ማስታወቂያ
ለመደበኛ መርሃ ግብር ድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመንበመደበኛ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችንተቀብሎማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነምየመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ እና መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከመስከረም 10 ቀን 2015 ዓ/ምድረስ ለአዲስ አመልካቾች ከተዘጋጀው ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/graduatapp/የማመልከቻ ቅጹን በማውረድ (Download) በማድረግና በመሙላት ከላይ በተገለፀው ድረ ገጽ online ወይም በአካል ትምህርቱ ወደሚሰጥበት የአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር በመገኘት ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለምዝገባ መሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤ ትምህርት የሚሰጥባቸውን የሙያ መስኮች፤ ለማመልከቻ (application fee) የሚከፈልባቸውን የዩኒቨርሲቲው የባንክ ቁጥሮችነ እና የማመልከቻ ፎረሙን ከማመልከቻ ድረ ገጹ https://bdu.edu.et/graduatapp/ማግኘት ይችላሉ::
ማሳሰቢያ፤ አመልካቾች
1ኛ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ማስላክ ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ ዩኒቨርሲቲውየሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ወስደው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፈተና የሚሰጥበት ቀንበውስጥማስታወቂያእንዲሁምበዩኒቨርሲቲውሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/እናየፌስቡክገጽወደ ፊት ይገለፃል፡፡
3ኛ ከዚህ በፊት ለመማር ተመዝግበው ባቋረጡበት የትምህርት መስክ በተመሳሳይ የቅበላ ዓይነት መመዝገብ አይቻልም፡፡
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
photo