Latest News

                             መቶ ሃያ ሶስተኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

የ2011 ዓ.ም. የአድዋ ድል በሁለት አበይት ክዋኔዎች ታስቦ ውሏል፡፡ አንደኛው  መነሻውን ጊዮርጊስ አደባባይ በማድረግ  እለቱን ለመዘከር የተደረገ የእግር ጉዞ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ  ይህን ታሪካዊ ቀን በማውሳት የተደረገው ትምህርታዊ ውይይት ነው፡፡

በበዓሉ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳኝነት አያሌው ታዳሚውን  የሚያነቃቃ ንግግር  አድርገዋል፡፡ አቶ ዳኝነት በንግግራቸው አልደፈር ባይ የአድዋ ጀግኖች አባቶቻችን ፍፁም በሆነ መንፈሳዊ ፅናት በዱር በገደል፣ በእግር በፈረሰ ተዋግተው ያቆዮዋትን ነፃ አገር፤ ወጣቱ ትውልድ ሊጠብቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ፡፡

በዩኒቨርሲቲው ባህል ማዕከል እና የታሪክ ቅርስ አስተዳደር የጋራ ትብብር በተደረገው ውይይት  ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች በዘመኑ ተንሰራፍቶ የነበረውን አፍሪካን እና ሌሎች የአለም ክፍሎችን የመቀራመጥ የአውሮፓዊያን የእብሪት አጀንዳ በሀይል መስበር እንደሚቻል ያሳዩበት አንፀባራቂ ድል መሆኑ በኩራት ተወስቷል፡፡

በእለቱ የዩኒቨርስቲው ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ እንደተናገሩት አድዋ ለመላው ኢትዮጵያውያን በነፃነት ለመቆማችን ምስክር ከመሆንም አልፎ ለጥቁር ህዝቦች ታላቅ ድልና  ዘመን ሳይሽረው በሁሉም ልብ ተፅፎ ከትወልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ የኩራት ምንጭ ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የአድዋ አንፀባራቂ ድል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች በቅኝ ግዛት ለነበሩት ሁሉ የነፃነት ተምሳሌት እንደሆነ ፕ/ር ሹመት ሲሻኝ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ከአድዋ የምንወስዳቸው ትምህርቶች እና የሴቶች ሚና በአድዋ የጦር ሜዳ ውሎ በሚሉ ርዕሶች ፅሁፎች ቀርበው በታዳሚዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የዛሬው ትውልድ ታሪክ ዘካሪ ብቻ ሳይሆን ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች ተጠቅሞ ያለፈውን፣ ዛሬን ብሎም ነገን  ባገናዘበ መልኩ ለአገሩ የተሻለ እድገት ለማምጣት እንዲተጋ የቃልኪዳን ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አርማ ከአባት አርበኞች ተረክቧል፡፡

 

ዩኒቨርሲቲው ለነባር የከፍተኛ አመራር አባላት እውቅና ሰጠ

---------------------------------------------------------

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ኃላፊነታቸውን በማጠናቀቃቸው ሙሉ በሙሉ ግልጽ በሆነ ውድድር በአዲስ የተተኩ ነባር የከፍተኛ አመራር አባላትን እውቅና ሰጠ፡፡

 

በዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በተዘጋጀውና በአዲስ የተተኩ አመራሮችን ለማመስገን በተዘጋጀው በዚህ የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ነባሮቹ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮችና የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሀላፊው በስራ ዘመናቸው ዩኒቨርሲቲውን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ በሚደረጉት ጥረቶች ውስጥ ላበረከቷቸው አስተዋጽኦዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ተቀብለዋል፡፡

 

ለነዚህ ነባር የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አባላት ምስጋና በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ነባሮቹ አመራሮች ለአዲሶቹ የስራ ርክክብ እና በሃላፊነት ዘመናቸው የጀመሯቸውን ስራዎች እንዲያስቀጥሉ አደራ በማለት የዩኒቨርሲቲውን የጥበብ ሰንደቅ ዓላማና ከእንጨት የተሰራ የጥበብ አርማ ዋንጫ (Wisdom Wooden Trophy) አበርክተውላቸዋል፡፡

 

