Latest News

Bahir Dar University president, Dr. FirewTegegne welcomes research delegates from Hungary

3o January 2023

Bahir Dar

Dr. FirewTegegne and BDU management has held a partner meeting with Dr. Melinda Tar, researcher and professor of Hungary University of Agriculture and Life Sciences at the president’s conference room. The discussion started with a brief presentation of BDU’s overall profile  followed by Dr. Tar’s presentation on Hungary’s total context as well as the historical and institutional background of Hungary University of Agriculture and Life Sciences which merged with 8 other universities in 2021.

DR. Tar also overviewed the university’s staff and student population as well as programs that have been run in the university.

Dr. Firew remarked that since BDU works tirelessly to improve research and technological transformation in the field of agriculture, the experience and collaboration with the Hungary University of Agriculture and Life Sciences will be of great value to both parties. A discussion of potential ways to strengthen the partnership between the two universities was made towards agreement of the two parties to start drafting a memorandum of understanding to be able to make the partnership more concrete.

Up on conclusion of the discussions, the delegates have visited the Zenzelima Campus, BDU where the College of Agriculture and Environmental Sciences resides.

 

 

 

 

 

 

‹‹አንድ እርምጃ›› የመድረክ ቴአትር ለእይታ ቀረበ

*************************************************

(ጥር 20/2015 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ‹‹ሰላም ለሁሉም  ሁሉም ለሰላም›› የሚል መሪ ሀሳብ ያነገበው አንድ እርምጃ ቴአትር ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ተዘጋጅቶ የቀረበ የመድረክ ቴአትር ሲሆን በፔዳ ግቢ አዳራሽ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለእይታ ቀርቧል።

የአንድ እርምጃ ቴአትር ደራሲና አዘጋጅ ቢንያም ወርቁ ሲሆን በቴአትሩ ‹‹ሰላም ለሁሉም  ሁሉም ለሰላም›› ያለውን አስፈላጊነት በተለይም አገራችን ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያጋጠማት ያለው የዘረኝነትና ጎጠኝነት ችግር ዜጎቿን ለሞትና መፈናቀል እየዳረጋቸው በመሆኑ ይህ አላስፈላጊ ድርጊት መቆም እንዳለበት ግንዛቤ የሚፈጥር ቴአትር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቴአትሩን ለመመልከት ከዩኒቨርሲቲው ሁሉም ግቢዎች የመጡ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

 በቴአትሩ ይገረም ደጀኔ፤ ፍቃዱ ከበደ፤ ሸዊት ከበደ፤ ትዕግስት ግርማ፤ያሬድ ኢጉ፤ሰለሞን ሀጎስ፤ ማህሌት ሰለሞን፤ ሄኖክ በሪሁን እና ሌሎችም ታዋቂና ወጣት አርቲስቶች ተሳትፈዋል፡፡

ከከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

Tik Tok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY

የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከበረ

*****************************************

 (ጥር 16/2015 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳተኞች ድጋፍና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ31ኛጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ30ኛ ጊዜ፤ በዩኒቨርሲቲው ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአካል ጉዳተኞች ቀን "አካታች የፈጠራ ስራ እና ሽግግራዊ መፍትሔ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጥበብ ህንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አክብሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካል ጉዳተኞች ድጋፍና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ዘላለም ተመስገን ጥሪውን አክብረው ለመጡ ታዳሚዎችና ለፅሁፍ አቅራቢዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ትኩረት ተነፍጎት የቆየ ቢሆንም በወርሃ ጥቅምት 2011 ዓ.ም የአካል ጉዳተኞች ድጋፍና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተቋቁሞ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ዘላለም በማስከተል ዩኒቨርሲቲው ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችም ሆነ መምህራን ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ በተለይም በያዝነው የትምህርት ዓመት አዲስ የገቡትን ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት ዓይነት እንዲማሩ መደረጉና በዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት በጎ ፈቃደኛነት ወጥ የሆነ መመሪያ ሳይኖር ሁሉም አካል ጉዳተኛ መምህር መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ መደረጉ አኩሪ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ይላሉ ዳይሬክተሩ በዚሁ ልክ ያልታዩ በርካታ የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ስላሉ ችግሮች የመፍትሔ አቅጣጫ ያገኙ ዘንድ ከተለያዩ አካላት ጋር ለመነጋገር የበዓሉ መከበር ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስገንዝበው የአካል ጉዳት ያለብን ሰዎች የወደፊት ተስፋ በመሰነቅ በሚያጋጥሙን እንቅፋቶች ሳንሰነካከል ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ራስን ማብቃት እንደሚገባ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ የአካል ጉዳተኞች ችግር የሁላችን ሊሆን እንደሚገባና ከባድ የሚባል የአካል ጉዳት ያለበት ሰው ለማመን በሚያዳግት መልኩ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን በተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎች እንደሚታይ አውስተው በኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ግን ከማህበረሰቡ የግንዛቤ ማነስ ጀምሮ ለአካል ጉዳተኞች መሰጠት የሚገባው ትኩረት ወደ ጎን የተተዎ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር እሰይ አክለውም በአገር አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ 22% ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አለመቅረባቸውን የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙና ዩኒቨርሲቲውም እንደ ዩኒቨርሲቲ አካል ጉዳተኞችን የሚደግፉ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ተሻሽለው እንዲወጡ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባው ብሎም ተፈፃሚነታቸውን የሚመለከተው አካል እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው እያከናወነው ካለው ተግባራት ጋር ሌሎች ተጨማሪ ተግዳሮቶች ወይም መሟላት ያለባቸው ነገሮች በዝርዝር ቀርበው መፍትሔ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የአካል ጉዳተኞችና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች  ታሪካዊ ዳራ እና አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የህግ ድንጋጌዎች በሙያው ባለቤት ምሁራን የቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በማጠቃለያውም ዶ/ር እሰይ ዩኒቨርሲቲው የአካል ጉዳተኞች ከአለሙት ግብ እንዲደርሱ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገልፀው የአካል ጉዳተኞች ድጋፍና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለአካል ጉዳተኞች የተለየ ድጋፍ በማድረግ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስክር ወረቀት አበርክቶላቸዋል፡፡

