ደማችን ለአርበኞቻችን፤ ህይወታችን ለሀገራችን

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደም ለገሱ

****************************

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹ደማችን ለአርበኞቻችን፤ ህይወታችን ለሀገራችን” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አካሄደዋል፡፡

በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የግሸ አባይ ግቢ ተማሪዎች ለሃገራችን ህልውና እና ለእያንዳንዳችን መኖር እየተዋደቁ ላሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚኒሻ እና የፋኖ አባላት ደም በመለገስ የበኩላቸውን አስተዋፆ አድርገዋል፡፡

አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እንደገለጹት ገንዘብ ከማዋጣትና ደም ከመለገስ ባሻገር ሀገራችን ኢትዮጵያን ከገጠማት ችግር ለማውጣት ሁሉም ወጣት ወደ ጦር ግንባር በመዝመት አጥፊውን የህወሓት የሽብር ቡድን ለመደምሰስ መዋጋት አለበት ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ 414 ተማሪዎች ደም ለግሰዋል፡፡