Latest News

Six BiT-BDU graduates, who won the SSI-Agri Hackathon of 2021, have developed two ICT systems that enable the advancement of small scale irrigation.

News article in full: https://www.facebook.com/bitpoly/posts/1472923713108794

“የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ትምህርትና ፖለቲካ መለያየት አለባቸው”

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ባዳዩ (ታህሣሥ 02/2014ዓ.ም)

የኢ.ፌ.ድ.ሪ.ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለመጀመሪያ ጊዜ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ባካሄዱት የውይይት መድረክ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ትምህርትና ፖለቲካ መለያየት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ለሚኒስትሩ እና ተሳታፊ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደተናገሩት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ከሚገኙ ቀዳሚ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያው የምርምር ዩኒቨርሲቲ መሆኑን አውስተው በሃገራዊ እና አህጉራዊች ችግሮች ላይ ምላሽ የሚሰጡ ምርምሮችን በመስራትና ምሁራንን በማፍራት እየተጋ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አክለውም ትምህርት ሚኒስትሩ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ለማነጋገር በመምጣታቸው አመስግነዋል፡፡

 

በምክክሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኢታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኢታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትምህርት ጥራትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቁዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

በመድረኩ የትምህርት ጥራትን በአምስት ዓመታት ውስጥ የተሻለ ለማድረግ መሠራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተመከረ ሲሆን ከመምህራን ደምወዝና ጥቅማጥቅም፣ ከትምህርት ፖሊሲና ትምህርት ተቋማት መሪዎች አቅም ጋር በተያያዘ ሃገራዊ ጉዳዮች ተነስተው ተመክሮባቸዋል፡፡

 

በዚህም ለትምህርት ዘርፉ መውደቅ ለአገራዊ ችግር መንስኤ መሆኑ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ከችግሩ ለመውጣት ምን መደረግ እንዳለበት እና ሁሉም የትምህርት ተቋማት በየደረጃው ከገቡበት ችግር እንዲወጡ የሚያችል ምክረ ሃሳብ ተሰንዝሯል፡፡

 

ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል የመምህራንና የትምህርት ማህበረሰቡ ተሳትፎ ቀጣይነት ያለው ሃገራዊ ምክክርና የፖሊሲ ማሻሻያ የግብዓት ሃሳቦችን በመለገስ ረገድ ትኩረት እንደሚሰጠው በመግለጽ የመምህራን ጥቅማጥቅምንና ተያያዥ ጉዳዮችን ማስተካከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚመክሩበት ተናግረዋል፡፡

 

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሐኪሞች ቡድን በመላክ በነፋስ መዉጫ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1893170847551158

 

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሐኪሞች ቡድን በመላክ በነፋስ መዉጫ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1893170847551158

 

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለወረታ የሕክምና ማገገሚያ ማዕከል የመድሓኒትና ግብዓት ድጋፍ አደረገ፡፡

https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1892557767612466

 

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ የሐኪሞች ቡድን ለመቄት ሆስፒታል ላከ።

https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1892564300945146

ሰወች ለሰዎች(people to people) የተሰኘ ግብር ሰናይ ድርጅት ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና እቃዎች እርዳታ ሰጠ።

https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1892574707610772

የስንቅ ዝግጅት ስራ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠናክሮ ቀጥሏል
**************************************
ባዳዩ (ሕዳር 29/2014) ፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ስንቅ በማዘጋጀት የተለመደ ደጀንነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
 
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ለህልውና ዘመቻው በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በተንቀሳቃሽ ህክምና አገልግሎት፣ ደም በመለገስ፣ በቀጥታ ዘመቻው ላይ በመሳተፍ፣ የደረሱ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በመስጠት የደጀንነት ኃላፊነታቸውን በብቃት እየተወጡ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
 