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

Tik Tok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY

 

በስራ አመራር እና እቅድ ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው

*********************************************************

 (ጥር 16/2015 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የስራ ዘርፎች እያገለገሉ ለሚገኙ አመራሮች በየደረጃው ያለውን የስራ አመራር ጥራት ከፍ ማድረግ እና የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥተው ተቋማቸውን በተገቢው መልኩ መምራት የሚያስችልና ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና በቀድሞው ሰኔት አዳራሽ እየተሰጠ ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የፌዲራል ስልጠና ኢንስቲትዩት መምህር እና ተመራማሪ ዶ/ር ተመስገን ዳኘ  እንደገለጹት  የስልጠናው ርዕስ የማቀድ እና ስራ የመምራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በስራ አመራር ክፍሉ ውስጥ ስለ ፅንሰ ሀሳቡ፣ መሪነትና አመራር ምንድን ነው? የጥሩ መሪ መገለጫዎች ምንድን ናቸው?  የመሪነት ዘይቤስ ምንድን ነው?  የሚለውን በተመለከተ መወያየት ሲሆን እንዲሁም እቅድ በማቀድ ዘርፍ ነገሮችን አሻግረው እያዩ የሚያስቀምጡ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡ ይህን  እያሰቡ ያሉትን ነገር ደግሞ የሚመሯቸውን ሰዎች በማስከተል ወደ ተግባር የሚቀይሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ተመስገን ዳኘ አክለውም ስራ አመራር በጥቅሉ በጎ ተፅዕኖ ማሳደር ሲሆን ይህን ለመተግበር ከምንመራቸው ሰዎች ተሽሎ መገኘት፣ የምንመራቸውን ሰዎች ዋጋ መስጠት፣ አርአያ ሁኖ መገኘት፣ እምነት ከተግባር ጋር አብሮ መሄድ እና የምንናገረውን ነገር በተግባር መኖር መቻል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

መሪዎች የስሜት ብልህነት የተላበሱ መሆን መቻል አለባቸው፡፡ በዚህ ስር ራስን ማዎቅ፣ ራስን መምራት፣ ሌሎችን ማዎቅ እና ሌሎችን ማስተዳደር የሚሉት ርዕሶች በስልጠናው ይነሱበታል፡፡  በተጨማሪም የልቦና ውቅር  ምን  እንደሚመስል በመገንዘብ ሰልጣኞቹ ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው በመመልከት ከእውነታው ጋር እያገናዘቡ ሌሎችንም ርዕሶች በማንሳት እንዲወያዩ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

Tik Tok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY

 

