ታህሳስ 04 ቀን 2017 ዓ.ም
የጥሪ ማስታወቂያ
ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች በሙሉ
በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5 እስከ ጥር 7/2017 ዓ.ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግሽ አባይ ግቢ (Gish Abay Campus) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፡ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
- የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣
- ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣
- አራት 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል።