Latest News

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ተስፋ የህፃናትና አረጋዊያን መርጃ ማእከልን ጎበኙ!!
 

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ተማሪዎች በተስፋ የማህበረሰብ አቀፍ ልማት ማህበር ማዕከል ጥር 25 በመገኘት የማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው በመጎብኘት ለማህበሩም የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል። በጉብኝቱም የማዕከሉን ሥራ አድንቀዋል፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ድህረ ምረቃ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዲን የሆኑት ዶ/ር ተከተል አብርሃም በዕለቱ ተገኝተው ከመምህራን፤ ከሰራተኞችና ከተማሪዎች ያሰባሰቡትን ጥሬ ገንዘብ እና የተለያዩ አልባሳት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ  ተወካይ በተገኙበት ለማህበሩ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ስለሽ ጌታቸው አስረክበዋል፡፡

ማህበሩ በ2000 ዓ.ም. ኪዳነ ምህረትና ባታ በተሰኙ እድሮች በ27 አባላት መነሻነት የተቋቋመ ሲሆን ባሁኑ ስዓት 100 ህፃናትን  የማስተማርና የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ከሁለት ሺ በላይ ለሚሆኑ እና ዕድሚያቸው ከ5 ዓመት በላይ ሆነው በደማቸው ኤች.አይ.ቪ ያለባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ቤት ለቤት በመሄድ ድጋፍ እንደሚሰጥ የማዕከሉ ኃላፊ በዕለቱ ገልጸዋል፡፡

 አቶ ስለሽ ጌታቸው አክለውም  ማህበሩ አገር በቀል እንደመሆኑም ከማህበሩ አባላት መዋጮ ባሻገር የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞችን የሚያካሂድ እንደሆነ ገልጸው ለታደሙትም የማህበሩ አባል በመሆን  የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በሙሉጉጃም አንዱዓለም

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ብሉ ናይል ውሃ ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ መንደር መመስረት (Climate Smart Villages/CSV/) የተሰኘው ፕሮጀክት በገጠር ልማት ላይ ለመስራት ስምምነቱን በዩኒቨርሲቲው ጥበብ ህንፃ አዳራሽ አሳወቀ፡፡

የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ዶ/ር የሻንበል መኩሪያው ሲሆኑ ፕሮጀክቱ ሊሰራ ያሰበው አኩሪ ተግባር በመሆኑ በወረቀት ላይ ያለው ተግባራዊ ሆኖ እንዲታይ አሳስበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ፕሮጀክቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የሰበሰባቸውን ተሞክሮዎች ያካተቱ የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የታለመው ንድፈ ሀሳብ ወደ ተግባር ተለውጦ ይታይ ዘንድ ከዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች ጀምሮ ሁሉም የሚመለከተው አካል ርብርብ ማድረግ እንደሚገው የፕሮጀክቱ ባለቤቶችና በሙያው የተካኑ ምሁራን ተናግረዋል፡፡

በእለቱም የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ከተለዩ በኋላ ተግባራዊ እንቅስቃሴውንም ተጨባጭ ለማድረግ የስራ ድርሻ ክፍፍል ተደርጓል፡፡

BDU signs Memorandum of Understanding with icepe, International Center for Insect Physiology and Ecology.
The occasion is held at the president's office with the presence of icipe delegates and University's officials. The signatories were the president of Bahir Dar University, Dr Firew Tegegne and Director General of icipe, Dr Segenet Kelemu.

In the ceremony, the distinguished scientist Dr Segenet Kelemu, Director of icipe, shared her experience about the importance of focusing on one thing and stand out in it to be a successful professional or an organization leader. She also underscored that it is always right to work hard on what one has and strive towards something great. Explaining her the remark, she said one cannot or shall not stay without a car while having a car is very important, but, for example, begin with a Volkswagen, and then steadily works hard to have a dream Mercedes car.