ዝግጅቱን አስመልክተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ዩኒቨርሲቲው በሌሎች ተቋማት ከተወደሰውና ነጻና ግልጽ ውድድርን መርህ ባደረገ መልኩ አመራሮቹን ለመተካት እየተሰራ ከለው ውጤታማ ስራ ጎን ለጎን እየተካሄደ ያለው የሰራን ሰው የማመስገን ባህል በአርዓያነት የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰው ቀጥሎ ባሉት መካከለኛ አመራሮች ደረጃም ይህ ጉዳይ ተጠናክሮ መተግበር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡   

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሚመራ አንድ የልኡካን ቡድን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጎበኘ
------------------------------------------------------------------------------------
 
አርባ አምስት አባላት ያሉትና በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሚመራ አንድ የልኡካን ቡድን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአንድ ቀን ሰፊ ጉብኝት አደረገ፡፡
 
የጉብኝቱ ዋና አካል በሆነውና ልኡካን ቡድኑ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘና ሌሎች የከፍተኛ አመራር አካላት ጋር ባደረገው ውይይት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ከሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን እንደ ባሕር ዳር ካሉ ነባርና የመጀመሪያው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች በሶስቱ ዋና ዋና ሂደቶች በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በአመራር፣ በዓለማቀፍ አጋርነትና ሌሎች አበረታች አፈጻጸም በታየባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መውሰድ ስለሚችላቸው ልምዶች ሰፊ ውይይትና የልምድ ልውውጥ ተደርጓል፡፡
 
በሌላ በኩል ሁለቱ ተቋማት ወደፊት በተለያዩ ዘርፎች በጋራ መስራት ስለሚችሉባቸው ጉዳዮች በጥልቀት ተወያይተዋል፡፡
 
ልኡካን ቡድኑ ከሰአት በኋላ በነበረው ቆይታ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ዋና ዋና ዘርፎች በአካል በመገኘት በቅርቡ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመልካም ምሳሌ የተወሰደበትን የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ምርጫ ሂደት ጨምሮ በዋና ዋና ክፍሎች በተጨባጭ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በስፋት ጎብኝቷል፡፡

በሙሉጎጃም አንዱዓለም

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው Development of Micro grid Research Center in Bdu to Support USAID’S Power Program የተሰኘው ፕሮጀክት በጃካራንዳ ሆቴል ዓውደ-ጥናት፣ በወራሚት ቀበሌ ደግሞ የመስክ ጉብኝት አካሄደ፡፡

መርሃ- ግብሩ በይፋ መጀመሩን ያበሰሩት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ ለታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ዓውደ ጥናቱ  ፕሮጀክቱ ለሚያከናውናቸው የተለያዩ ተግባራት ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልፀው ፍሬያማ ውይይት እንዲሆን ተመኝዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ መምህርና የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ ዶ/ር በላቸው ባንትይርጋ በንግግራቸው እንደጠቀሱት ፕሮጀክቱ ታዳሽ ሀይሉችን በመጠቀም የተለያዩ ፋና ወጊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ገልፀው ለአብነትም በወራሚት ቀበሌ የሚገኘውን ት/ቤት በሶላር አማካኝነት የመብራት ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ  የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፍሮው ተገኘን ጨምሮ የተለያዩ ምሁራን የታደሙ ሲሆን በወራሚት ቀበሌ ሉማሜ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ የተሰራውን “የማክሮግሪድ” ሰርቶ ማሳያ ጣቢያ በመስክ ጉብኝቱ ለማየት ተችሏል፡፡

ዶ/ር ተስፋየ ሽፈራው ቦጋለ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ዛሬ የካቲት 19/2011 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ በቅርቡ ሲካሄድ በቆየው የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንትነት ምርጫ ተወዳዳሪ ከነበሩት መካከል የላቀ ውጤት ያስመዘገቡትን ዶ/ር ተስፋየ ሽፈራው ቦጋለን የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾመ፡፡

 

ዶ/ር ተስፋየ ከሌሎች አራት ዕጩዎች ጋር በተለያዩ መመዘኛዎች ተወዳድረው በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ በመሆናቸው ቦርዱ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ የወሰነ ሲሆን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ነገ የካቲት 20/ 2011 ዓ.ም በይፋ ስራ ይጀምራሉ፡፡

 

