ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከህክምናና ጤና ሳይን ኮሌጅ በመጡ ባለሙያዎች ከሁሉም ግቢዎች ለተወጣጡ ነርሶችና የጤና መኮንኖች Integrated Emergency Patient Training በሚል ርዕስ ዙርያ ለ 30 የህክምና ባለሙያዎች ከ 27—30/09/2011 ዓ/ም ድረስ ለ4 ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጧቸዋል፡፡ ሰልጣኞችም ከስልጠናዉ በቂ ዕዉቀት እንዳገኙና ቀጣይም ተመሳሳይ መድረኮች ተፈጥረዉ የተለያዩ ስልጠናዎች እንዲሰጣቸዉ አሳስበዋል ፡፡በመጨረሻም ሥልጠናዉን ላጠናቀቁ የጤና ባለሙያዎች የዩኒቨርሲቲዉ አጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ኤክስኪቲቭ ዳይሬክተር ከሆኑት ከ ዶ/ር ደሳለኝ እጅጉ እጅ ሰርተፍኬት ተቀብለዋል የስራ መመርያም ተሰጧቸዋል፡፡