ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
- የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም (መጀመሪያ ዲግሪ) ለመማር የሚያመለክቱ የመግቢያ መስፈርት
1.1 በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ውጤት ለሚያመለክቱ
1.1.1 (ሀ) ለመደበኛ ፕሮግራም
- የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው በትምህርት ሚኒስቴር የሚወጣውን የዘመኑን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
(ለ) ለኢ-መደበኛ ፕሮግራም
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው የዘመኑን የከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል የተቀመጠውን ዝቅተኛ የመግቢያ ነጥብ ያሟሉ፤
- በ2015 ዓ/ም እና በ2016 ዓ/ም ለሁሉም ፆታ 50% እና ከዚያ በላይ (ለተፈጥሮ ሳይንስ 350፤ ለማህበራዊ ሳይንስ 300፤ ለዓይነ ስውራን 250) እና ከዚያ በላይ ያመጡ፤
- በ2014 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 50% (ለተፈጥሮ ሳይንስ 1ኛ ዙር ተፈታኝ 300፤ 2ኛ ዙር ተፈታኝ 350 እና ለማህበራዊ ሳይንስ 1ኛ ዙር ተፈታኝ 250፤ 2ኛ ዙር ተፈታኝ 300) እና ከዚያ በላይ ያመጡ፤ ለግል (ድጋሚ ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች) ለሁሉም ፆታ 355 እና ከዚያ በላይ፤
- በ2013 ዓ.ም ለወንድ 330፤ ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ
- በ2012 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 140 እና ከዚያ በላይ
- ከ2009 - 2011 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 295 እና ከዚያ በላይ
- በ2008 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 275 እና ከዚያ በላይ
- በ2007 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 250 እና ከዚያ በላይ
- ከ2004 - 2006 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 265 እና ከዚያ በላይ
- በ2003 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 298፤ ለሴት 280)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 290፤ ለሴት 280) እና ከዚያ በላይ
- በ2002 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 180፤ ለሴት 150)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 205፤ ለሴት 180) እና ከዚያ በላይ
- በ2001 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 128፤ ለሴት 126)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 206፤ ለሴት 151) እና ከዚያ በላይ
- በ2000 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 221፤ ለሴት 176)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 238፤ ለሴት 176) እና ከዚያ በላይ
- በ1999 ዓ.ም እና በ1997 ዓ/ም ለወንድ 201፤ ለሴት 175 እና ከዚያ በላይ
- በ1998 ዓ.ም ለወንድ 201 እና ከዚያ በላይ፤ ለሴት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ያስመዘገቡ በሙሉ፤
- በ1996 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 101 እና ከዚያ በላይ
- ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲኘሎማ ለሚያመለክቱ፤
- ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲኘሎማ ለሚያመለክቱ፤
1.1.2 ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ በቀድሞው የትምህርት ፖሊሲ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያነት አያገለግልም፤
1.1.3 በአንድ ዘመን የተቆረጠ የመቁረጫ ነጥብ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ብቻ በግላቸው ለሚማሩ ያገለግላል፡፡ ከ5 ዓመት በኋላ ስለማይሰራ በግላቸው ከፍለው ለመማር የሚፈልጉ እንደ አዲስ የመግቢያ ፈተና ወስደው በዘመኑ የሚቆረጠውን የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ፤
1.1.4 ከ2014 ዓ/ም በፊት በነበሩ የመቁረጫ ነጥብ ይማሩ ለነበሩ/መማር ለሚፈልጉ የየዘመኑ የከፍተኛ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ያለምንም የጊዜ ገደብ የሚስተናገዱና የ5 ዓመቱ የጊዜ ገደብ አቆጣጠር ለሁሉም አመልካቾች ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
- ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት፤
- በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ 10ኛ ክፍልን (በቀድሞው 12ኛ ክፍልን) ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- ቢያንስ በደረጃ 4 /Level 4/ የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ ወስደው ብቁ የሆኑና ጊዜው ያላለፈበት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፤
- የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ብቁ በሆኑበት ሙያ የሁለት ዓመት ተግባራዊ የስራ ልምድ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ካገኙበት ሙያ ጋር ተዛማቸ በሆነ ፕሮግራም መቀጠል የሚችሉ፤
- የግብርና ባለሙያዎች ከደረጃ 4 /Level 4/ ወይም ከዲፕሎማ COC የብቃት ማረጋገጫ ያላቸውና በተመሳሳይ መስክ መቀጠል የሚችሉ፤