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን በውድድር በተመረጡ ኃላፊዎች እንዲያዙ ለማድረግ በጀመረው እንቅስቃሴ በቦርድ በተሰየመ መልማይ ኮሚቴ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ግልጽ በሆነና የተቋሙን ማህበረሰብ ባሳተፈ የምርጫ ሂደት የመረጠ ሲሆን ኮሚቴው የተለያዩ የም/ፕሬዚዳንት ቦታዎችንም በተመሳሳይ መንገድ በተለያዩ መመዘኛዎች እያወዳደረ ሲመድብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በዩኒቨርሲቲው የተሰየመ ሌላ መልማይ ኮሚቴ ሌሎች የአካዳሚክ ክፍሎች ኃላፊዎችን (ዲኖችና ዳይሬክተሮች) ሙሉ በሙሉ ግልጽ በሆነ ውድድር እየመደበ ይገኛል፡፡

አዲስ አባላትን ጨምሮ እንደገና የተዋቀረው አዲሱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ትናንት የካቲት 18/2011 ዓ.ም ስራ ጀመረ፡፡

ስራ አመራር ቦርዱ ስራ በጀመረበት በዚሁ ቀን ዩኒቨርሲቲው እስካሁን በሄደባቸው ርቀቶች ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በተለይ ተቋሙን ኢ-ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ የተሰሩ እንደተማሪዎች የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (SIMS)፣ የንብረት ግዥ አስተዳደር ስርዓት (PMS)፣ የተቋሙ የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ክፍል እያከናወናቸው ያሉ በኦንላይን ለመማር የሚያስችሉ አሰራሮችን (e-learning) ለመጀመር የተከናወኑ ስራዎችን ተመልክቷል፡፡

ቦርዱ በተጨማሪም ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጨምሮ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ግንባታዎችን፣ የምርምር ፕሮጀክቶችን፣ ወርክሾፖችንና ሌሎች በርካታ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ግቢዎቹ እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች ሲጎበኝ ውሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ ዛሬ በሁለተኛ ቀን ውሎው ቦርዱ የዩኒቨርሲቲውን የ2011 ዓ.ም መጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የገመገመና ሲካሄድ በቆየው የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ምርጫ ውጤት ላይ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ሌሎች ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይም ጥልቅ ውይይት በማካሄድና ውሳኔዎችን በማሳለፍ የስራ ዘመኑን የመጀመሪያ ስብሰባ አጠናቋል፡፡

ትምህርት ክፍሉ ለመጀመሪ ጊዜ የሚያስመርቃቸው የ3ኛ ዲግሪ እጩ ተመራቂዎች ተቋቁሞ
*******************************************************************

በሙሉጎጃም አንዱዓለም
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ በኢትዮጲያ ቋንቋዎችና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ የሆነውን በ3ኛ ዲግሪ የመጨረሻውን የጥናታዊ ጽሁፍ ተቋቁሞ ሀሙስ የካቲት 14፣2011 ዓ.ም. በደመቀ ሁኔታ አካሄደ፡፡

የፋኩልቲው አንጋፋ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ማረው ዓለሙ ፕሮግራሙን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት አገር በቀል በሆነው የአማርኛ ቋንቋ በ3ኛ ዲግሪ ደረጃ መሰራቱ ዋና ዓላማው ቋንቋውን ለማሳደግና ትምህርቱን ለማስፋፋት እንዲሁም የጥናት ዉጤቱ ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ግብዓት ለማድረግ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ዶ/ር ማረው አክለውም እርሳቸው በሚመሩት አማርኛን ማስተማር የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም የሚጻፉ ጥናታዊ ጹህፎች ደረጃቸውንና ጥራታቸውን የጠበቁ ሆነው እንዲቀጥሉ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

