ምክኒያታዊና ንፁህ ትውልድ እንፍጠር

‹‹ምክኒያታዊና ንፁህ ትውልድ እንፍጠር›› በሚል የተሰባሰቡ ተመራቂ ተማሪዎች አቅመ ደካሞችን መገቡ

ምክኒያታዊና ንፁህ ትውልድ እንፍጠር በሚል በተመራቂ ተማሪዎች የተቋቋመው ማህበር የከተማውንና የፔዳ ግቢ ማህበረሰብን በማስተባበር አቅመ ደካሞችን መገበ፡፡

የምክኒያታዊና ንፁህ ትውልድ ማህበር ስራ አስፈፃሚ የሆነው ተማሪ ተመስገን ሙሉቀን እንደተናገረው የማህበሩ ዓላማ ተማሪዎችና ወጣቱ ላይ ንፁህና ምክንያታዊ የሆነ ትውልድ ገቢራዊ አስተሳሰብን መፍጠር ሲሆን የዚህ እንቅስቃሴ አንዱ ማሳያ በእለቱ የተካሄደው የምገባ ፕሮግራም ነው ብሏል፡፡ ተማሪ ተመስገን  አክሎም በዕለቱ በየቤቱ በዓል ሲመጣ ተቸግረው የሚያሳልፉ ወደ 500 የሚጠጉ አቅመ ደካሞችን በማሰባሰብ እኛ የቀመስነውን ለማቅመስና አለንላችሁ ለማለት በማሰብ የምግብ ማጋራት ፕሮግራሙ እንደተከናወነ  ጠቁሟል፡፡

በቀጣይም ተመራቂ ተማሪዎች ከምርቃት በኋላ ግቢውን ለቀው እስኪወጡ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሞክሮ የማካፈል እና የጥምቀት በዓል ከተከበረ በኋላ ደግሞ በከተማው የፅዳት አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