Latest News

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስ ፋኩሊቲ ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የመታሰቢያ መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

በትዕግስት ዳዊት

በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በተለይም በጂኦግራፊ የትምህርት መስክ፣ በሀገራችን ፖለቲካ እና በርከት ያሉ ተግባራትን በመከወን ዘመን የማይሽረው አስተዋጽ አበርክተው እና አሻራ ትተው ያለፉትን ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን በጥቂቱ ለመዘከር የተደረገ መርሀ ግብር መሆኑን መርሀ ግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የፋኩልቲው ዲን ዶ/ር ቃለወንጌል ምናለ  ተናግረዋል፡፡

 

ደ/ር ቃለወንጌል አክለውም ወደፊት የማህበራዊ ሳይንስ ፋኩልቲ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን ጨምሮ የሌሎችንም በተለያየ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ለሆኑ የአንጋፋ ምሁራን ስራዎች ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ መርሀ ግብሮች፣ እንዲሁም ውይይቶችን በሰፊው እንደሚያዘጋጅ ተናግረዋል፡፡

በማስከተል የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም አጭር የህይወት ታሪክ በዶ/ር አረጋ ባዘዘው የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ቀርቧል፡፡

የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የቀድሞ ተማሪ የነበሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር ፈረደ ዘውዱ የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የአስተማሪነት ዘመን ትዝታቸውን ያካፈሉ ሲሆን ፕሮፌሰሩን ሀገር ወዳድ፣ ለወገን ተቆርቋሪና ጀግና ምሁር ሲሉ አውስተዋቸዋል፡፡

በተጨማሪም ዶ/ር ጥጋብ በዜ እና ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በህይወት ዘመናቸው ስላበረከቷቸው ታሪክዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበረሰባዊ ይዘት ስላላቸው መጽሀፍት፣ ስላዘጋጇቸው የማስተማሪያ መጻህፍት እንዲሁም ስለ ማህበራዊ ህይወታቸው የሚዳስስ ወረቀት አቅርበዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ዘመን ተሸጋሪው የአደባባይ ምሁርና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች መሆናቸውም ተወስቷል፡፡

በመርሀ ግብሩ የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የቀድሞ ተማሪዎች፣ የስራ ባልደረቦች፣ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ታድመዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ መክፈቻ የሻማ ማብራት ስነ-ስርአት እንዲሁም የሁለት ደቂቃ የህሊና ጸሎት በሊቀ-ህሩያን በላይ መኮኘን የተደረገ ሲሆን በመጨረሻም የደራሲያን ማህበር ባህር ዳር ቅርንጫፍ ፕሬዚዳት የሆኑት ሊቀ-ህሩያን በላይ መኮንን የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን ህልፈት አስመልክተው አጠር ያለ ግጥም አቅርበዋል፡፡

 

 

 

የማስክ/ጭንብል/ የቤት ውስጥ አዘገጃጀት እና አጠቃቀም የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሠጠ ነው

ትዕግስት ዳዊት

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ መምህራን እና FGCF ከተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በመጡ አሰልጣኞች የተዘጋጀው የአሰልጣኞች ስልጠና ባሕር ዳር ዙሪያ ከሚገኙ 63 ት/ቤቶች ለተወጣጡ ፍላጎቱ ያላቸው 126 መምህራን እየተሰጠ ሲሆን ከጥቅምት 25 ጀምሮ እስከ 28 እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

ከዚህ ስልጠና በኋላ ኋሰልጣኞች በሚያስተምሩባቸው ት/ቤቶች ለሚገኙ ስልጠናውን ላልወሰዱ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

FGCF ከተባለው ግብረ-ሰናይ ድርጅት ስልጠናውን ለመስጠት የመጡት ሲ/ር ማርናት አዱኛ እንዳሉት በኮሮና ምክንያት ተዘግተው የነበሩት ትምህርት ቤቶች በቅርቡ የሚከፈቱ በመሆናቸው የኮሮናን አደጋ ለመቀነስ እንዲቻል መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ ሲ/ር ማርናት  አክለውም ተማሪዎችና መምህራን ወጭ ሳያወጡ ቤት ውስጥ በሚገኙ ባገለገሉ ልብሶች ጭንብል ማዘጋጀት እንዲችሉ የሚያስችል ውጤታማ ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው ከማስክ/ጭንብል/ አሰራር በተጨማሪ ሲ/ር ማርናት ስለኮሮና ቫይረስ (COVID _19) መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች ለሰልጣኞች አስረድተዋል፡፡