የዘገባ ቡዱኑ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እና የማዕከላዊ ግቢ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በህልውና ዘመቻው ለሚዋደቁ ጥምር የፀጥታ ሀይሎችና ተፈናቃይ ወገኖቻችን ስንቅ የሚሆን ዳቦ ቆሎ በማዘጋጀት በድጋሜ አለኝታነታቸውን አሳይተዋል፡፡
 
የስንቅ ዝግጅት ካሁን በፊት በተለያዩ ግቢዎች ማለትም በዋናው ግቢ፣ በዘንዘልማ ግቢ፣ በሰላም ግቢ፣ በግሸ አባይ ግቢ እና በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሚችሉት ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በስንቅ ዝግጅቱ ሲሳተፉ ያገኘናቸው ሰራተኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በሙሉጌታ ዘለቀ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለማይካድራ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች ድጋፍ አደረገ

ባዳዩ (ህዳር 30/ 2013ዓ/ም)፡-

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ት/ቤትና መሬት አስተዳደር ተቋም ለማይካድራ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች የአልባሳት፣የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የተቋሙ ባልደረቦች ወደ አካባቢው ለጥናት በሄዱበት ጊዜ ወደ 40 የሚደርሱ በማይካድራዉ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውንና አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በመገንዘብ የተቋሙን ሀብት እና ሰራተኞችን በማስተባበር ወደ 259,676 ብር የሚያወጣ የምግብ፣ የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለ40 የጉዳቱ ሰለባዎች ተበርክቶላቸዋል፡፡

በማይካድራ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የሕግ ትምህርት ቤት ዲንና የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዩኒቨርሲቲዉ ያደረገዉ ድጋፍ ከዘር ጭፈጨፋ የተረፉትን ወገኖች ከጎናችሁ ነን የሚለዉን መልዕክት ለማስተላለፍና ችግራቸው በዘላቂነት እስከሚቀረፍ ድረስ የእለት ችግራቸውን ለማስታገሰ የተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊዎች አያይዘዉም ዩኒቨርሲቲው በሀገራዊ የሕልውና ዘመቻው ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰዉ ወራሪዉ ሀይል የሰብአዊ መብት ጥሰት በፈፀመባቸዉ አካባቢዎች በመገኘት የደረሰውን ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት በማጥናት ጉዳቱን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማጋለጥ አንደኛዉ ተግባር እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

እርዳታውን የተረከቡት የማይካድራ ጥቃት ሰለባዎች ማህበር ሊቀመንበር አቶ ግርማይ እንደገለጹት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማይካድራ የጉዳት ሰለባዎችን አስታውሶ ለችግራችን በመድረስ ይህንን ትልቅ ድጋፍና እገዛ ስላደረገላቸዉ በማሕበሩ ስም ከፍ ያለ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡  

ተጎጂዎች ከደረሰባቸዉ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና አዕምሯዊ ጉዳት በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዉ የሚገኙ በመሆናቸው ረጂ ተቋማት፣ የዲያስፖራው ማህበረሰብ፣ ባለሃብቶች እና ፍላጎት ያለዉ አካል ሁሉ የጉዳቱን ሰለባዎች ከችግራቸዉ ወጥተው በዘላቂነት ራሳቸውን ችለዉ እንዲቋቋሙ ለማድረግ አፋጣኝ የሆነ ድጋፍና እገዛ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ የማሕበሩ ሊቀመንበር ገልፀዋል፡፡

 ከገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ እስከ አሁን ድረስ በቂ ህክምና ያላገኙ፣ከስነ-ልቦና ጉዳታቸዉ ያላገገሙ፣ ከአዕምሯዊ ስቃይ ያልተላቀቁ ተጎጅዎች ያሉ በመሆናቸዉ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ተገቢው ህክምና በአፋጣኝ እንዲደረግላቸዉ የጉዳቱ ሰለባዎች የጠየቁ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዉ በሚገኙበት ወቅት ይህንን ድጋፍ ስላደረገላቸዉ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሀኪሞችን ቡድን ወደ ጋሸና ግንባር ላከ
=====================================================================
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ ስፔሻሊስቶችን የያዘ የህክምና ቡድን ጋሸና ግንባር ወደሚገኙ የማገገሚያ ማዕከላት ላከ፡፡ የህክምና ቡድኑ በጋሸና ግንባር የትግሬ ወራሪ ቡድን በፈጠረው ጦርነት ምክንያት የቆሰሉና ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ለማከም ተሰማርተዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር የሽጌታ ገላው እንደገለጹት በጋሸና ግንባር ህክምና ለመስጠት የአጠቃላይ ቀዶ ህክምና፤ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስቶች፤ አንስቴዥያን፤ የጥርስ እና የስነ-አዕምሮ ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ያካተተ ቡድን ተሰማርቷል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እስከ አሁን ድረስ ከ34 በላይ አባላትን የያዘ የሀኪሞች ቡድን ወደ ጋሸና ግንባር በተለያዩ ሁለት ቦታዎች የላከና ዘመቻው ለሁለት ሳምንት የሚቆይ መሆኑን ፕሮፌሰር የሽጌታ ገላው ተናግረዋል፡፡

‹‹የአዕምሮ ጤና ህክምና እንደጨው ሁሉም ቦታ መኖር አለበት››(ፕሮፌሰር ፈንቴ አምባው)

*******************************************************************

በአማራ ክልል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ምሁራን በጦርነቱ ምክንያት  የተፈጠረውን የአዕምሮ ጤና፤ ስነ-ልቦናዊ፤ማህበራዊና አካላዊ ጉዳቶችን የሚዳስስና ችግሮችን የሚፈታ የምክክርና ስልጠና መድረክ ከህዳር 25-26/ 2014ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው እንደገለጹት በአማራ ክልል በትግሬ ወራሪ ኃይል የተወረሩ አካባቢዎች በደረሰባቸው ዘረፋና ውድመት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ ሰብአዊና ቁሳዊ ቀውሶች ተፈጥሯል፡፡ የደረሰውን ውድመትና ጉዳት በመለየትም ችግሩን ለመቅረፍ በየዘርፉ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በፍጥነት ደርሰን መጠገንና መገንባት እንዲሁም የተጎዱትን ማከም የምንችልበትን እድል እንዳናጣ አሁን የሰለጠነው የስነ-አዕምሮ ህክምና ቡድን አባላት በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

የስልጠናው አስተባባሪ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና ሳይንስ ትምህርት ቤት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፈንቴ አምባው እንደገለጹት የስልጠናው አላማ የአዕምሮ ጤና፤ ስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ ላይ ትኩረት በማድረግ በጦርነቱ የተፈናቀሉና የተለያዩ ጉዳቶች የደረሱባቸውን ሰዎች ችግር መፍታት  የሚያስችልና በክልሉ መተግበር የሚችል የአሰራር ማእቀፍ ማዘጋጀት ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናው የተሳተፉት የሳይካትሪስት፤ የሶሻል ወርክና የሳይኮሎጅ ባለሙያዎች ሲሆኑ እነዚህ ባለሙያዎች ድጋፍ ሲሰጡ ምን አይነት አካሄድን ሊከተሉ ይገባል የሚል ሲሆን የተሰጠው የተለያዩ አካላት በምን መልኩ ማገዝና መደገፍ እንዳለባቸውም በስልጠናው ተመላክቷል፡፡

ከሰልጣኞች የሚጠበቀው እያንዳንዱ የሙያ ዘርፍ በምን አግባብ በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ድጋፍ እና የምክር አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል የሚለውን በጥናት እንደሚለዩ ተገልጿል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን ሁለንተናዊ ችግር ለመፍታት የሚያስችል በአጭር፤በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የሚፈቱ ችግሮችን የለየ እቅድ በማቀድ ችግሮችን ለመፍታት ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ፕሮፌሰር ፈንቴ አምባው ተናግረዋል፡፡

