የእጅ ማፅጃ /Sanitizer/ በስፋት እየተመረተ ነው

 የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የእጅ ማፅጃ/Sanitizer/በሙሉ አቅሙ ማምረት ጀመረ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚያደረጉ ጥረቶች አንዱ የሆነውን የእጅ ማፅጃ /Sanitizer/ በሙሉ አቅሙ እያመረተ ነው ፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኬሚካልና ምግብ ምሕንድስና መምህር አቶ ባንተላይ ስንታየሁ እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ ካሁን በፊት በነበረው ግብዓት በሙከራ ደረጃ የእጅ ማፅጃ / Sanitizer/ ማምረቱን አውስተው  አሁን ደግሞ ተፈጥሮ የነበረውን የአልኮል ግብዓት መንግስት  መቅረፍ በመቻሉ፤ ካለፈው በተሻለ የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት  መሰረት ያላቸውን የሰው ሃይል በመጠቀም በቀን እስከ 500 ሊትር እየተመረተ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ምርቱ የዩኒቨርስቲው ማዕከል በሚያቋቁመው ቴክኒካል ኮሚቴ እንደሚሰራጭ ጠቁመዋል፡፡

የንጽህና መጠበቂያውን ለማዘጋጀት በዋናነት  ‘ኢታኖል፣ ሀይድሮጅን ፐር ኦክሳይድ ፣ግላይሴሮል ፣ሽቶ እና አልኮል አገልግሎት ላይ ውሏዋል ብለዋል ፡፡