COVID-19 ወረርሽኝ ድጋፍ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19)  መከሰት  ተከትሎ  እርዳታ  ለሚያስፈልጋቸው  አካላት ድጋፍ አያደረገ ነው

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በአገራችን ከተከሰተ ጀምሮ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደ እውቀት ተቋም እያደረጋቸው ካሉት አስተዋጽኦዎች ጎን ለጎን ወረርሽኙን  መከላከል  ይቻል ዘንድ ባሕር ዳር ከተማ  ለሚኖሩና ድጋፍ ለሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል 267 ኩንታል ፈኖ ዶቄት፣ 118 ኩንታል ሽሮ እና 34 ኩንታል በርበሬ ለከተማው አስተዳደር አስረክቧል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ግቢዎች (በቢዝነስ እና ኢኮኖሚስ፣ ዘንዘልማና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት) የተሰባሰቡትን እርዳታዎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ገድፍ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት  ለባሕር  ዳር  ከተማ  አስተዳደር  ተቀዳሚ  ምክትል  ከንቲባ  ዶ/ር  መሐሪ ታደሰ አስረክበዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት የተገኙት በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ መለስ አድማሱ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ለከተማው ማህበረሰብ እያበረከተ ያለውን አስተዋፆ በመምሪያው ስም አመስግነው በዕለቱ የተረከቡትን ቁሳቁሶች በከተማው ክፍለ ከተሞች የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ግብረ ሃይል ቀበሌ አመራሮች ለሚመለመሉ የእለት ጉርሳቸውን መሽፈን ላልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውል ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የዛሬውን ጨምሮ ግንቦት አንድ በምዕራብ ጎንደር ዞን ለሚገኙ ከውጭ በየብስ መጓጓዣና በእግር ለሚገቡ ሰዎች አስገድዶ ለይቶ ማቆያዎች የሚሆን 50 ኩንታል የዳቦ ዱቄት ፣ 5 ኩንታል ሽሮ እና 3 ኩንታል በርበሬ ድጋፍ አድርጓል፡፡