የፕሮግራሙ አስተባባሪ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፤ ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ፤ ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲና ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ  የተውጣጡ ምሁራን በስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጋሸና ግንባር በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በመደገፍ መልሶ ስራ ማስጀመር የሚያስችል ጉብኝት አደረገ፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ህዳር 23/ 2014 ዓ/ም)፡-ጉብኝቱ በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረምና የአብክመ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የተደረገ ሲሆን የዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ዋና ጸሃፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን እንዳሉት በጋሸና ግንባር ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እና ባሕር ዳር  ዩኒቨርሲቲ መመደባቸውን ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በጋሸና ግንባር የሚገኙ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት በትግሬ ወራሪ ኃይል ምክንያት በተፈጸመባቸው ዘረፋ የደረሰባቸውን ውድመትና ጉዳት በመጎብኘት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን የልዑካን ቡድን የመሩት የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው እንደገለጹት የባሕር ዳር  ዩኒቨርሲቲ ሀገራችን ኢትዮጵያ በትግራይ ወራሪ ሀይል የተከፈተባትን የህልውና ጦርነት ለመቀልበስ በሚሰሩ ስራዎች በንቃት በመሳተፍ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ጉብኝትም ከአሸባሪው ወራሪ የትግሬ ቡድን ነጻ የወጡ የጤና ተቋማትን መልሶ ስራ ለማስጀመር ይቻል ዘንድ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም ሶስት ስፔሻሊስት ሀኪሞችን የያዘ ሃያ አንድ አባላት ያሉት ህክምና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ጤና ተቋማቱ መላኩን ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የህክምና መድሀኒቶች፤ አልጋዎች፤ ፍራሾችና የተለያዩ ግብአቶችን ለጤና ተቋማቱ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡ ድጋፉም በጦርነቱ የተጎዳው ማህበረሰብ መልሶ እስከሚቋቋምና እስከሚጠናከር ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው አክለው ተናግረዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው እና ከአሸባሪው የትግሬ ወራሪ ቡድን ነጻ ወጡ የህክምና መዳረሻዎችን ለማስጎብኘት በስፍራው የተገኙት የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ ሲስተር ፈለቁ መኮንን አሸባሪው ቡድን በፈጸመው ወረራ ንጹሃንን በመግደል ማፈናቀሉን፣ ንብረት መዝረፍና ማውደሙን አስረድተዋል፡፡ ቡድኑ በሰሜን ወሎ ዞን ካወደማቸው ተቋማት መካከል ሰባት ሆስፒታሎችና ሰባ ሰባት ጤና ጣቢያዎች መሆናቸውን በማስረዳት ከነዚህ ውስጥ ከጠላት ነጻ የወጡትን አንድ ሆስፒታልና ሰባት ጤና ጣቢያዎች መልሶ የማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ጤና መምሪያ ም/ሃላፊዋ ለጎብኝ ቡድኑ አስረድተዋል፡፡

 

በአሸባሪው ቡድን ጉዳትና ዘረፋ ከተፈጸመባቸው የህክምና ተቋማት ውስጥ በእለቱ የተጎበኘው የሸደሆ መቄት ሆስፒታል ሲሆን የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ጌታ ለጎብኘኝው ቡድን ሆስፒታሉ የደረሰበትን ጉዳት አሳይተዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ ሆስፒታሉ ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ ህብረተሰብ ክፍሎችን ሲያገለግል የነበረ እና በአደረጃጀቱና ስራ አፈጻጸሙ በሰሜን ወሎ ዞን ደረጃ ተሸላሚ እንደነበረ በማስታወስ በሆስፒታሉ ለአገልግሎት ተከማችተው የነበሩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ መድኃኒቶች እና ሌሎች ህክምና ግብዓቶች በአሸባሪው የትግሬ ወራሪ ቡድን በመውደማቸውና በመዘረፋቸው ሆስፒታሉ አገልግሎት ማቆሙን ተናግረዋል፡፡