ሜጫ ወረዳ በወተት አባይ ት/ቤት መምህር የሆኑት መምህር ሽባባው አስማረ የስልጠናውን ጠቃሚነት አብራርተው ወጭ ቆጣቢና ማንም ሰው አገልግሎት ከሰጡ ጨርቆች ማዘጋጀት የሚችለው መሆኑን እና ያገኙትን እውቀትም ለሌሎች እንደሚያጋሩት አያይዘው ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ ከፍርን የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት የመጡት መምህርት ማለፊያ ልየው ከስልጠናው ስለኮሮና ቫይረስ (COVID _19) ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶች፣ በቁሶች ላይ ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል/ማስክ/ በቤት ውስጥ እንዴት እንደሚዘጋጅና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሰፊ እውቀት ማግኘታቸውን አጋርተውናል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ውይይት ተካሄደ ፡፡

የአገሪቱን የአሳ ግብርና ለማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ለማስጀመር Advancing Climate Smart Aquaculture Technologies (ACliSAT) በሚል ርዕስ ከመስከረም 22-23 አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡ በአውደ ጥናቱ  በዋነኛነት የፕሮጀክቱን ትግበራ ማስጀመር በሚቻልባቸው፣ በትብብር መስራት በሚያስፈልግባቸው ጉዳዮችና በአጠቃላይ የአገሪቱን የአሳ ግብርና ማሳድግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የሚያተኩሩ ጥናታዊ ፁሁፎች ቀርበው፣ ሰፊና ገንቢ ውይይት ተደርጓል፡፡  

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተስፋየ ሽፈራው  ዩኒቨርሲቲው ዘንዘልማ በሚገኝው ካምፓሱ ከቅድመ ምረቃ እስከ ፒኤችዲ ደረጃዎች በአሳ ልማት ዘርፍ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ተስፋየ አክለውም ጣና ሀይቅ አካባቢ የአሳ ሀብታችንን በተሻለ መንገድ ለመጠበቅ የሞዴል ፋርም ተገንብቶ ለስልጠና እና የአሳ እርባታን ለማዘመን እየተሰራ ቢሆንም በሃገሪቱ ፈጣን የህዝብ ብዛት፣ ከፍተኛ የወጣት ሥራ አጥነት መጨመር እና ከተጋረጠብን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጋር ሲነፃፀር ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በላይ መስራት እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህር እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ዋሴ አንተነህ በበኩላቸው የእለቱ አውደ ጥናት ዋና አላማ የአሳ ግብርናን በኢትዮጰያ ማስፋፋት በሚቻልበት ዙሪያ በIFAD እና WorldFish ድጋፍ የሚተገበረውን ፕሮጀክት በማስጀመር ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡ 

ዶ/ር ዋሴ ፕሮጀክቱ ኤርትራና ግብፅን እንደሚያካት ጠቁመው፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም በኢትዮጵያ ያለውን የውሃ ልማት በተመለከተ ማንኛውም እንቅስቃሴ እንዲያስፈፅም ተወከሎ እያስተባበረ ይገኛል ብለዋል፡፡

 

ምግብ ቤት አስተናጋጆች የደንበኞች አገልግሎትና አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በማገልገል ላይ ላሉ የምግብ ቤት ሰራተኞች በደንበኛ አገልግሎትና አያያዝ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ፡፡

