Latest News

                               1. Dessie Salilew Wondim (PhD)  

  1. Workneh Ayalew Kebede (PhD)

 

  1. Aynalem Haile Gebele (PhD)  

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ስልጠና ፕሮግራም መድረክ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ተጀመረ

በሙሉጎጃም አንዱዓለም

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ  ሕንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረው ይህ ስልጠና ከየካቲት 4 እስከ 06/2013 የሚቆይ ሲሆን   የከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት  ሀገሪቱ  የምትፈልገውን  የሰው  ኀይል በብዛትና በጥራት በማፍራት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በአግባቡ ተግባራዊ የሚያደርጉ  አመራሮችን ለማውጣት ከታለመው ተከታታይ ስልጠና አንዱ መሆኑን  የሳይንስና  ከፍተኛ  ትምህርት  ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶክተር) ጠቁመዋል፡፡

 

ስልጠናውን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ለታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የከፈቱት ሲሆን "ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በወፍ በረር" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ዶከመንተሪ መረጃ በማቅረብ ዩኒቨርሲቲው ያከናወናቸውንና ሌሎች በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን በሰፊው አስተዋውቀዋል፡፡

 

ዩኒቨርሲቲው በፕሮጀክቶች አማካኝነት የበርካታ ማህበረሰብን ችግር እየፈታ እንደሆነና ቴክኖሎጂ ነክ ፈጠራዎችን በስፋት በመስራት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የሐኪሞችን ሙሉ የመከላከያ አልባሳት በማምረት ያላሰለሰ ጥረት ማድረጉን ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ  ግቢዎች  ከመማር  ማስተማር፣  ምርምርና  ማህበረሰብ  አግልግሎት  ተግባሮቹ  በተጨማሪ  ለጀማሪ  ዩኒቨርሲቲዎች  የዕውቀትና  የቴክኖሎጂ  ሽግግር እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

 

በዩኒቨርሲቲው ምሁራን የተሰራ "PALM City Bahire ደar" የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ በታዳሚዎች ፊት በይፋ ስራ ላይ እንዲውል ተደርጎ ለእንግዶች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እንደሚሰጥ የፈጠራው ባለቤቶች አስረድተዋል፡፡

 

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ያቀረቡት ገለፃ ይበል የሚያሰኝና ለሌሎች ተቋማት ጥሩ ተሞክሮ እንደሆነ ጠቁመው የስልጠናው ዋና ዓላማ የሳይንስና  ከፍተኛ  ትምህርት  ሚኒስቴር  በቀጣይ  10  ዓመታት ከተለመደው አሠራር በመውጣት በክህሎትና በእውቀት የዳበሩ አመራሮችን ለማፍራት  ታልሞ መሆኑን ተናግረዋል።

 

ዩኒቨርሲቲዎች ባለፉት ጊዚያት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን  አውስተው ይህ ተሞክሮም በቀጣይ በሚሠራው ሥራ ልምድ የሚወሰድበት  መሆኑን  አስገንዝበዋል፡፡ ሚንስትሩ አክለውም ውይይቱ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ ከወረቀት በዘለለ ውይይት ላይ ያተኮረና በቅንጅት ስራ የዳበረ ብሎም አንዱ ተቋም ከሌላው ጋር ተናቦ የተሻለ ውጤት የሚመዘገብበት እንዲሆን አሳስበዋል፡፡

 

 

በኢትዮጽያ እና ሱዳን ግንኙነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ሲሆን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፣ከወሎ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከሱዳን ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ሙሁራን በኢትዮጽያ እና ሱዳን የቀድሞ ግንኙነት እንዲሁም ወደፊት ስለሚኖረው ጥምረት ትኩረቱን ያደረገ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን እንደሚያቀርቡ ተነግሯል፡፡

 

A discussion focusing on Ethio-Sudanese relations is underway at Bahir Dar University, Ethiopia.

Scholars from Bahir Dar University, Wollo University and Sudanese Universities will be presenting their research papers on the previous relations between the two countries, Ethiopia and Sudan.  Also, papers that focus on the future relationship of the two neighboring counties will be presented. The discussion is expected to continue tomorrow.