የፋኩልቲው ዲን ዶ/ር ዳዊት አሞኘም ለተመዘገበው ስኬት በሂደቱ ውስጥ የተሳተፉትን ሁሉንም በፋኩልቲው ስም አመስግነው የእለቱን አቅራቢ እንኳን ደስ አለህ በማለት በሶስት አመት ከመንፈቅ በሆነ ጊዜ ብቻ ፕሮግራሙን ለማጠናቀቅ መቻሉ በራሱ ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ምናልባትም በዚህ አጭር ጊዜ ሲጠናቀቅ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ የመጀመሪያው ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የአሁኑ እጩ ተመራቂዎች በፋኩልቲው ስር የኢትዮጲያ ቋንቋዎችና ስነ-ፅሁፍ መምህር የሆኑት አቶ ማስተዋል ውበቱ እና የዓርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ ሐይላኣይ ተስፋይ ሲሆኑ በዕለቱ ጥናታቸውን ያቀረቡት አቶ ማስተዋል የጥናታቸው ርዕስ “ የትብብር ብልሀታዊ ማንበብ ዘዴ” የተሰኘ ነው፡፡ ለጥናቱ መነሻ የሆነው ከ1-8 ክፍል ያሉ ተማሪዎች የማንበብ ልምዳቸውና ተነሳሽነታቸው አናሳ መሆኑንን የሚጠቁሙ ጥናቶች መኖራቸው እና የ1ለ5 የትብብር ብልሀትም በአግባቡ አለመተግበሩ እንደሆነ አቅራቢው ጠቁመው ጥናታቸውም የተጠቀሰውን የንባብ ብልሀት ለመፈተሸ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እጩ ተመራቂው ስለ ስለጥናታቸው ለሰላሳ ደቂቃ ያህል ካቀረቡ በኋላ ከውጭ እና ከውስጥ ለመጡ ገምጋሚዎች እንዲሁም ከታዳሚው ለተነሱ አጠቃላይ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም የእለቱ ሊቀመንበር የክፍቱ ተቋቁሞ እንደተጠናቀቀ ገልጸው ተቋቁሞው ከ15 ደቂቃ ረፍት በኋላ በዝግ እንደሚቀጥል በማመልከት ለነበረው ጊዜ ታዳሚውን አመስግነዋል፡፡

              በትዕግስት ዳዊት

የተቀናጀ የዘር ሴክተር ልማት በኢትዮጵያ/ ISSD/ የግምገማ እና የልምድ ልውውጥ አውደ ጥናቱን ከየካቲት 11፣ 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በባህር ዳር አካሄደ፡፡

 

ዶ/ር ደረጀ አያሌው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ሳይንቲፊክ አስተባባሪ (ISSD Project Amhara Unit Scientific Coordinator) በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንዳሉት የአውደ ጥናቱ ዋና አላማ በአመቱ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገምና ስራዎችን ለማስቀጠል ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ለስኬታማ አፈፃፀም ምን መደረግ እንዳለበት ለመምከር እንዲሁም በተመዘገቡት ስኬታማ ተሞክሮዎች ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ  አውደ ጥናት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

አክለውም የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ በ5 ቦታዎች ማለትም ከኦሮሚያ ዘር ኢንተርፕራይዝ ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ፣ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን እየሰራ ያለ ፕሮጀክት እንደሆነ ገልፀው ሁሉም የፕሮጀክቱ ሰራተኞች በየአመቱ አንድ ቦታ ላይ በመሰባሰብ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና ችግሮችን በማረሞ በቀጣይ የዘር ሴክተሩን ለማሳደግ የሚሰራበት ነው ብለዋል።

 

የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ጥሬ ገንዘብን በቀጥታ ለአጋር አካላት የማይሰጥ ይልቁንም አርሶ አደሮችን በማደራጀት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት መሬታቸውን ክላስተር በማድረግ ክህሎትና አመለካከት በማምጣት  ደረጃውን የጠበቀ ዘር ማምረት እንዲቻል ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በተጨማሪም እንደ አስተባባሪው ገለፃ ፕሮጀክቱ የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ ስልጠና ይሰጣል ብለዋል።

 

ዶ/ር ደረጀ እንዳሉት ፕሮጀክቱ በዋናነት ጥራት ያለው፣ አርሶ አደሩ የመረጠውና በምርምር የተገኘ ዘርን ወቅቱን ጠብቆ በተፈለገው መጠን ለአርሶ አደሩ እንዲደርስና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘዬ ለመቀየርና ኢኮኖሚን ለማሳደግ አልሞ ይሰራል ብለዋል። የልምድ ልውውጡም የት ላይ እንዳሉ፣ ሌሎቹ  ምን የተሻለ ስራ እንደሰሩ የሚታይበት እና ለተሸለ ስራ ስንቅ የሚሰነቅበት እንደሆነ ዶ/ር ደረጀ ተናግረዋል። እነዚህን መልካም ተሞክሮዎችን ስንወስድ በመላ ሀገሪቱ ሊኖር የሚችለው የዘር ጥራት ዝውውር ያደርጋል ብለዋል።

 

