ማስታወቂያ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንተርኘርነርሽኘ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል በተመረጡ የአይሲቲ (ICT) ዘርፎች የቢዝነስ ኃሳብ እና ፍላጎት ያላቸውን 10 አመልካቾች ሙሉ ግብዓት ባሟላ ቤተ ሙከራ (Incubation Center) ለ1 ዓመት ኃሳባቸውን በማበልፀግ ወደ ንግድ ድርጅት ለማሸጋገር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፍላጐት ያላችሁ እና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ እንድታመለክቱና የእድሉ ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡

ሀ. የመመዝገቢያመስፈርት

1. በቴክኒክና ሙያ ቢያንስ በደረጃ 3 በICT ዘርፍ የተመረቀ/ቀች እና ከዚያ በላይ

2 አመልካቹ በዘርፉ ሊሠራ ያሠበውን/ችውን የቢዝነስ እቅድ ማጠቃለያ /business plan executive summary/ማቅረብ የሚችል/ምትችል

3. ለማመልከት ያነሳሳቸውን ምክንያት /Statement of Motivation/ ከአንድ ገፅ ያልበለጠ መግለጫ ማቅረብ የሚችል/ምትችል 4. ከአንድ ገፅ ያልበለጠ የማንነት መግለጫ (Curriculum Vitae) ማቅረብ 5. ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ የሚከተለውን ቅፅ በመሙላት ይመዝገቡ፡፡

ሙሉስም------------------------------------- የት/ዝግጅት--------------- ስልክቁጥር------------------------የኢሜይል አድራሻ----------------------------------------

መሰማራት የሚፈልጉበት ዘርፍ

1. Software Development

2. Website Development

3. Networking

ለ/ የመመልመያ መስፈርቶች

1 ማዕከሉ የሚያወጣቸውን የተግባር፣ የፅሁፍና የቃልፈተና ማለፍ መቻል

2 ከማዕከሉ ጋር ሙሉ ጊዜውን/ዋን ሠጥቶ/ታ ሊሰራ የታሰበውን የኘሮጀከት ኃሳብ ወደ ንግድ ድርጅት እስኪለወጥ ድረስ በማዕከሉ ክትትል አድራጊነት ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/ች

3 ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ኗሪ የሆነ/ች

በዚህ መሰረት ፍላጎት ያላችሁ በዚህ የኢሜይል አድራሻ እስከ የካቲት 05/2008 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡ elyibeltal@gmail.com

ለበለጠ መረጃ ባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንፃ 4ኛ ፎቅ (G4- R3) ቢመጡ ወይም በስልክ ቁጥር 0918784624 በስራ ሰዓት ይደውሉ፡፡