission and Review ሂደቱን ኦን-ላይን ለማድረግ በኮሌጁ ሙከራ እየተደረገ ሲሆን፤ በቀጣይ ሂደቱን አጠናክሮ ማስቀጠል፡፡ 

EJST Language expert and Layout Designer በመመሪያዉ መሰረት ለማስመደብ ጥረት ይደረጋል፡፡

~ EJST ጆርናላችን በScopus እና በWeb of Science እንዲታወቅ ለማድረግ የተጀመረዉን ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል፡፡

~ለአመቱ ምስጉን ሰራተኛ (ም/ዲን፣ ት/ት ክፍል ኃላፊ፣ መምህር፣ ቴክኒካል ረዳት፣ ሬጅስትራር፣ ቤተ-መጽሐፍት…) ዕዉቅና መስጠት፡፡

~ African Institute for Mathematical Sciences (AIMS) ጋር በተያያዘ ከዉጭ አጋር አካላት ጋር በመሆን ስልጠናዎችን መዉሰድ ኮንፍረንስ ማዘጋጀት በቀጣይ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ለመክፈት መስራት፡፡

~ Data Science ጋር በተያያዘ ከዉጭ አጋር አካላት ጋር በመሆን  ስልጠናዎችን መዉሰድ ኮንፍረንስ ማዘጋጀት የተጀመረዉን የመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራም አጠናክሮ መቀጠል፡፡

~ Summer School Progrm በምስራቅ አፍሪካ የስልጠና መዕከል ማደራጀት፤ ስልጠናዎችን መዉሰድ ኮንፍረንስ ማዘጋጀት፡፡

~ Statistics Support unit (SSU) ማዕከል መክፈትና ወደስራ መግባት፡፡

ከተለያዩ ሀገራት ጋር University partnership /አጋርነት/ መፍጠር፡፡ ለምሳሌ፡  በኬኒያ፣ በሩዋንዳ በደ/አፍሪካ፣ በህንድ እና በአሜሪካ ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የተጀመሩ አብሮ የመስራት ጅማሮዎችን አጠናክሮ መቀጠል፡፡ 

 7. ማጠቃለያ ቁልፍ አመላካቾች

የ2016 በጀት አመት የመማር ማስተማር ዕቅድ ቁልፍ አመላካቾች

0o2o4o5cg2354