የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ከቻይናው ናንጅግ የግብርና ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ከተቋቋመበት 2001 ዓ/ም ጀምሮ በመሬት አስተዳደር ዘርፍ ባለሙዎችን እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝም የተለያዩ ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸውና ችግር ፈቺ ምርምሮችና የማህበረሰብ እያከናወነ ይገኛል፡፡ የመማር ማስተማሩንና ምርምሩን ለማሳደግና ጊዜው ከሚፈልገው አስተሳሰብ ጋር ለማስተሳሰር ኢንስትቲዩቱ ከተለያዩ አገር በቀልና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ባለው ከፍተኛ ራዕይ መሠረት ከአሁን ቀደም የተለያዩ ስምምነቶችን በመፈራረም የገንዘብና የስልጠና ድጋፎችን አግኝቷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ለመጥቀስ ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ " Innovative Technology for hand Tenure Security in East Africa" የሚል የምርምር ዘርፍን ለማገዝ የሚያሰችል Unmanned Aerial Vehide (UAV) ወይም Drone የተባለ ቴክኖሎጅ ለመረከብ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ  የPhD program in "Land Policy and Governance" በ2009 ዓ.ም. የጀመረ ሲሆን የዚህን ፕሮገራም አገራዊና አህጉራዊ ጠቀሜታ በመረዳት በDAAD በኩል የጀርመን መንግስት ለፕሮግራሙ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

እንዲሁም በነሃሴ ወር 2008 ዓ/ም ከ Nanjing Agricultural University (NAU) ከመጡ Prof Wu Wie ከተባሉ ምሁር ጋር አንድ ላይ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሠፋ ያለ ውይይት በተቀም ደረጃ ተካሄዷል፡፡ በውይይቱ ወቅት Prof. Wie NAU በቻይና ውስጥ ቀደምትና ስመጥር ከሚባሉ የትምህርት ተቋማት አንዱ መሆኑን ገልጸው በተለያዩ ሃገራት NAU እየሰራቸው ያሉትን የተለያዩ ስራዎች በምሳሌነት በመጥቀስ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በመቀጠልም በአሁኑ ወቅት የቻይና መንግስት ከኢኮኖሚ ትብብርነት ባሻገር በምርምር፣ሳይንስና ቴክኖሎጅ ከታዳጊ አገሮች ጋር ለመስራት ቁርጠኝነት ላይ እንደደረሰ ገልፀው የእሳቸውም ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ምክንያቱ ይህ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ የመሬት አስተዳደር ኢንስትቲዩት  ዳይሬክተር ዶ/ር አቻምየለህ ጋሹ በበኩላቸው Prof Wu Wie የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲን በመጎብኘታቸው አመስግነው ከ NAU ጋር በአጋነት መስራ ለሁለቱም ተቋማት ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ከቻይና የመሬት አስተዳደር ዘርፍ  ብዙ ለመማር እንደሚረዳት ገልፀዋል፡፡ በመቀጠልም አንድ ላይ ለመስራ የሚያስችሉ ነጥቦችን ለመለየት ሠፋ ያለ ውይይት ከተደረገ በኃላ ለመነሻነት የ PhD ፕሮግራሙን በማገዝ በኩል ማለትም ለPhD እና Msc ተማሪዎችን በstudent exchange እንዲታገዙ ማድረግ፤ የመመረቂያ ምርምራቸው ላይ አማካሪ መሆን፤ Guest lecturer ማስተማርና የጥምር ምርምሮችን አንድ ላይ ለመስራት ስምምነት ላይ የተደረሠ ሲሆን ስምምነቱን በመሬት አስተዳደር ኢንስትቲዩት በኩል ዶ/ር አቻምየለህ ጋሹ ሲፈርሙ በNAU በኩል ደግሞ ፕሮፊሰር Shi Xiao-ping ፈርመዋል፡፡