በኮረና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉ ስልጠና ሰልጣኞች ርቀታቸዉን በጠበቀ መልኩና የፊትና አፍንጫ ጭንብል  በመጠቀም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ አጫጭር የስልጠና መርሃ ግብሮች መከናዎን ጀምረዋል ፡፡ የዚህ ስልጠና መርሃ ግብር አካል የሆነው በሁለት ቀናት የተካሄደው ስልጠና በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የተካሄደ ሲሆን በተማሪዎች አገልግሎት በኩል የምግብ ቤት አስተናጋጆች በተማሪ መስተንግዶና አገልግሎት አሰጣጥ ልይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡ በደንበኞች አገልግሎት ዙርያ በተካዴደው በዚህ ስልጠና ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 40 ሰልጣኞች ፤ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ 92 ሰልጣኞች እና ከሳይንስና ማሪታይም አካዳሚ ደግሞ 50 ሰልጣኞች በአጠቃላይ 182 የሚሆኑ የምግብ ቤት አስተናጋጆች ከቢዚነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በመጡ አሰልጣኞች ከ 19-22/01/2013 ዓ/ም ድረስ ስልጠናውን ወስደዋል፡፡ ሰልጣኞችም በወሰዱት ስልጠና መደሰታቸዉንና በሰለጠኑት አግባብም ለማግልገል መዘጋጀታቸዉን ገልጸዋል፡፡

በስልጠናዉ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ እንዳሉት ስልጠናው የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ የበለጠ ለማሻሻል የሚያስችል በመሆኑ ቀጣይነት እንደሚኖረው ጠቁመው ለዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ በስፋት የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አክለውም በአሁኑ ሰዓት ስልጠና የወሰዳችሁ ሁላችሁም ሰልጣኞች በሰለጠናችሁበት አግባብ ደንበኞቻችን የሆኑትን ተማሪዎቻችንን በተገቢዉ መንገድ እንድናስተናግድ አሳስባለሁ ሲሉ አቶ ወርቁ የስራ ትዕዛዝና መልዕክት በማስተላለፍ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ተማሪዎችን ለመቀበል የተደረገውን ቅድመ ዝግጅት ጎበኘ

በትዕግስት ዳዊት

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል በሁሉም ግቢዎች እያካሄደ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ዘርፈ ብዙ ስራ ጎብኝቷል፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለወራት ተቋርጦ የነበረውን የገፅ ለገፅ የመማር ማስተማር ሂደት የተማሪዎች ደህንነትና ጤናቸው በተጠበቀ መንገድ ይቀጥል ዘንድ በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ግቢዎች ሲከናወኑ የቆዩትን ዘርፈ ብዙ የዝግጅት ስራዎች ኃላፊዎቹ የጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ ዩኒቨርሲቲው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል በሚያስችል መልኩ ከተማሪዎች ማደሪያ፣ መማሪያ ክፍል፣ የምግብ አገልግሎት፣ የህንፃዎች እድሳት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አካቷል ፡፡

በጉብኝቱ አመራሮች ግቢዎቹ ያከናወኗቸውን በርካታ እንቅስቃሴዎች አድንቀው አንዳንድ መሻሻል ያለባቸውን ተግባራት ጠቁመዋል፡፡

በጉብኝቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University signs MoU with Karolinska Institutet, Sweden.

Please follow the link herewith for the details:

https://www.facebook.com/321567344711524/posts/1557223574479222/

Training of Trainers (TOT) on Audio-visual Techniques, Digitization of Modules and Applications of E-learning Platforms is delivered by a collaborative effort of Sasakawa Africa Associations (SAA)/SAFE and College of Agriculture and Environmental Sciences, Bahir Dar University.

By Mulugeta zeleke
The training which focused on training of twenty seven instructors for them to be able to be trainers themselves on Audio-visual Techniques, Digitization of Modules and Applications of E-learning was held on 22th and 23rd of September 2020.

Dr. Asaminew Tassew, Dean, College of Agriculture and Environmental Sciences, Bahir Dar University delivered welcoming speech. In his speech, he acknowledged SAA/SAFE and the commitment of the College’s management to provide full support and proactive collaboration in actively implementing the pilot project. He added, the College is ready to leverage resources, such as staff, space, and general infrastructure for the success of the pilot project.

Dr. Mercy Akeredelou from SAA/SAFE remarked that COVID 19 pandemic has impacted the whole world including academia. This was made evident to SAA from the rapid rural appraisal study conducted immediately after the spread of the pandemic in Africa. It was evident from the results of the study that all training institutions were under lock-down with students sent out of the University/Agricultural College campuses and training programs Also, the SAFE Demand driven curriculum content could not be delivered because its main mode of curriculum delivery was the face to face modality which required students’ physical presence in the classroom setting.

