Latest News

የነጭ ሪቫን ቀን በሐገር ዓቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

(ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፤ ታህሳስ 21/2014ዓ/ም)

የነጭ ሪቫን ቀን ‹‹ እኔ ለእህቴ ጠባቂ ነኝ ሰላም ይስፈን፣ ፆታዊ ጥቃት ይቁም›› በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ በጥበብ አዳራሽ ታህሳስ 20/2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በድምቀት ተከብሯል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ጾታና ልማት ጥናቶች ትም/ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አቶ ተናኘ ይሰማው እለቱን አስመልክቶ “ፃታዊ ጥቃትን እንደጦርነት መጠቀም” በሚል ርዕስ ለመነሻ ሀሳብ የሚሆን ጥናታዊ ጹሁፍ አቅርበዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1989 ታህሳስ 6 ቀን በካናዳ ሞንትርኤል በሚባል ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ አብረውት የሚማሩ 14 ሴት የምህንድስና  ተማሪዎች ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ ማህበረሰቡን ያነቃነቀ እንደ ነበርና ለነጭ ሪባን ቀን መከበር ዋና ምክንያት መሆኑን በመነሻ ጽሁፉ ላይ ተመላክቷል፡፡ በ1991 እ.ኤ.አ ጥቃቱን ለማስቆም በወንዶች የሚመራ ነጭ ሪቫን በሚል የሚጠራ አመታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ ቀን  ሕዳር 25/2014ዓ/ም  እስከ ታህሳስ  6/2014ዓ/ም  እንዲሆን  መወሰኑን በጥናታዊ ጹሁፍ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና አለም-አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርት የሆኑት ሙሉነሽ ደሴ  በሀገራችን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዊያን ላይ  ከመደፈር ጀምሮ ህይወት የማጣትና የንብረት ውድመት ማጋጠሙን ተናግረዋል፡፡  ከጦርነቱ አካባቢ የሚመጡ ተማሪዎቻችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የችግሩ ሰለባዎች በመሆናቸው  ለተማሪዎች የስራዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬቱ በማህበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠናዎች በተለየ መልኩ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በዚህ ዙሪያ ድምጽ የሚያሰሙበት፣ ቅስቀሳ የሚያደርጉበት፣ የሚያስተምሩበትና የህብረተሰቡን አስተሳሰብ  ለመቀየር  ስራዎችን የሚሰሩበት ቀናት ናቸው ብለዋል፡፡

በእለቱ መርሃ ግብር ለመነሻ ሀሳብ በቀረበው የጥናት ጽሁፍ የሴቶችን መብት ለማስከበር በርካታ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎች በዓለማችን ላይ ቢወጡም አሁንም ድረስ ጥቃቶች ሊቆሙ እንዳልቻሉ ተመልክቷል፡፡ ጥናቱን መነሻ በማድረግና በጦርነቱ ወቅት በሴቶችና ህፃናት ላይ የተከሰቱ በርካታ ችግሮችን በማንሳት ከሁሉም ግቢ የመጡ ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት መሠረታዊ የሆነውን የሰው ልጆች መብት የሚጥስና ተጎጅዎችን  ለሞራል መላሸቅ፣ ለአካላዊ ፣ ወሲባዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቶች እንደሚዳረግ በውይይቱ ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ዘለቀ

 

 

“ሥነ-ቃል ለታሪክ፤ ታሪክም ለሥነ-ቃል” የምክክር ጉባኤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

(ባዳዩ ታህሳስ 20/2014ዓ/ም)

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት እና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር “ሥነ-ቃል ለታሪክ፤ታሪክም ለሥነ-ቃል” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የምክክር ጉባኤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው ሴኔት አዳራሽ በመካሔድ ላይ ይገኛል።

