በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮሌጅ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል የእጅ ማፅጃ/ Sanitizer የማምረት ሂደቱ ቀጥሏል፡፡

ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በነበረዉ ዘገባ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል በWHO መስፈርት መሰረት የእጅ ማፅጃ/ Sanitizer እያመረተ እንደነበር መገለፁ ይታወቃል፡፡ በዘገባዉም በኮሌጁ አነሳሽነት በአምስት የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል መምህራን መሪነት ከ 400 ሊትር በላይ ሳኒታይዘር እንደተዘጋጀ፤ ነገር ግን የሳኒታይዘር መያዣ ዕቃ ዕጥረት በመኖሩ ዕቃዉ ተገዝቶ እስኪመጣ በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዙር የተዘጋጀዉ ከ 400 ሊትር በለይ ሳኒታይዘር በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ዉስጥ ለሚሰሩ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም በከፊል በዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደር ህንፃ ለሚሰሩ ሰራተኞች የተሰጠ ሲሆን፤ የሳኒታይዘር መያዣ  ዕቃ መገዛቱን ተከትሎ  በአሁኑ ሰዓት ባለዉ የአልኮል መጠን ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ደረጃ ቀደም ሲል ተዘጋጅቶ ከተሰራጨዉ በተጨማሪ ከ 1600 ሊትር በላይ ሳኒታይዘር ተዘጋጅቶ ያለቀ መሆኑን ከአዘጋጅ ኮሚቴዉ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ስርጭቱን በተመለከተ የኮሌጁ ዲንና የኮሚቴዉ አባላት በዩኒቨርሲቲዉ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመነጋገር በአጭር ግዜ እንደሚያሰራጩ ተገልጿል፡፡