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሠለጠናቸውን 5117 ተማሪዎች አስመረቀ

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መመረቅ የነበረባቸው እና በኮረና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት መቋረጡን ተከትሎ የዘገዩ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ 4203፣ በሁለተኛ ዲግሪ 759፣ በሦስተኛ ዲግሪ 10፣ በስፔሻሊቲ 40፣ በፒጂዲቲ ቅድመ ምረቃ 105 በአጠቃላይ 1623 ሴት 3494 ወንድ ተማሪዎችን በድምሩ 5117 ተማሪዎችን ጥር 29/5/2013 ዓ.ም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በክብር እንግድነት በተገኙበት አስመርቋል።

 

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት “የዘንድሮ ተማራቂዎችን እንደተማሪ በርካታ መሰናክሎችን አልፈው ለዛሬው ቀን በመብቃታቸው "ከመወርቅ" በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ችግሮች በመከራ ጊዜ እንደ ወርቅ ነጥራችሁ በመውጣታችሁና ለዚህ ታሪካዊ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡” ዶ/ር ፍሬው አክለወም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንዲሆንና በሀገራችን ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ግምባር ቀደም እንዲሆን ላገዙት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ ላሉ የወጣት አደረጃጀቶችና ለሌሎች አጋር ተቋማትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

 

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተመራቂዎች ዓለምን እየፈተነ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ ውስብስብ ችግሮችን አልፈው መመረቅ መቻላቸው ታሪካዊ ተመራቂዎች መሆናቸውን አውስተው ተመራቂ ተማሪዎች ሀገርና ቤተሰብ የጣለባቸውን አደራ በአግባቡ እንዲወጡ በሰለጠኑበት የትምህርት መስክ ጠንክረው በመስራት ሀገራቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ተመራቂ ተማሪዎች ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን ለሀገሬ ምን አደረኩላት ብሎ ራስን መጠየቅ እና በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙትን ጥልቅ ዕውቀት ተጠቅመው በኮረና ቫይረስ ወረርሽ የቀዘቀዘውን ኢኮኖሚ እንዲሻሻል በማገዝ በሀገር ግንባታ ላይ የበኩላችውን አስተዋፆ ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለባሕር ዳር ከተማ ብሎም ለክልሉ እንደ ዓይን ብሌን የሚታይ ግዙፍ የዕውቀት ማዕከል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

 

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በመመረቂያ ፕሮጀክቶች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት እና የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የወርቅ ዋንጫ ተሸልመዋል፡፡

 

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ፣የባሕር ዳር ዩኒቨረሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ፣ የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋም ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

 

የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ባማረው እና በተዋበው የዩኒቨርሲቲው ስታዲየም በፖሊስ ማርሽ ባንድ በቀረበ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መዝሙር እና በሙሉ ዓለም የባህል የሙዚቃ ባንድ በቀረቡ የተለያዩ ባህላዊ ውዝዋዜዎች እና ዘመናዊ ሙዚቃዎች በመታጀብ ደምቆ ውሏል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምረቃ በዓል የተሳካ እንዲሆን ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር ዉይይት ተካሄደ

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ የተሳካ ሆኖ ይጠናቀቅ ዘንድ  ከክልሉ የፀጥታ ኃይል፣ ከክልሉ አድማ ብተና፣ ከትራፊክ ፓሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ኃይል፣ ከክልሉ ፖሊስ፣ ከከተማዉ ፓሊስ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ዉይይት አካሂዷል። ዉይይቱን የመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኑ ገድፍ ምረቃዉ የተሳካ እንዲሆን እንደከዚህ ቀደሙ የፀጥታ መዋቅሩ በመቀናጅት ውጤታማ ሥራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል። 

በዉይይቱ የዩኒቨርሲቲዉ ፀጥታና ደህንነት ኃላፊ ኢንስፔክተር ሀብታሙ መለሰ የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዉ ሰፊ ዉይይት ተካሂዷል፡፡  በቀረበው ሃሳብ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ  ምረቃዉ ከዋዜማው  ጀምሮ የተሳካ እንዲሆን የራሳቸዉን የፀጥታ ኦፕሬሽን አዘጋጅተዉ ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች በቅንጂትና በተገቢው የኃላፊነት መንፈስ እንደሚንቀሳቀሱ መግባባት ላይ ተደርሷል ።

Alliance for Research, Innovation and Education in Ethiopia/AfRIE/ delivers high level training to staff

Alliance for Research, Innovation and Education in Ethiopia successfully completed three day long virtual training on grant writing for more than 75 professionals/staff in Bahir Dar and Debre Markos Universities.

AfRIE has been working with Bahir Dar University in capacity building of its faculty in areas of education, research, supervision and other project focused areas from which the current training can be mentioned as just an instance.

AfRIE is created by a group of volunteer Ethiopian and other national professionals based in the US with the aim to share expertise and experiences to Ethiopian professionals and institutions. AfRIE aims to support Ethiopian universities and research centers to improve their standards in education, research, innovation, and development capabilities.

 

Bahir Dar University would like to appreciate the contribution of AfRIE which is working tirelessly to contribute its share to improving the lives of Ethiopians, the present and the future.

Pages