ሆስፒታሉ አሁን ከጠላት ነጻ ስለወጣ ግብአቶችን አሟልቶ ስራ ለመጀመር መዘጋጀታቸውን ሥራ አስኪያጁ አክለው ገልጸዋል።

 

ጉብኝ ቡድኑ በአስጨኳይ ሆስፒታሉን ስራ ማስጀመር የሚቻልበትን የስራ ስምሪትና ምክክር በማድረግ ስራ ተከፋፍሎ የንፋስ መውጫ ሆስፒታልን ስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ ለህብረተሰቡ ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው ቀጥለዋል

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ላለፉት ሁለት ሳምንታት የዘማች ቤተሰብን ሰብል በመሰብሰብ ከፍተኛ እርብርብ እያደረጉ መሆኑ ያታወቃል፡፡ በተመሳሳይ ህዳር 22/2014 ዓ.ም በሰሜን ሜጫ ወረዳ አማሪት ቀበሌ በመገኘት የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ ለህብረተሰቡ ያላቸውን አጋርነት በተግባር አሳይተዋል፡፡ 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ የእለቱ የሰብል ስብሰባ ዋነኛ ዓላማ የዘማች ቤተሰብ አርሶ አደሮችን ቅድሚያ ሰጥቶ መሬቱን ነፃ ማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሜጫ ወረዳ ወደ ሰባት ሺ የሚጠጋ ሄክታር ማምረት የሚችል ትልቅ መስኖ ያለበት አካባቢ ከመሆኑ አንጻር በምስራቁ የአማራ ክፍል የወደመውን ሰብል ለመተካት በሰፊው ማምረት እና የተመረተውን ሰብል በአግባቡ መሰብሰብ መቻል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም አርሶ አደሮች ከወቅቱ ጋር የሚስማሙ ሰብሎችን እንዲዘሩ በማማከር እና ኮምባይነር እና ዘመናዊ ማረሻ ቴክኖሎጂዎችን በማስገባት የአገሪቱን ወቅታዊ ፈተና ለማለፍ የሚያስችሉ አበረታች ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብና ቴክኖሎጅ ሽግግር ተቀዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር ተሰማ አይናለም በበኩላቸው ባለፈው ሳምንት ይልማና ዴንሳ እንዲሁም ጎንጂ ቆለላ ወረዳዎች ላይ የጤፍ አጨዳ ውጤታማ እንደነበር አንስተዋል፡፡ የሰሜን ሜጫ ወረዳ አካባቢ የመስኖ መሬት እንደመሆኑ ተሎ ሰብሉ ተነስቶ በሌሎች ሰብሎች እንዲተካ እና በምዕራብ አማራ ያለው አጠቃላይ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በእለቱ የሚከናወነው የበቆሎ እና ዳጉሳ ሰብል ምርት ስብሰባ ጅማሮ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነግረውናል፡፡

በአማሪት ቀበሌ የመንግስትን የክተት ጥሪ ተከትሎ አባቱንና ወንድሙን ግንባር ያዘመተው ወጣት አማረ ተስፋሁን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ሰብላቸውን በመሰብሰብ ላሳዩት አጋርነት አመስግነዋል። ቀጣይም ሌሎች ሰብሎችን ለመሰብሰብ ድጋፋቸው እንዳይለየን በማለት መልክዕት አስተላፏል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ እስኪደመሰስ ድረስ አካባቢን ከፀጉረ ልውጦች መጠበቅና የዘማች ሚሊሻዎች ቤተሰብ እንክብካቤ እና ሰብል ስብሰባ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስናቀው አገኘው ተናግረዋል።

 

Congratulations!
==========
The Startup at BiT MakerSpace of BiT-BDU is shortlisted among the Top-16 Nominee of the 2022 Royal Academy of Engineering Award

Pages