
የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም
የጥሪ ማስታወቂያ
በ2015 ዓ/ም በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ
በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ፤
ከየካቲት 20 - 22 ቀን 2015 ዓ/ም ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፤
1ኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፣
2ኛ በተለያየ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ወሰነ ትምህርት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በ2015 ዓ.ም 1ኛ ወሰነ ትምህርት ለመልሶ ቅበላ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን 1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ያቋረጣችሁ ግን መልሶ ቅበላ የምትጠይቁት በ2ኛው ወሰነ ትምህርት መሆኑን እናሳስባለን፡፡
3ኛ ከተገለጸው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
Main Registrar Office
Tel: 0582205934
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University