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዎን ሆስፒታል ያሰለጠናቸውን ስፔሻሊስት ሐኪሞች በክልሉ የተለያየ ሆስፒታሎች የማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ አሰማራ፡፡

ለአንድ አመት የሚቆየው ይህ የሐኪሞች ስምሪት በክልሉ በተለይም በባሕር ዳር አካባቢ በጥበበ ጊዎንና በፈለገ ሕይወት ሆስፒታሎች ያለውን የስራ ጫና ለመቀነስና ታካሚዎችም ርቀው ሳይጓዙ በአቅራቢያቸው አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የጥበበ ጊዎን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ተቀዳሚ ዳይሬክተር ፐሮፌሰር የሺጌታ ገላው ከመጋቢት 2009 ዓ.ም ጀምሮ ሃኪሞችን ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች የመላክ ተሞክሮ እንደነበረ ገልጠው ወደፊትም ይህን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡ 
በዚህ ዙር 13 የሚደርሱ ስፔሻሊስት ሐኪሞች የተሰማሩ ሲሆን ስድስት የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና እና ሰባት የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ሓኪሞች መሆናቸው ተገልጧል፡፡ እነዚህም ሐኪሞች ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመነጋገር የበለጠ አገልግሎት ወደሚሰጡበት ምዕ/ጎጃም፣ ምስ/ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋና አዊ ዞኖች የተመደቡ ናቸው፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የጤና ቢሮ ተወካይ አቶ አበበ ከህክምናውም ባሻገር ጥሩ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት በቆይታቸው ለውጥ እንዲያመጡ አደራ ብለዋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘም ለሃኪሞቹ ባስተላለፉት መልዕክት የሙያውን ክብር በመጠበቅ ማህበረሰባችን የሚጠብቀውን የህክምና አገልግሎት ከመልካም ሙያዊ ስነ ምግባር ጋር በማጣመር አርዓያነት ያለው ተግባር ፈጽመው በመመለስ የራሳቸውንም ሆነ የተቋማቸውን ስም በበጎ እንዲያስጠሩ በማሳሰብ የግል ተሞክሯቸውንም ለታዳሚው አጋርተዋል፡፡ የተለያዩ እንግዶች ምስጉን ሐኪሞችና የሐኪሞቹ አሰልጣኝ መምህራን በተገኙበት ስነ-ስርአት ላይ ከሐኪሞቹም የተለያዩ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በመጨረሻም ፕሬዚደንቱ የማስታወሻ ስጦታ ለተጓዥ ሀኪሞች አበርክተዋል፡፡

በኢትዮ- ሱዳን ህገ-ወጥ ፍልሰትን ለመከላከል ምክክር ተካሄደ

==================================

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር መካከል የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰት ህግን የተከተለ  እንዲሆን ለማድረግ በሁለቱ አጎራባች ሀገራት ሙሁራንና የሚመለከታቸው አካላት መካከል Better Migration Management Sudan/ Ethiopia በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር ምክክር ተካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገዳሪፍ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ኢብራሂም የሱፍ ለዘመናት የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት በሚያጠናክር መልኩ ፍልሰቱን ህጋዊ ለማድረግ የተጀመረው ፕሮጀክት አሁን ያለበት ደረጃ በመድረሱ የተሰማቸውን  ላቅ ያለ ደስታ ገልፀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ኢብራሂም አክለውም የገዳሪፍ ግዛት ዩኒቨርሲቲ የምርምር ተቋም በመሆኑ  በማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ  እየሰራ እንደሚገኝ አትተው ዩኒቨርሲቲአቸው   በኢትዮጵያ ከሚገኙ የድንበር አዋሳኝ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሰዎች ፍልሰት ዙሪያ በጥምረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በበኩላቸው  በምክክር መድረኩ ለተገኙ ተሳታፊዎች እና ባለ ድርሻ አካላት  እንኳን ወደ ባህር ዳር መጣችሁ ካሉ በኋላ ስለፍልሰት የሚካሄደው ምክክር በሰው ልጅ መገኛ በሆነችው ሀገር መሆኑ  ውይይቱን ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ አክለውም ፍልሰት ለሰው ልጅ ቀድሞ የነበረ እና ወደፊትም የሚኖር ተፈጥሯዊ ጉዳይ እንደሆነ ገልፀው ነገር ግን ህጋዊ መልክ የያዘ እና የዜጎችን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ባከበረ መንገድ መከናወን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ፍልሰት በህጋዊ ይዞታ እንዲኖረው ለማድረግ የምርምር ማዕከል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚደንቱ የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ያሉትን የጀርመን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት አመስግነዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከገዳሪፍ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጡ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ አርሶ አደሮች እና ወደ ገዳሪፍ ለስራ የሚሄዱ ኢትዮጽያዊያን ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

በትዕግስት ዳዊት

 

Bahir Dar University has signed an agreement with Lucy Academy to launch E-learning programs. The partnership agreement is believed to promote access to quality education in Africa and beyond.

