Congratulations!!
Bahir Dar University EiTEX receives a certificate of recognition
Africa leather and leather products institute’s (ALLPI) Awards Ethiopian Institute of textile and fashion technology
By recognizing the institute’s contribution to the leather sector development in Ethiopia through training , research and development and collaborating with ALLPI to transform the leather sector’s Small and mid-size enterprises (SMEs) to become innovative, competitive and productive through applicable research and development. In addition to this, the institute wins the 2020 ALLPI Executive Director’s Award of 2020 in the 14th ALLPI Annual Forum carried out in Hawasa from 16-18th December 2020.
እንኳን ደስ አለን!
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ የቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የዕውቅና ሽልማት አገኘ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ የቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እድገት ላበረከተው አስተዋፅኦ በ African Leather and Leather Products Institute/ALPPI የእውቅና የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡
ተቋሙ ይህን እውቅና ያገኘው በኢትዮጵያ የቆዳ ሥራ እድገት እንዲያሳይ በስልጠና፣ በጥናትና ምርምርና እድገት፣ ከ ALPPI ጋር በትብብር በመስራት የኢትዮጵያ የቆዳው ዘርፍ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመለወጥ ፈጣሪ፣ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ተግባራዊ የምርምርና የዕድገት ሥራዎች እንዲሰሩ በማስቻሉ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ለ14ኛ ጊዜ ከታህሳስ 7-9/ 2013ዓ.ም ሀዋሳ በተካሄደው አመታዊ የምክክር ጉባኤ ኢንስቲትዩታችን የ2020 African Leather and Leather Products Institute/ALPPI Executive Director’s Award ተሸላሚ ሆኗል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም የኢትዮጵያ የቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያሰመዘገበውን እውቅና እያደነቀ ለተቋሙ ሰራተኞችና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡
ይህን የመሰሉ የእውቅና ሽልማቶች በሁሉም ዘርፎች እንዲደገሙ በማድረግ ልዩነት ፈጣሪ በመሆን የዩኒቨርሲቲያችንን ራዕይ ለማሳካት የበኩላችን እንወጣ!!