ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በርቀት መርሐ ግብር የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ አዲስ የግል አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች መማር የምትፈልጓቸውን ኘሮግራሞችና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et ወይም በርቀት ማስተባበሪያ ኘሮግራም ጽ/ቤት ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/cde ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የመግቢያ መስፈርት  በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት መሠረት ማሳሰቢያ፡-  የማመልከቻ ጊዜ ከነሐሴ 15/2011 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2012 ዓ.ም  ኦፊሺያል ትራንስክርቢት ከምዝገባ በፊት ቀድሞ መድረስ አለበት  በ2011 ዓ.ም መሰናዶ ያጠናቀቁ ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች ማመልከት የሚችሉት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ከታወቀ በኋላ ይሆናል::

Pages

Subscribe to Continuing Distance Education Programs RSS