 

For more information about the E-learning programs visit https://www.lucyacademy.com/

 

Learn anytime, anywhere!

 

Professor Mammo Muchie has made a speech on Ethiopianism in an aim to building solidarity among Ethiopians. He also gave a lecture on research and publication in another session.  

 

The speaker, Professor Mamo Muchie, who is by profession a professor of science, technology and innovation, raised an issue which appears far from his field of study. He happens to be more interested in history and particularly on Ethiopian history as a response to eternal love for his country. He said his love and obsession with knowing more about Ethiopia has grown high when he experienced how people in South African countries react to Ethiopians and Ethiopianism philosophy. This experience, he argues, informs him that Ethiopians don’t know themselves and how powerful their impact is at global level.

 

The professor said Ethiopianism as a philosophy and religion has emerged after the historical defeat of the white colonizers by Ethiopians who were determined to declare their freedom at any cost. Due to this, Ethiopians have become spiritual strength to all the colonized because of Adwa that recorded the defeat of the white colonizers by the fearless and high-spirited Ethiopians. The professor added, the victory of Adwa has electrified the spirit of resistance and the urge for emancipation among the colonized.

While putting the contribution of Ethiopian people to the world, he said that Ethiopia did not provide material help to the world but spiritual public good by defying colonial aggression. In conclusion to his talk, the professor urge the audience and the academic community to craft the ‘third Ethiopian manifesto’ that will help transcend Ethiopia to a new high in every parameter.

The professor in his second session talked about research and the tips that help academicians in publishing in highly rated reputable journals. The president of Bahir Dar University Dr. Firew Tegegn on the occasion handed professor Mammo a letter appointing him as an adjunct professor at the Institute of Technology, Bahir Dar University.

In the event, the university’s officials, teachers, students and other interested people both from the university and outside participated.

A speech on ‘Women in Ethiopian history’ Delivered

====================================

Playwright and Poet professor Fikre Tolossa delivered a public lecture on ‘Women’s contribution for the civilization of Ethiopia’ at Bahir Dar University, Peda campus.

In his talk, Professor Fikre highlighted the significant roles women played at different levels in governing Ethiopia. He argues that this fact signifies the level of mental civilization Ethiopians had which was markedly better than the situation today’s civilized nations have been in the past. He added gender was only an agenda in the twentieth century while females had enjoyed the highest positions in Ethiopia thousands of years ago. The professor used different historical documents to support his claim.

In the meantime, the professor talked a little about the current hostile situation in Ethiopia. As a reaction to the race based clashes happening in different parts of Ethiopia, the professor in his speech stressed the importance of unity in nation building, and he said it is the right time to try to push the reform in Ethiopia to reach to a level that ensures all rounded sustainable development. He mentioned the recently happening seemingly race based confrontations. He argued it is illogical for Ethiopians to fight on race basis as all the people are from the same race based on scientific evidences.

The conflict between different language speaking people in Ethiopia, he said, is analogous to a conflict that may happen between siblings who happened to be born in two different places which made them to be speakers of the respective languages. Such race based conflicts, according to the professor, are barbaric and what is even worse in Ethiopian context is that it happens between people from one race.

In the lecture, university’s officials, teachers, students and interested personalities from out of the university have participated.