ዛሬ ታህሳስ 20/2014ዓ/ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕዳ ግቢ በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሂውማኒቲስ ፋካሊቲ ዲን ዶ/ር ሰፋ መካ የዘርፉ ምሁራን ለሥነ-ቃልና ለታሪክ መጠበቅና እድገት ከፍተኛ ሚና እና ኃላፊነት እንዳለባቸው በመግለጽ  ለእንግዶችና ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ “ሥነ-ቃል ለታሪክ፤ታሪክም ለሥነ-ቃል” ያላቸውን ቁርኝትና ተዛምዶ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ጠቁመዋል።የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚደረግ ሲሆን የተለያ አርእስቶች ያላቸው ስምንት የጥናት ጽሁፎች የሚቀርቡ መሆኑን ከወጣው የጉባኤው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለመከታተል ያመች ዘንድ የሚቀርቡና በመቅረብ ላይ የሚገኙ አርዕስቶች፡-የቃል ታሪክ ጽንሰ ሀሳብ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር (በዶ/ር ተመስገን በየነ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ)፤ የቃል ታሪክ ጠቀሜታ፤ እስከ አሁን ያሉ ጥረቶች እና የወደፊት አቅጣጫዎች (በዶ/ር ሞገስ ሚካኤል ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ)፤ የትኩረት አቅጣጫ ጥቆማ (በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ-መጽሀፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር )፤ የቃል ታሪክ፤ ከታሪክ ጥናት አንጻር (በአቶ አገኘሁ አዳነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ጥበባት ኮሌጅ ዳይሬክተር)፤ በቃል ታሪክ ዙሪያ የሌሎች አፍሪካ አገራት ተሞክሮ (በአቶ ገረመው ከበደ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ- መጽሀፍት አገልግሎት፤የቃል ታሪክ አሰባሰብና አሰናነድ፤ ( ዶ/ር ሰለሞን ተሾመ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) እና የወደፊት አቅጣጫና የማጠቃለያ መልእክት (በዲያቆን እንዳልካቸው ወርቁ የሰሜን ምእራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ) ሲሆኑ በውይይቱም የተጋበዙ ባለሞያዎች፤ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል!!

በምድረ- ግቢ  ፅዳትና ውበት ስራዎች የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ግቢዎች  እውቅና ተሰጠ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሰባቱም ግቢዎች የምድረ- ግቢ  ፅዳትና ውበት ስራዎች  ለበርካታ ወራት በዳይሬክተር ደረጃ ተቋቁሞ ተጨባጭ እና ውጤታማ ስራዎችን  እየሰራ ይገኛል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት  ያወጣውን  መስፈርት አሟልተው የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ግቢዎች ታህሳስ 14/2014 ዓ.ም በጥበብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የእውቅና መስጠት ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

በእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ገደፋዉ ሽፈራዉ በዩኒቨርሲቲያችን የግቢ ፅዳት እና ውበት ስራዎች በሁሉም ግቢዎቸ እንዲተገበሩ ግንዛቤ በመፍጠርና ለስራውም ልዩ ትኩረት በመስጠት; ስራው ዘላቂና ሳይንሳዊ መንገድን በተከተለና በእውቀት ላይ ተመስርቶ እንዲመራ በማዕከል  ደረጃ አመራር በመመደብ በሁሉም ግቢዎች  ውጤታማ ስራ እንዲሰራ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

ለወደፊት ተገቢውን ክትትልና እገዛ ለማድረግ ያግዝ ዘንድ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት አማካኝነት አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም የማወዳደሪያ መስፈርት በማውጣት  በመስፈርቱ መሰረት የላቀ አፈፃፀም ላሳዩት ግቢዎች ማለትም የግብርና እና አካባቢ ሳንስ ኮሌጅ ግቢ አንደኛ  የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ  ግቢ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ በማግኘት የእውቅና ምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡  

በተመሳሳይ በምድረ- ግቢ  ፅዳትና ውበት ስራ ላይ ጥሩ አፈፃፀም ላስመዘገቡ  ለግብርና አካባቢ ሳይንስ ግቢ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ለአቶ ታደሰ መኳንንት  እና  ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ  ግቢ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ለኮማንደር ፈንታሁን አያሌው በአስተዳደር ዘርፉ ላበረከቱት አስተዋፆ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ  የላፕቶፕ ኮምፒውተር  ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ዘለቀ

ታህሳስ 14/2014 ዓ.ም  

ባዳዩ

 

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "የሐሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ላይ ያሳደረው ጫናና መፍትሄው" በሚል ርዕስ ነገ ታህሳስ 16/2014 ዓ.ም የሚያካሂደውን ታላቅ ጉባዔ ምክንያት በማድረግ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በባሕር ዳር መግለጫ እየሰጡ ነው።

