ለዘላቂ የቱሪዝም ልማት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የባለ ድርሻ አካላት ሚና ለዘላቂ የቱሪዝም ልማት በባህር ዳር ከተማ» በሚል ርዕስ መጋቢት 6/2009 ዓ.ም የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ ተገለፀ፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
በእለቱ ሶስት የመወያያ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን በውይይቱም የቱሪዝም እሴት ሰንሰለት ምግብና መኝታ፣ ባርና ሪስቶራንት፣ የጉዞ ወኪልና አስጐብኝ፣ መጓጓዣና ግብዓቶችን በተገቢው መንገድ በማቅረብ የቱሪስቱን ቆይታ እንዲረዝም የሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ከዩኒቨርሲቲው የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል የመጡት ዶ/ር አበበ ድረስ በበኩላቸው በቱሪዝም ዘርፍ 12 መሰቦች በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ቢሆንም ላለመታወቅ እንደ ምክንያት የሚነሱ መሰረተ ልማት አለመሞላት፣ የግንዛቤ እጥረትና በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖር መሆናቸውን በመጥቀስ! ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቱሪዝም ለሀገር እድገት ከሚሰጠው ጠቀሜታ አንፃር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በማግስቱ ወደ ኡራን ኪዳነምህረት የባሕር ላይ ጉዞ በማድረግ የሀመር ኖህ ኡራ ኪዳነምህረት ቤተ መዘክር በመጐብኘት በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተሰሩ ጥንታዊ ስዕሎችና እድሜ ጠገብ የብራና ላይ እጅ ፅሁፎች የታሪክ መዛግብትን ማየት ተችሏል፡፡