- ከዲፕሎማ ለመምህርነት ሙያ የሚሰለጥኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡትን የመግቢያ ፈተና ያለፉና በሰለጠኑበት ሙያ መቀጠል የሚችሉ፤
- ኦፊሻል ትራንስክርፕት ቀደም ከተማሩበት ተቋም መማር ወደፈለጉበት ተቋም ማስላክ የሚችሉና ትክክለኛ የሆነ ኦፊሻል ትራንስክርፕት ያላቸው፤
2) PGDT ለመማር የሚያመለክቱ የመግቢያ መስፈርት
- ከታወቀ ተቋም በመምህርነት ሙያ የትምህርት መስኮች ብቻ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፤
- በግላቸው ከፍለው መማር የሚችሉ ወይም ስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ኦፊሻል ትራንስክርፕት ቀደም ከተማሩበት ተቋም መማር ወደፈለጉበት ተቋም ማስላክ የሚችሉና ትክክለኛ የሆነ ኦፊሻል ትራንስክርፕት ያላቸው፤
3) የድህረ ምረቃ ፕሮግራም (2ኛና 3ኛ ዲግሪ) ለመማር የሚያመለክቱ የመግቢያ መስፈርት
3.1 የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ለመመዝገብ፤
- በስርዓተ ትምህርቱ ላይ በተቀመጡ የሙያ መስኮች እውቅና ካለው ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ (ለ2ኛ ዲግሪ)፤ በሁለተኛ ዲግሪ (ለ3ኛ ዲግሪ) የተመረቁ፤
- በመንግስት ለሚገኝ የትምህርት ዕድል የእድሜ ጣራ 35 ዓመትና ከዚያ በታች (ለ2ኛ ዲግሪ)፤ 45 ዓመትና ከዚያ በታች (ለ3ኛ ዲግሪ) የሆኑ፤
- በግል ሙሉ ወጭ ለሚገቡ የትምህርት ዕድል የእድሜ ጣራ የለውም፡፡
- በግላቸው ከፍለው መማር የሚችሉ ወይም ስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በትምህርት ክፍሎች የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና የሚያልፉ፤
3.2 ኦፊሻል ትራንስክርፕት ቀደም ከተማሩበት ተቋም መማር ወደፈለጉበት ተቋም ማስላክ የሚችሉና ትክክለኛ የሆነ ኦፊሻል ትራንስክርፕት ያላቸው፤
ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች በዩኒቨርሲቲው ነፃ ትምህርት እድል ተሰጥቷቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር የሚያመለክቱ
- ዲፕሎማ ወይም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ደረጃ 4 /Level 4/ ያላቸው፤
- ቢያንስ በደረጃ 4 /Level 4/ የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ ወስደው ብቁ የሆኑና ጊዜው ያላለፈበት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፤
- የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ብቁ በሆኑበት ሙያ የሁለት ዓመት ተግባራዊ የስራ ልምድ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ካገኙበት ሙያ ጋር ተዛማቸ በሆነ ፕሮግራም መቀጠል የሚችሉ ናቸው፡፡
አባሪ፤
የመግቢያ መስፈርት (ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ላልሆኑ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁጫ ነጥብ)
12ኛ ክፍልየተፈተኑበትዘመን | ወደ ከፍተኛ ትም/መግቢያ ዘመን | የየዘመኑ መቁረጫ ነጥብ | ምርመራ | |||
ተፈጥሮ ሳይንስ | ማህበራዊ ሳይንስ | |||||
ወንድ | ሴት | ወንድ | ሴት | |||
1995 | 1996 | 101 | 101 | 101 | 101 |
|
1996 | 1997 | 201 | 175 | 201 | 175 |
|
1997 | 1998 | 201 | ሁሉም | 201 | ሁሉም |
|
1998 | 1999 | 201 | 175 | 201 | 175 |
|
1999 | 2000 | 221 | 176 | 238 | 176 |
|
2000 | 2001 | 128 | 126 | 206 | 151 |
|
2001 | 2002 | 180 | 150 | 205 | 180 |
|
2002 | 2003 | 298 | 280 | 290 | 280 | ከ500 |
2003 | 2004 | 265 | 265 | 265 | 265 | ከ700 |
2004 | 2005 | 265 | 265 | 265 | 265 | ከ700 |
2005 | 2006 | 265 | 265 | 265 | 265 | ከ700 |
2006 | 2007 | 250 | 250 | 250 | 250 | ከ700 |
2007 | 2008 | 275 | 275 | 275 | 275 | ከ700 |
2008 | 2009 | 295 | 295 | 295 | 295 | ከ700 |
2009 | 2010 | 295 | 295 | 295 | 295 | ከ700 |
2010 | 2011 | 295 | 295 | 295 | 295 | ከ700 |
2011 | 2012 | 140 | 140 | 140 | 140 | ከ400 (Eng., Math., Apt. & Phy./Geo. |
2012 | 2013 | 330 | 320 | 330 | 320 |
|
2013 | 2014 (1ኛ ዙር) | 300 | 300 | 250 | 250 | ከ600 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ500 (ማህ/ሳይንስ) (Civics cancelled) |
2014 (2ኛ ዙር) | 350 | 350 | 300 | 300 | ከ700 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ600 (ማህ/ሳይንስ) | |
2014 | 2015 | 350 | 350 | 300/250 | 300/250 | ከ700 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ600 (ማህ/ሳይንስ)፤ከ500 (ዓይነ ስውራን) |
2015 | 2016 | 350 | 350 | 300/250 | 300/250 | ከ700 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ600 (ማህ/ሳይንስ)/ከ500 (ዓይነ ስውራን) |
ማሳሰቢያ፤ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ በአንድ ዘመን የተቆረጠ የመቁረጫ ነጥብ ለ5 ተከታታይ ዓመት ብቻ ያገለግላል፡፡ ከ5 ዓመት በኃላ እንደ አዲስ የመግቢያ ፈተና ወስዶ በዘመኑ የሚቆረጠውን የመቁረጫ ነጥብ ማምጣት ይተበቃል፡፡
ለ2016 ዓ/ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መቁረጫ ነጥብ