የተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር

የተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

ትዕግስት ዳዊት

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የስነምግባር እና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት  ከማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርራን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ዩኒቨርሲቲ አቀፍ በስነ-ምግባር እና ሙስና ላይ ያተኮረ የጥያቄና መልስ ውድድር አካሂዷል፡፡

ውድድሩ መካሄድ የቻለው የፌዴራል ስነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ስነ-ምግባር እና ሙስና ተኮር ጥያቄዎች  ላይ የጥያቄ እና መልስ ውድድሮች እንዲካሄዱ እና በውድድሩ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተማሪዎች እንዲልኩላቸው ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ሲሆን በሁሉም ግቢዎች ተማሪዎች በውድድሩ እንዲሳተፉ በማድረግ  ከተወዳዳሪዎች አብላጫ ውጤት ያመጡ 9 ወንድ እና 5 ሴት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለአሸናፊዎች አሸናፊ ውድደድር ተለይተዋል። በዚህ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር  የሶስተኛ አመት የህክምና ሳይንስ ተማሪ የሆነችው   ብሩክታዊት መለሰ  እና የሶስተኛ አመት የኤሌክትሪካል ምህንድስና ተማሪ የሆነው አበበ አለማየሁ  እኩል ውጤት በማስመዝገብ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቀዋል።

ውድድሩን ያሸነፉት ሁለቱ ተማሪዎች የፌዴራል ስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተቌቌመበትን 20ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ግንቦት 16/ 2013 ዓ.ም በሚያከብረው መርሃ ግብር በመገኘት የተዘጋጀላቸውን ሽልማት እንደሚወስዱ ታውቋል።