የሳይንስ ካምፕ ፍፃሜ

የልጃገረዶች የሳይንስ ካምፕ (STEM Girls Camp) ቆይታ ፍፃሜ ደረሰ

በሙሉጎጃምአንዱዓለም

የባህሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ኢንጅነሪንግ እና ሒሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል (STEM Center) በየዓመቱ የሚያካሂደው የሴቶች  ካምፕ ፕሮግራም ዋንጫ የወሰደውንና ጠንካራውን ቡድን በመለየት ፍፃሜ አግኝቷል፡፡

ተማሪዎች ማረፊያቸውን በዩኒቨርሲቲው ሰላም ግቢ አድርገው ለ8 ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ሳይንስን በጨዋታ መልክ ተምረዋል፡፡ በቆይታቸው ወቅት ጥሩ ስራ የሰራውን ለመለየት ያመች ዘንድ በአገር በቀል ታዋቂ ሳይንቲስቶች ስም ማለትም በፕሮፌሰር ሶስና ሃይሌ፣ በፕሮፌሰር ያለምፀሀይ መኮነን፣ በዶ/ር ደብረወርቅ ዘውዴ እና በዶ/ር ሰገነት ቀለሙ ቡድን መስርተው ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈረው-ተገኝተው ተማሪዎች ወደ መጡበት ት/ቤት ሲመለሱ የቀሰሙትን እውቀት ለሌሎች ዕድሉን ላላገኙ ተማሪዎች እንዲያካፍሉና ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትኩረት ሰጥተው ለሞዴልነት የተጠቀሱትን ታዋቂ ሴት ሳይንቲስቶች በመተካት አምባሳደር እንዲሆኑ መክረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ተማሪዎች ቆይታቸውን በሪፖርት መልኩ አቅርበው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡት የፕሮፌሰር ያለምፀሀይ ቡድኖች ከዶ/ር ተስፋዬ እጅ ዋንጫ ተበርክቶላቸዋል፡፡