It was among the recommendations of this study that training institutions need to complement the face to face delivery with the e-learning mode of delivery so that lectures could go on even at difficult times like now and in the future. SAA, therefore, decided to implement a pilot E-learning project in two training institutions in Africa, one in francophone countries and one in Anglophone countries. College of Agriculture and Environmental Sciences, Bahir Dar University is selected to implement the pilot project from Anglophone African countries due to the commitment of the University’s Management and staff.

Apart from the equipment already delivered to set up the e-learning platform, a series of TOTs are planned to be implemented with the Staff of the College of Agriculture and Environmental Sciences of the University to equip them with the knowledge and skills required to operate the e-learning platform and one of it is the skills in e-learning platform management, audio visual techniques and photography. The training is believed to enable instructor trainees to develop modules in very attractive and interactive ways that will not be boredom for students. It is also hoped to make the module delivery on the e-learning platform to be close to real life situations. It has been understood that the participants of the training will master the key concepts very well so that they can be resource persons for other Universities and training institutions in Africa.

In his closing remarks, Dr. Asaminew extended his huge gratitude to SAA/SAFE for the provision of equipment for the e-learning platform and for organizing the TOT. He also acknowledged the active participation of the instructors in the TOT.

BDU (Social Science Faculty) wins Erasmus Plus project

The Erasmus Plus Project, funded by the EU, which the Faculty has applied for funding in collaboration with the Italian based Sant Anna School of Advanced Studies has been selected as one of the winners of the 2020 European Erasmus Plus Program. The Project involves staff and student exchange for Graduate students. Also, Masters and PhD students at the Department of Political Science and International Studies will have the opportunity to travel to Italy and spend a period of time for writing their research project under the mentorship of a Professor from Italian university.

This is the third European winning project which the Faculty has successfully bided in collaboration with other European partners and departments at BDU. Two other Projects, notably, on Law, Democratization and Media, and European Joint Doctorate Program on the SDGs, of which the Faculty took the leadership and coordinator role on the behalf of BDU, have also been funded and currently are in their implementation Phase.

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ እውቅና ሰጪ መሆን የሚያስችለውን ፍቃድ አገኘ፡፡

************************************************

እንኳን ደስ አላችሁ!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስልጠና አቅራቢዎች እውቅና ሰጪ ለመሆን ባመለከተው መሰረት የፌደራል ጤና ሚኒስቴር የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ኮሚቴ ያዘጋጃቸውን መስፈርቶች በሙሉ በማሟላት የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ (Continuing Professional Development – CPD) እውቅና ሰጪ መሆን የሚያስችለውን ፍቃድ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አግኝቷል፡፡

ለዚህ ስኬት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ አካላት በሙሉ ኮሌጁ ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

------------------------------------------

Bahir Dar University has become a certified CPD accreditor.

***********************************************

CONGRATULATIONS!

College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University is certified by Federal Ministry of Health as an accreditor of Continuing Professional Development (CPD).

The College would like to thank those who have worked hard for this success.

(From: College of Medicine and Health Sciences Fb page)

Bahir Dar University signs MoU with HOPE-Spina Bifida and Hydrocephalus
**********************************************************************
(From: College of Medicine and Health Sciences, BDU Facebook page)
Bahir Dar University, through its Tibebe Ghion Specialized Hospital (TGSH) of College of Medicine and Health Sciences, signs a memorandum of understanding with HOPE-Spina Bifida and Hydrocephalus (HOPE-SBH). The agreement underlies working jointly for better quality of life of Ethiopian children with spina bifida and/or hydrocephalus (SB/H) through integration of multidisciplinary care unit at TGSH, thereby fostering prevention and treatment of SB/H.
The two parties will cooperate to build the capacity of nurses on continence management, promote physiotherapy services to avoid manageable disability, and educate parents on home-based care for improved results of surgical treatments. Introducing better patient history recording mechanism in the hospital system, creating awareness on the consumption of folic acid reach nutrition or supplements for prevention of the occurrence of the condition, and improving the medical treatment by supplying needed scarce equipment and supplies are further areas of engagement for TGSH and HOPE-SBH. The agreement will be a huge step in realizing TGSH’s efforts of child health endeavors.
 
Prof. Yeshigeta Gelaw, Chief Executive Director of College of Medicine and Health Sciences at Bahir Dar University, and Beza Beshah, General Director of HOPE-SBH, signed the agreement representing their respective institutions.

Pages