ለተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኤች አይ ቪ ጋር በሚኖሩ የአስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን በተቋቋመው የእድገት ስራ ማህበር አማካኝነት 25 ለሚሆኑ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለልደት በአል መዋያ የሚሆን ብር 400.00 ለእያንዳንዳቸው ተለግሷል፡፡
እርዳታው የተደረገላቸው የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በድል ችቦ፣ እውቀት ፋና፣ ሹም አቦ፣ መስከረም 16 እና ፈለገ አባይ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ወላጅ አልባ ልጆች እንደሆኑም የታወቀ ሲሆን ከዚህ እርዳታ ባሻገር በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመደበኛው ፕሮግራም ትምህርተቸውን ለሚከታተሉ ሁለት ከቫይረሶ ጋር ለሚኖሩ ተማሪዎች ቋሚ የቁሳቁስ እርዳታ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡
ማህበሩን 31 ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ የተቋሙ ሰራተኞች የመሰረቱት ሲሆን ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ፎቶ በማንሳት እና የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ከፍቶ በመስራት ገቢ እንደሚያገኝ በዩኒቨርሲቲው የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ገልፀዋል፡፡