ዶ/ር ደረጀ ዘር ላይ መስራት ውጤታማ ስለሚያደርግ አርሶ አደሮች ያመረቱትን ምርት ለገበያ እንዲያደርሱ ያግዝ ዘንድ የተለያዩ የዘር ማበጠሪያ ማሽኖች በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ተገዝተው ለአምራች ገበሬው ተሰጥቷል። ይሁን እንጂ ማሽኖቹ በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት አገልግሎት ላይ እንዳልዋሉ ጠቁመዋል። አርሶ አደሮች እንዲቀየሩና እንዲስተካከሉ ግብርናንም ለማሳደግና ለማዘመን ማሽኖቹ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለባቸው የኤሌክትሪክ ችግር እንዲቀረፍ ጥሪ አቅርበዋል።

 

ዶ/ር አምሳሉ አያና የISSD ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት የዘር ስርዓቱን ለማሻሻል የዘር እሴት ሰንሰለቱ ቀልጣፋ መሆን አለበት ብለው  ከዝርያ መረጣ ጀምሮ ያለውን ሰንሰለት በመቀነስ ብሎም ቀልጣፋ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለማምጣት እንዲቻል እየተሰራ ነው ባለዋል፡፡ ለዚህ ውጤታማነት ከነሀሴ 2001 ዓ/ም ጀምሮ ከአራት ክልሎች ጋር ISSD በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

 

This public lecture is part of the lecture series Perspectives on Positive Peace entitled as ‘Data Driven Democracy – How platforms provide opportunities for participation, community organizing, public engagement and business development’ was undertaken by The Department of Political Science and International Studies of Social Sciences Faculty, Bahir Dar University in collaboration with the Friedrich-Ebert-Stiftung.

 

The head of the Department of Political Science and International Studies, Mr Gebretsadik Awgichew, in his welcoming speech, said that the major objective of the gathering is to talk about the potentials of data for democratic systems. Data driven forms of civic participation increasingly become the modern approach to engage with citizens. Civic participation is considered a cornerstone of democracy. This form of data-driven democracy and civic participation promotes an understanding of democratization processes and democratic systems.

 

Mr. Gebeyehu Mengesha, the Vice Dean for Postgraduate, Research and Community Service of Social Science Faculty, in his opening remarks, said that Relevant data is used to create strong strategies, policies, programs and future plans which will be realistic. He added data can be used for performance evaluation, monitoring, controlling and auditing for institutions and organizations which are very important for democratic value creation and for suggesting new ways of doing things.

 

The speaker Mr Henrik Flor focused on the importance of data in the formation of a system that functions healthily and strong. He said obtaining data is a powerful tool for transparency and accountability of a certain functioning system, be it a state or an organization. Underscoring the indispensable role of data, the speaker argues that truthful data can help in bringing local and national democracy and in realizing proper utilization of public finance and budgeting. Moreover, such data can also play a pivotal role in process of policy making.

 

Mr Flor concludes that the future of our modern world depends on the timely and effective use of data. He reminds the scholarly community once again to be sensitive in building their claims with relevant and suffice data implicating the otherwise use might not serve the demand of the modern era.

 

 

BDU STEM Center Started the 4th STEM-Girls Camp Program

The Bahir Dar University STEM Center started its STEM-Girls camp program which is running from February 3 to 10, 2019. The training was officially opened by Dr Zewdu Emiru, the Vice President for Information and Strategic Communications of the University. The training is taking place in the Peda campus where dormitories and training facilities for the program are provided. 73 female students from grades 9 to 12 of all public and private high schools found in Bahir Dar City are attending the training. It is managed by 15 teaching staff pooled from all STEM departments of the university. The training includes STEM lab practices, life skill, team-work, field exercises, games with funny approaches of science, site visits related to STEM, a visit to Bahir Dar Maritime Academy and Bahir Dar University College of agriculture and environmental sciences (Nursery site, animal farm …). The STEM-Girls camp is an annual program of the BDU STEM center conducted during the semester break of schools. This year camping program is as usual is prepared in a competition form. Four Groups are competing and they are named after the well-known Ethiopian female scientists Prof Yalemtsehay Mekonnen, Prof Sosina M. Haile, Dr Segenet Kelemu and Dr Debrework Zewdie. The grouping is to inspire our future female scientists to follow the tracks of their fellow female senior professors. The camp will have competition throughout the whole week and finally the winner group will receive the winners’ cup at the end of the weeklong program.

 

Pages