 
It was a big moment of togetherness finding big names of Peda, BDU at a wedding ceremony organized by one of their colleague. Some of them came from abroad and some from distant places for the event. Almost all of them have served BDU for over 25 years diligently in upbringing qualified graduates at the former Bahir Dar Teachers College and the latter Bahir Dar University.
Standing at front (from camera left to right)
1. Kassie Shiferie (PhD, English)
2. Mihret Alemneh (PhD, Maths)
3. Ferede Zewdu (Asst. Prof., Geography)
4. Abdu Mohammed (Asst. Prof., English)
5. Tesfaye Dagnew (PhD, English)
6. Mulugeta Neqa (Asst. Prof., Geography)
7. Abebe Chekol ( Counselor, Pedagogy)
Standing at the back (from camera left to right)
1. Awoke Andarge (PhD, Mathematics)
2. Fentahun Ayele (PhD, History)
3. Getachew Adamu (PhD, Mathematics)
4. Nigussie Negash (PhD, Chemistry)
5. Getachew Abebe (PhD, Sport Sciences)
6. Reda Darge (Professor, Psychology)
In the second picture, we see Solomon Libsu (PhD, Chemistry) standing next to Professor Reda with Gash Ferede Zewdu and Dr.Kassie Shiferie to his left.
Respect and love to all who gave whatever they have to shaping the generation!
Credit: Tamiru Delelegn

Bahir Dar University Alumna’s account of her former BiT

The current software engineer of the big Microsoft Company, Eden Melaku was a student at Bahir Dar University in 2013. Among female graduates, she was awarded a gold medal with 3.97 average high score and a gold medal with a high score from the computer faculty and a certificate of recognition for doing the best graduation project of the year by the faculty. Her stay at Bahir Dar University testified that she has contributed to her identity today. In addition, she helped the institution she studied and the students in different ways. She's all in the way.

Bahir Dar Institute of Technology would like to express its gratitude for all the support given to Eden.

 

Eden’s Account

"My name is Eden Melaku Mulugeta. I graduated from the software engineering department in february 2021. I am a software engineer at Microsoft.

I joined BDU in 2015 as a freshman student in Yibab campus, after a year, the Computing faculty moved some students to peda and I was part of that. I completed my second year study in peda campus and moved to poly campus for my 3rd and remaining years of study. I had adventures and memorable times at Bahir Dar University.

During my 5 year study in BIT I had the privilege to learn the basics of programming and software engineering from amazing teachers who went above and beyond to help me build a foundation that I can thrive on. My department has an excellent curriculum designed to prepare us with skill and mindset for the corporate and entrepreneurial world. I thank all my teachers for helping me achieve my goal. I would like to give special gratitude to teachers who made me fall in love with software engineering. My first year object oriented design teacher Mr. Asegahegn, my object oriented programming and advanced programming teacher Mr. Desta Berihu.

I got the opportunity to stay the summer and work on a project under the help of an advisor after completing my second year that gave me extra time to work on real world problems outside of regular classes. I would like to thank the computing faculty and Dr. Gebeyehu for organizing this.

I would like to thank the ICT4D research center for helping me during my final year project with materials, office space and technical advice. BIT has an excellent staff from teachers to administration, I am so happy to study in an institute determined to create high-skilled, valuable engineers.

I would like to help BIT with mentoring graduating students to prepare them for technical interviews, which can help them get a job in big tech companies; I can give technical training and workshops. I will also participate in the poly alumni network on a variety of projects it is working on.

Thank you,

Eden"

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግሽ ተራራን በማልማት እውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት

****************************************************************

(ጥር 13/2015 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ በድምቀት የተከበረውን አገር ዓቀፍ የግዮን በዓል አስምልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳን ዶ/ር ፍሬው ተገኘ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና ማህበረሰብ እንዲሁም የክልሉን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና የሚዲያ አካላትን በመያዝ ወደ ቦታው በማቅናት በዕለቱ የተከናዎኑ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ክዋኔዎችን በመታደም አካባቢውን ለማልማት ከሚሰሩ ስራዎች በተጨማሪ የቦታውን ገናናነት እና ወደፊትም ለሀይማኖታዊ ቱሪዝም የሚያበረክተውን አስተዋፆ ይበልጥ ጎልቶ እንዲወጣ ከምንም በላይ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ተገልጿል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰካላ ወረዳ በግሽ ተራራ እና አካባቢው ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎችን ሲሰራ ከመቆየቱም በላይ አካባቢውን ሀይማኖታዊ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ስራዎችን በስፋት እየሰራ ይገኛል፡፡ ጥር13/2015 ዓ.ም የተከበረውን የጻድቁ አቡነ ዘርዓ ብሩክ ዓመታዊ የንግስ በዓል ሲከበር ሊቃውንቱ የሚለብሱት 125 ሰማያዊ ካባ በልዩ ሁኔታ በማሰራት እና ከዓመታዊ የንግስ በዓሉ ጎን ለጎን ለግዮን በዓል ለሚሮጡ አትሌቶች ከ120 በላይ ቲሸርቶችን በመለገስ ዩኒቨርሲቲው ለቦታው እና ለቱሪዝም እድገት እንደሀገር የሚያደርገውን ተቋማዊ አስተዋፆ የክልል፤የዞን እና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እውቅና ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ከምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር በልዩ ሁኔታ የተሰራ ካባ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ 