15/04/2014 ዓ.ም

ባዳዩ

በላሊበላ ግንባር ለሚገኝው የወገን ጦር የአይነት ድጋፍ ተደረገ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በላሊበላ ግንባር ለሚገኝው የፀጥታ ሀይሎች ከ400 ኩንታል በላይ የደረቅ ምግብ ታህሳሰ 12/2014 ዓ.ም ግንባር ድረስ በመሄድ ድጋፍ አደረገ፡፡

ለወገን ጦር የተሰጠው ድጋፍ በይባብ፣ ዘንዘልማና ዋናው ግቢ፣  ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ እና ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ሰራተኞች መዘጋጀቱን ከአስተባባሪዎች መረዳት ተችሏል፡፡

የትህነግ ወራሪ ኃይል ያደረሰውን ጉዳት የሚያጠና ግብረ-ኃይል ተዋቀረ

*********************************************************

በትግራይ ወራሪ ኃይል የደረሰብንን ቁሳዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት በመተንተን ለቀጣይ ምን መደረግ እንዳለበት የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አጥንቶ የመልሶ ማልማት ስልታዊ ዕቅድ ማዘጋጀትን ዓላማ አንግቦ የሚሰራ ግብረ ኃይል ተዋቀረ፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናቶች ተቋም ዲን ዶ/ር አዳነ ተስፋ እንደተናገሩት በትግራይ ወራሪ ሀይል ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የጉዳቱን መጠንና አይነት በዝርዝር አጥንቶ መረጃውን በመሰነድ እና በቀጣይ የተለያዩ ስራዎችን ለመከወን የሚያግዝ መረጃ እንዲኖር ከዩኒቨርሲቲው የተውጣጡ የተለያዩ ባለሙያዎችን አካቶ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ 

ከባሕር ዳር፣ ደብረ ታቦርና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከክልሉ የተውጣጡ የተመረጡ ባለሙያዎች  ወራሪው ኃይል እየተደመሰሰና አካባቢውን እየለቀቀ በመሆኑ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች በጥናት የተደገፈ የመልሶ ማልማት ስራ ለመስራት በጋሸና ግንባር የደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ አካቢዎችን ለማጥናት የተዋቀረ ኮሚቴ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኮሚቴው ፀሀፊ ዶ/ር አዳነ ተስፋየ እያንዳንዱ የቡድኑ አባል በውስጡ በተደራጁ አራት ዘርፎች በቤተሰብ ደረጃ የደረሱ ሰብአዊ ቀውሶችን፣ በኢኮኖሚ ዘርፍ፣ በመሰረተ ልማት እና ማህበራዊ ዘርፎች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በአግባቡ በመሰነድ በቀጣይ ምን መደረግ እንዳለበት አቅጣጫ ይሰጣል፡፡ በተለይም የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ዘርፉ የሚጠኑ ጥናቶችን በሙሉ በፎቶ፣ በቪድዮና በድምፅ ተቀርፀው ያለፈውንና ሁኔታ የሚያሳይ መረጃ ተሰንደው እንዲቀርቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አዳነ አክለውም ዋና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ፕላንና ኢኮኖሚ ሰብሳቢ፣ የዩኒቨርሲቲ ፎረም ምክትል ሰብሳቢ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናቶች ተቋም ዲን ፀሀፊ፣ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አባል፣ የምሁራን መማክርት አባል በመሆን ግብረ-ኃይሉን እንደሚቆጣጠር ገልፀዋል፡፡ 

 

ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ /ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከPartners in Education in Ethiopia and Operation Eye sight Universal-Canada (OES) ጋር በመተባበር ለአዲስ አለም ሆስፒታል የዓይን ሕክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡

ሙሉ ዜናውን ለማግኘት፡-https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1898213397046903

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሜካኒካል እና ኢንዱስትሪያል ምህንድስና ፋኩልቲ መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የተበላሹ የህሙማን አልጋዎችን ጠግነው አስረከቡ
=============================================
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት፡-https://www.facebook.com/bitpoly/posts/1473865696347929

የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የደረሱ ሰብሎች በአራት የተለያዩ ዙሮች/ዘመቻዎች ሰበሰቡ፡፡

ሙሉ ዜናውን ለማግኘት፡- https://www.facebook.com/eitex.et/posts/323061279819064

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ 2ኛ ዙር የሐኪሞች ቡድን ለነፋስ መውጫ ሆስፒታል ላከ።

https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1896880667180176

Pages