በመርጡለ ማሪያም ድጋፍ

የባሕር ዳር  ዩኒቨርሲቲ ለፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ አደረገ

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 30/2014 ዓ.ም  በምስራቅ ጎጃም ዞን በመርጡለ ማሪያም ከተማ በመገኘት ለአማራ  ክልልና ለፌዴራል ፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ አድርጓል።

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ገደፋዉ ሽፈራዉ በርክክቡ እንደገለፁት የተደረገዉ ድጋፍ ሁለት መቶ (200) ኩንታል የዳቦ ዱቄት ሲሆን በጥሬ ገንዘብ ሲተመን  ከ1.1 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጣ ጠቁመዋል።

  

የምስራቅ ጎጃም ዞን የግብርና መምሪያ ኃላፊ  አቶ ፈንታሁን ቸኮል እና የመርጡለ ማሪያም ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ዋለ ድጋፉን  የተረከቡ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ አቶ  ፈንታሁን ቸኮል ምስጋና አቅርበዋል። አክለውም  ጦርነቱ በድል  እስኪቋጭ ድረስ  መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

 

ድጋፉን ለማስረከብ የሄደውን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ልኡክ የመሩት አቶ ገደፋው ሽፈራው  በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው  የህልውና ትግሉን ለመደገፍ በተለያዩ ግንባሮች በመገኘት ለፀጥታ ኃይሎች እና ለተጎዱ የህብረተሰብ  ክፍሎች  ፈርጀ ብዙ   ድጋፍ  ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው ፣ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  የተማሪዎች ዲን ዶ/ር ምኒይችል ቢተው እና  የጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙላት ጠብቀዉ ዩኒቨርሲቲውን በመወከል ተገኝተዋል።