ለአርሶ አደሮችና ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።
በትዕግስት ዳዊት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለ222 አርሶ አደሮች የቡና አመራረትና ድህረ ምርት አያያዝ የንድፈ ሀሳብ እንዲሁም የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል። የዚህን ስልጠና ማንዋል ያዘጋጁት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን
1. ዶ/ር ምናለሸዋ አጥላባቸው -የኬሚካዊ ይዘታቸውን(ጣዕማቸውን) ላይ 
2. ዶ/ር መልካሙ አለማየሁ - በድህረ ምርት እንዲሁም ምርት አያያዝ ላይ
3. ዶ/ር ዳንኤል አያሌው - ለቡና ልማት ተስማሚ የሆኑ ቦታዎችን መረጣና ካርታ ዝግጅት ላይ 
4. ዶ/ር ብዙአየሁ ቀሪሰው - የቡና ዘረመል ልየታው ላይ በመሳተፍ 
የስልጠናው ዋና ይዘት የቡና አመራረትና ድህረ ምርት አያያዝ ላይ ሲሆን ስልጠናው የአማራ ክልል የቡና ምርት፣ ጥራትና የገበያ ድርሻ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡ ስልጠናውን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያቀረበው ሲሆን አርሶ አደሮችና የዘርፉ ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት በአማራ ክልል ያሉ ቡና አምራቾች ከዘርፉ የሚጠቀሙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ያለመ ነው።
የስልጠናው ይዘት በዋናነት የሚያጠነጥነው የቡና ልማት አስፈላጊነትና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ፣ በአለም ላይ በሚታወቁ ዋና ዋና የቡን ዝርያዎች ላይ፣ ለቡና ተክል ልማት ተስማሚ ሁኔታዎችን የመለየት፣ የቡና ዘር አመራረጥና ዝግጅት፣ የቡና ችግኝ ጣቢያ አመሰራረት እና ችግኝ ዝግጅት፣ የቡና ችግኝ ተከላ እና ማሳ አዘገጃጀት፣ በቡና ማሳ ውስጥ የሚደረጉ አጠቃላይ እንክብካቤዎች እንዲሁም የቡና ምርት አሰባሰብ፣ ዝግጅትና ጥራት አጠባበቅ በሚሉት እና በመሳሰሉት ጭብጦች ላይ ያጠነጠኑ ነበሩ።
ዶ/ር መልካሙ አለማየሁ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምርት አያያዝ መምህር እና ተመራማሪ ሲሆኑ ለአርሶ አደሮችና ባለሙያዎች እንዳሉት በስልጠናው በአማራ ክልል የሚገኙ 222 ቡና አብቃይ አርሶአደሮች እና የዘርፉ ባለሙያወች የተሳተፉበት ሲሆን ሰልጣኞችም ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ላልሰለጠኑ አርሶ አደሮች እና የአካባቢያቸው ነዋሪዎች እንዲያሰለጥኑ በማሰብ ሲሆን ለሰልጣኞችም የስልጠናው ማንዋል ተሰጥቷቸው ብለዋል፡፡ ዶ/ር መልካሙ አክለውም ሰልጣኞች አሰልጣኞች እንዲሆኑ በማድረግ ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች ከዘርፉ ተጠቃሚ የሚሆኑበት እንዲሁም የአካባቢያቸው ቡና እንደየሀገሩ ስምና እንደጥራት አይነት/ብራንድ/ የምርት መለያ ስያሜ ተሰጥቶት ልክ እንደሌሎች የሀገራችን ክፍል ቡናዎች በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነትን እንዲያገኙና እንዲታወቁ ይሰራል ብለዋል ።
ስልጣኞች በጎ ፈቃደኛ በሆነች ሴት አርሶ አደር ጓሮ በሚገኙ ቡናዎች ላይ የተግባር ልምምድ ያደረጉ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ለድህረ ምርት አያያዝ የሚረዳ አልጋ በተግባር በመስራትና በማሳየት ሰልጣኞችም ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በተግባር ያዩትን በመተግበርና ተጠቃሚ በመሆን ኑሯቸውን እንዲቀይሩ ዶ/ር መልካሙ አሳስበዋል።
የስልጠናው ተሳታፊ አርሶ አደሮችም ስልጠናውን በመውሰዳቸው ጠቃሚ መረጃ በማግኘታቸው ምርታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም ከቡና ልማት ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል።

In an effort to produce qualified graduates, to conduct problem solving researches and to engage in various fruitful community based activities, collaborative works with other academic institutions and stakeholders is crucial. In this regard,Bahir Dar University is actively engaged in working collaboratively with professional organizations, national, continental and international institutions creating free scholarship and fellowship opportunities both for the teachers and students. Also, opportunities are opening up to our university community to participate in different projects that require collaborative effort of various institutions.
To further scale up the benefit gained from different collaborations, Bahir Dar University signed an agreement to be a member of the East African Agricultural Universities Forum. Being a member of this forum is believed to create many new opportunities for the university community. Therefore, concerned bodies in our university should work closely with the forum for a pronounced result.
External Relations and Partnership Directorate

Pages