ለአብያተ መጽሃፍት አስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ አብያተ መጽሃፍት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር General Concept of Library Automation System እና የኮሃ አዉቶሜሽን አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዉ የ አይ.ሲ.ቲ. ዳይሬክቶሬት በመጡ ባለሙያዎች አማካኝት ስልጠና ተሰጧል፡፡ ሰልጣኞችም በሰለጠኑት አግባብ ስራዎች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማየትና ለመገምገም ያመቻቸዉ ዘንድ በጋራ በመሆን የሁሉንም ግቢዎች አብያተ መጽሃፍቶችን በመጎብኘት የሰለጠኑትን በተግባር የማሳየት ስራ ተሰርቷል፡፡