በክብረ በዓሉ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝምና ቅርስ መምህር የሆኑት አቶ እንዳላማው ክንዴ በበኩላቸው አባይ የሚለውን ስያሜ በአቡነ ዘርዓ ብሩክ እንደወጣ እና ይህ ሐይማኖታዊ ቱሪዝም የበለጠ እንዲገለጥ በስፋት የማስተዋወቅ ስራ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡    

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

Tik Tok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY

Anniversary Memories

The great companionship

Bahir Dar Teachers College had communion collegiate relationship with Gondar College of Medical Sciences which later evolved to University of Gondar. This was strengthened largely through the annual inter-collegiate sports Festival/competition used to be held between communities of the two colleges from 1970s to 1990s.They used to manifest their love and respect for each other in the reception of their counterparts when they meet for the Sports event. When the Gondar Medical College hosts the Sport event, they receive their visiting BDTC counterparts from Azezo While the BDTC staff used to receive the visiting G.C.M.S from Zenzelima These pennants of Gondar College of Medical Sciences teams (pictures taken in those good old days) displayed at BDU's Sport Academy archive center mark the breath of joy and companionship.

Besides, for some years, G.M.C.S was admitting best performing freshman graduates of Bahir Dar University in its Medical Sciences program.

የምድረ ግቢ ጽዳትና ውበት ስራዎች የ6 ወራት የአፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

****************************************************************

(ጥር 09/2015 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስምንቱም ግቢዎች ባለፉት 6 ወራት ያከናወኗቸውን የምድረ ግቢ ጽዳትና ውበት ስራዎች ሪፖርትና የመስክ ምልከታ የተደገፈ ግምገማ ከጥር 4/2015 ዓ.ም እስከ ጥር 9/2015 ዓ.ም በተቋቋመው ኮሚቴ ተካሂዷል፡፡

በሳይንስና ማሪታይም አካዳሚ ጅማሮውን ያደረገው የሪፖርትና የመስክ ላይ ጉብኝት ስራ ማዕከላዊ (ጥበብ) ግቢን፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ የቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ሰላም)ግቢ፣ ግሽ አባይ ግቢ፣ ፖሊ እና ፔዳ ግቢዎችን በማየት በመጨረሻም ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ (ዘንዘልማ) ግቢ ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ተግባራት መገምገም ተችሏል፡፡ ከቀረበው ሪፖርትና የመስክ ላይ ጉብኝት አብዛኞቹ ግቢዎች አበረታች ስራ የሰሩ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡

ከልዩ ልዩ የሙያ መስኮች የተቋቋመው የግምገማ ኮሚቴ ለሁሉም ግቢዎች ስራው ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥል ምን አይነት የአሰራር ስልቶችን እየተከተሉ እንደሆነ፣ ግቢዎች የምድረ ግቢ ጽዳትና ውበት ስራዎች በምን አይነት ዲዛይን እየሰሩ እንዳሉ፣ በየግቢዎቹ የሚተከሉት እፅዋትና ሳሮች ከውበት ባለፈ ለጤና ያላቸውን አስተዋፅኦ እና መሰል መሰረታዊ ነጥቦችን በማንሳት ሪፖርቱን የገመገመ ሲሆን የቀረበው ሪፖርት ትክክል መሆን አለመሆኑንም መስክ ላይ በመውረድ እያንዳንዱን ስራ ለማየት ችሏል፡፡

በተደረገው ግምገማ መሰረት በቀጣይ ቀናት ለየግቢዎቹ ደረጃ በማውጣት የማበረታቻ ሽልማት ለመስጠት እንደሚሰሩ የኮሚቴው አባላት ተናግረዋል፡፡

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

Tik Tok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY

 

Our 60th Anniversary Sports festival is underway!

---------------------------------------------------------------------

As part of our diamond jubilee celebration, Sports festival is taking place in the presence of many spectacles. Until today, three competitive football games have been held. Each half of a game lasts for 40 minutes just five minutes short of the FIFA games, according to the information from the coordinators of the tournament.  The results are:

  1. Tibebe and PolyPeda VS. Science and Maritime (2 : 2)
  2. Bahir Dar Technology Institute VS. Education and Humanities (5 : 1)
  3. Sport Academy VS. EiTEX (5 : 1)

All are invited to come and enjoy the football matches!

Play safe and enjoy the game!

Good Luck to All!

Pages