You are here

ኦርጅናል ዲግሪ ማሰራት ለምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት ኦርጅናል ዲግሪ ላልተሰራላቸው የዩኒቨርሲቲው ተመራቂወች ደረጃውን በጠበቀ ሚስጥራዊ ህትመት ለማተም ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ከ17/02/2012 ጀምሮ እያመለከታችሁ ማሰራት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለማመልከት በምትመጡበት ጊዜ የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባችዋል፡፡
1. ቴምፖራሪ ዲግሪ(ዋናውን)
2. ክሊራንስ
3. የወጭ መጋራት ያለባችሁ (የወጭ መጋራት የከፈላችሁበትን ደብዳቤ እና ደረሰኝ ዋናውን እና አንድ አንድ ፎቶ ኮፒ)
4. የህትመት እና የአገልግሎት 295 ብር በዩኒቨርሲቲው የተከፈለበት ደረሰኝ
5. በአካል መምጣት ለማትችሉ ከዐቃቤህግ ጽ/ቤት ህጋዊ ዉክልና
ማሳሰቢያ ፡-1.ኦርጅናል ዲግሪውን የምትወስዱበት ቀን ከአመለከታችሁበት ቀን ጀምሮ በሁለት ወሩ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
2.ክሊራንስ የጠፋባችሁ 30 ብር እየከፈላችሁ ከፋይላችሁ ኮፒ ማስደረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Contact

 

 Main Registrar Office 

Tel:   0582205934

 

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University